YESUF APP
በዚህ ፔጅ አዳዲስ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችና እንደዲሁም የሞባይል አፕሊኬሽኖች አጠቃቀም የምናቀርብበት የፌስቡክ ገፃችን ነው Follow በማድረግ ይከታተሉ
20/11/2025
ወይ ዘንድሮ የማንሰማው ነገር የለ የሞቱ ዶሮዎችን በማረድ እና በማሸግ ለተለያዩ ሱቆችና ሆቴሎች ለማከፋፈል ሲዘጋጁ የነበሩ ግለሰቦች ተያዙ
በአዲስ አበባ ከተማ በሾላ ገበያ የሞቱ ዶሮዎችን በማረድ እና በማሸግ ለተለያዩ ሱቆችና ሆቴሎች ለማከፋፈል ሲዘጋጁ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታወቀ።
ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ከሰላም ፀጥታ ፅ/ቤት እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ በጋራ በመሆን ባደረገዉ ድንገተኛ ኦኘሬሽን ነው።
በተደረገው ክትትልና የተቀናጀ ኦፕሬሽን ግለሰቦቹ የሞቱ ዶሮዎችን በማረድ እና በማሸግ ለተለያዩ ሱቆችና ሆቴሎች ለማከፋፈል ሲዘጋጁ በነበረበት ሁኔታ መያዛቸው ተጠቁሟል።
በዚህም የታሸገ ዶሮ በቁጥር መቶ 100 ተበልቶ ለመታሸግ የተዘጋጀ አርባ ሁለት 42 መያዝ መቻሉን ከባለሥልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
================
ምንጭ:–የአዲስ ስታንዳርድ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
1000