Glorious Life Church
The gospel of Jesus Christ is the only solution for man kind, so keep following us as we follow Jesus Christ. You are blessed.
17/05/2026
ቸርች እንዴት ነበር?
(How was Church?)
"...የጸና እምነት..."
✍️ የእምነት መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ የሚፈጠር ጽኑ የሆነ መረዳት ነው። እዉነተኛ እምነት በሰው ጥረት የሚፈጠር ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ በሚሆን እርዳታ ነው። እምነት የሚሰራው በውስጥ ሰው ውስጥ ስለሆነ፤ መንፈስ ቅዱስ ጠንካራ እምነትን በመፍጠር ረገድ ጥልቅ ተሳተፎ አለዉ።
በመንፈስ ቅዱስ የሚፈጠር ጽኑ መረዳት ነው ስንል እምነት አንድ ሃገር ሊሆን ይችላል ብሎ ከመስማማት በላይ ነው ማለታችን ነው። ማለትም እምነት ሙሉ በሙሉ መረዳት መረታት ነው። አብርሃምም ለእምነት ሕይወት ምሳሌያችን የሆነው በልቡ ሙሉ እምነት እና መታመን ነበረው::
“ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም።”
— ሮሜ 4፥20-21
ሌላው ልንረዳ የሚገባን እውነት የእምነት መንፈስ በእግዚአብሔር በተገለጠው ቃል የተመሰረተ ነው። ይህም ማለት ከሎጎሱ ቃል በወጣው በሬማ ቃል ማለታችን ነው።
በዚህም ምክንያት ነው እምነት ስር ሊኖረው ይገባል የምንለው፤ ያ ስር ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል ነው። የእምነት መሠረት የእግዚአብሔር ቃል ሲሆን ይህ እምነት እንዲመጣ ያለ ማቋረጥ ቃሉን መስማት ይኖርብናል።
“እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።”
— ሮሜ 10፥17
በመጨረሻም ዋናው መሠረታዊ ሀሳብ እምነት የሚጀምረው "እኔ ምን እፈልጋለሁ?" በማለት ሳይሆን "እግዚአብሔር ምን ብሏል?" በማለት ነዉ። ያለ እግዚአብሔር ቃለ መንቀሳቀስ ደግሞ ድፍረት እንጂ እምነት አይደለም። ስለዚህ በእምነት መንፈስ በማይናወጥ በእግዚአብሔር ላይ ባለ መተማመን ባለው ምርት ተጠቃሚ እንሁን።
“ከክፉ ነገር አይፈራም፤ በእግዚአብሔር ለመታመን ልቡ የጸና ነው።”
— መዝሙር 112፥7
ቀን እሁድ 09/09/2018
⛪️ የክብር ሕይወት ቤተክርስቲያን
አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
መልካም የመነሳትና የማብራት ምሽት
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the place of worship
Telephone
Website
Address
Haile G/Selasie Street
Addis Ababa
GLC