Fidel Tube

Fidel Tube

Share

Welcome to my Channel
ፊደል Tube

04/05/2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 5 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,758 ላቦራቶሪ ምርመራ 5 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 140 ደርሷል።

25/04/2020

እስክንድር ነጋ በአሁን ሰዓት ኮልፌ ፖሊስ መምሪያ እንደሚገኝ ፓርቲው አስታውቋል

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ ዛሬ ሚያዚያ 17/2012 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ ከቤታቸው እንደወጡ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት የእስር ትዕዛዝ መታሰራቸውን በፌስቡክ ገጹ ያስታወቀው የፓርቲው ቃል አቀባይ አቶ ስንታየሁ ቸኮል “በአሁን ሰዓት ኮልፌ ፖሊስ መምሪያ እንዳለ አረጋግጠናል” ሲል በድጋሚ አስታውቋል፡፡
አቶ እስክንድር “…ኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 05 የድሆችን ቤት ፈረሳን አስመልክቶ ለምን ተገኘህ…” በሚል እንዳሰራቸውም ነው ቃል አቀባዩ በገጻቸው ያሰፈሩት፡፡

20/04/2020

ልዩ የስራ ጠባይ ላላቸውና ድጋፍ ለሚሹ የይለፍ ፍቃድ እየተሰጠ ነው

ከኮድ-2 ተሽከርካሪዎች የፈረቃ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ልዩ የስራ ጠባይ ላላቸውና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ የተሽከርካሪ የይለፍ ፍቃድ እየሰጠ መሆኑን የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
ከዛሬ ጀምሮ እንዲተገበር ሆኖ ከወጣው የፈረቃ እንቅስቃሴ መመሪያ ጋር በተያያዘ ጥያቄ ያላቸው አካላት ወደ ባለስልጣኑ እየመጡ ነው ያሉት የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ይግዛው ዳኘው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተቀመጠው የልዩ ድጋፍ አሰጣጥ መመሪያ መሰረት እየተስተናገዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለጤና እና ፋርማሲ ባለሙያዎች፣ ለሚዲያ አካላት እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች አዋጁን ለማስፈጸም በወጣው የትራንስፖርት ስምሪት መመሪያ አንቀጽ 10 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት በተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ እየታየ የይለፍ ወረቀት እየተሰጣቸው እንደሆነም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ:አላይን አማሀሪክ

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa

Opening Hours

00:00 - 12:00