Gebeya

Gebeya

Share

Here you can find Accessories for Men and Women,Watch,Neck chain,mobile devices,mobile covers,bands

23/07/2020

Gebeya News 🗞📰

የኢንተርኔት መቋረጥና የትራንስፖርት አገልግሎት...

'ዛይራይድ' የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት በሀገሪቱ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ሳቢያ ኢንተርኔት በመቋረጡ በ2 ሳምንት ግማሽ ሚሊዮን ብር (500,000 ብር) ገቢ ማጣቱን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ተናግሯል።

23/07/2020

Welcome back Ethiopia 🇪🇹😘🥰🇪🇹

26/06/2020

በመደጋገፍ፣ በሥራና በፅናት የሚገነባ ሀገር እንጂ በወሬ የሚገነባ ከተማም፤ ሀገርም የለምና ጸንተን ሀገራችንን እንገነባለን።

Takele Uma Banti

23/06/2020

Gebeya News 📰🗞

ተመድ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በግድቡ ዙሪያ ያለቸውን ልዩነት በውይይት እንዲፈቱት አሳሰበ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለቸውን ልዩነት በጋራ ውይይት እንዲፈቱት አሳሰበ።
በግብፅ በግድቡ ዙሪያ እየተደረገ ያለው ድርድር ከስምምነት ላይ ሳይደረስ የውሃ ሙሌት እንዳይጀመር ስትል ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ደብዳቤ ማስገባቷ ይታወሳል።

ሀገሪቱ የፀጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ መክሮ የውሳኔ ሀሳብ ያሳልፋል ብላ ብትጠብቅም፤ የዲፕሎማቲክ ምንጮች እንዳስታወቁት ግን ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት ስብሰባ እንደማያደርግ እና የውሳኔ ሀሳብ እንደማያሳልፍ አረጋግጠዋል።
ይልቁንም ሀገራቱ ልዩነታቸውን በጋራ እንዲፈቱ በደብዳቤ ብቻ እንደሚያሳውቅም ዲፕሎማቲክ ምንጮቹ አስታውቅዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ግብፅ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ጥያቄ ማቅረቧን ተከትሎ ኢትዮጵያ ያላትን አቋም በድጋሚ ለምክር ቤቱ ግልጽ አድርጋለች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለፀጥታው ምክር ቤት በላኩት ደብዳቤም፥ ኢትዮጵያ እየገነባች ያለችው ግድብ የታችኛውን የተፋሰስ አገር እንደማይጎዳ እና የሰላም እና ፀጥታ ስጋትም አለመሆኑን በድጋሜ አረጋግጠዋል።
ሱዳንም፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ በድርድር ሂደት ላይ እያለ ግብፅ ጉዳዩን ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት መውሰዷን እንደማትቀበል መግለጿ ይታወቃል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ጃሪክም በእለታዊ መግለጫቸው ህዳሴ ግብድን አስመልክቶ ለኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ መልእክት አስተላልፈዋል።
ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው፥ ሶስቱ ሀገራት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለቸውን ልዩነት በጋራ በመምከር መፍታት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
ሀገራቱ በአውሮፓውያኑ በ2015 በግድቡ ዙሪያ በፈረሙት የመርሆዎች ስምምነትን በመከተል ለልዩነቶቻቸው መፍትሄ ማበጀት ይገባቸዋል ሲሉም አሳስበዋል።
ምንጭ፦ cgtn.com

23/06/2020

Gebeya News 🗞📰

ሊደደርሱ የነበረውን የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፍ ተችሏል-- ኢመደኤ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ሰኔ 10፣ 12 ፣ 13 እና 14/2012 ዓ.ም መቀመጫቸዉን ግብጽ ያደረጉ የሳይበር ወንጀለኞች በኢትዮጵያ የኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጫና ለመፍጠር የተቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፉን አስታውቋል። የሳይበር ጥቃት ሙከራው የተቃጣው ሳይበር ሆሩስ ግሩፕ (Cyber_Horus Group)፣ አኑቢስ ዶት ሃከር (AnuBis.Hacker) እና ሴኪዩሪቲ ባይ ፓስ (Security_By_Passed) በተባሉ የሳይበር አጥቂዎች አማካይነት መሆኑን ኤጀንሲው ገልጿል፡፡ ወንጀለኞቹ ለረጅም ጊዜ ሲዘጋጁ የቆዩ እና ኤጀንሲው ሲከታተላችው የነበሩ ሲሆን በይበልጥ አርብ ሰኔ 12/2012 እና ቅዳሜ ሰኔ 13/2012 ከፍተኛ የሚባል የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ማድረጋቸውን ገልጿል። በዚህ ጊዜ ዉስጥ የ13 የመንግስት፣ 4 መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን የድረ-ገጽን የማስተጓጎል ሙከራ ማድረጋቸውን አስታውቋል ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡ የሳይበር ጥቃት ሙከራው በሀገሪቱ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፤ የደህንነት መስሪያ ቤቶች እና የግል ድርጅቶች ድረ-ገጽ ላይ ያነጣጠረ ነበር ተብሏል፡፡ ሳይበር ሆሩስ ግሩፕ፣ አኑቢስ ዶት ሃከር እና ሴኪዩሪቲ ባይ ፓስ የሳይበር ጥቃት አድራሽ ቡድኖች ሃላፊነቱን የወሰዱ ሲሆን ዋና አላማቸዉም ከህዳሴው ግድብ ዙሪያ በተለይ በውሃ አሞላል ጋር በተያያዘ ሁሉን አቀፍ ተጽእኖ በሀገሪቱ ላይ ለመፍጠር በማሰብ እንደፈጸሙት ተገልጿል፡፡ የሳይበር ጥቃት የተሰነዘረባቸው ተቋማት አብዛኛዎቹ በድረ-ገጽ ግንባታ ሂደት ደህንነታችው ታሳቢ ያላደረጉ ተቋማት፤ በቀጣይነት የደህንነት ፍተሻ ያላደረጉ እና ከፍተኛ የሳይበር ደህንነት ተጋላጭነት የነበረባቸው መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አረጋግጧል፡፡ ኤጀንሲው አስቀድሞ ቅድመ ዝግጅት በማድረጉ ምክንያት እና ይህን መጠነ ሰፊ የሳይበር ጥቃት መከላከል ባይችል ኖሮ ጥቃቱ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፤ ፖሊቲካዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ሊያስከትል ይችል እንደነበር የገለጸው ኤጀንሲው በመከላከሉም ሊደርሱ የሚችሉ ከፍተኛ አደጋዎችን ማስወገድ መቻሉን እና ይህንንም ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት አሳውቋል፡፡ በቀጣይም መሰል ጥቃቶች በስፋት፤ በረቀቀ መንገድ እና ከተለያዩ ስፍራ ሊሰነዘር እንደሚችል ግምት ውስጥ በማስገባት ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት .et domain ከመጠቀማቸው በፊት የድረ-ገጻቸውን ደህንነት አረጋግጠው እንዲጠቀሙ፤ ራሳቸውን ከሳይበር ደህንነት ተጋላጭነት ለመከላከል እና አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚኖርባቸው ኤጀንሲው አሳስቧል። ተቋማት ከኤጀንሲው ጋር በመተባበር ያለባቸውን የደህንነት ተጋላጭነት መድፈን እንዳለባችው እና የተለያዩ የሳይበር ደህንነት ጥቃት ሙከራ ሲያጋጥማቸውም ሆነ ሙያዊ ድጋፍ ሲያሻቸው ለኤጀንሲው በማሳወቅ አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ ማግኘት እንደሚችሉ አስታወቋል። ባለፉት ሁለት ቀናት ትብብር ላደረጉልን ተቋማት እና ግለሰቦች በተለይ ለኢትዮ ቴሌኮምና ለኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ኤጀንሲው ምሰጋና ማቅረቡን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
ኢዜማ

21/06/2020

የፀሐይ ግርዶሽ እና ጥንቃቄ!

የፀሐይ ግርዶሽን በዓይን በቀጥታ መመልከት ቋሚ ጉዳት በዓይን ላይ ያደርሳል። ግርዶሹን ለመመልከት ፦

1. ደረጃውን የጠበቀ የግርዶሽ መነፅር መጠቀም

2. ፒን ሆል ካሜራ ወይም በአነስተኛ ቀዳዳ ወደ ድፍን ካርቶን የሚገባውን ብርሃን የሚስለውን ስእል ጀርባ ለፀሐይ በማዞር መመልከት

3. ጨለማ ክፍል ውስጥ በቀዳዳ የሚገባውን የፀሐይ ብርሃን መሬት ወይም ግድግዳ ላይ የሚሰራውን ስእል መመልከት

4. በዛፎች ቅጠል አልፎ መሬት ላይ የሚያርፈውን የፀሐይ ስእል መመልከት

5. ለቴሌስኮፕም ሆነ ባይነኩላር የፀሐይ ብርሃን መጣኝ ደረጃውን የጠበቀ ፊልተር ግጥሞ መመልከት

6. ግርዶሹን የሚያሳዩ የቀጥታ ስርጭቶችን መመልከት

የፀሐይ መነፅር ፣ ፍሎፒ ዲስክ ፣ የፎቶ ፊልም ፣የራጅ ፊልም እና የመሳሰሉት ቁሶች መጠቀም በዓይን ላይ ጉዳት ያደርሳል

Want your business to be the top-listed Clothing Store in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Addis Ababa
00251