Ethio Info

Ethio Info

Share

Everyone has the same eyes but not the same view.

14/06/2025

ሰበር መረጃ ‼️

በርካታ የኢራን ሚሳኤሎች ወደ እስራኤል የአየር ክልል እየገቡ ነው።
እስራኤል ለማክሸፍ እየተረባረበች መሆኑን መረጃዎች እያወጡ ነው።


=====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
Like & Share በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣

Photos from Ethio Info's post 14/06/2025

እየተወሳሰበ የመጣው የቀይባህር ጉዳይ‼️
ከደቂቃዎች በፊት የኢራን ብሔራዊ ቴሌቪዥን በአወጣው መረጃ ኢራን ኢትዮጵያን በቀጥታ አደጋ ውስጥ ሊከት የሚችለውን እርምጃ ወስዳለሁ ስትል ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።

በዚህም መሰረት ኢራን "እስራኤልን እንዳላጠቃ ለመከላከል የሚሞክሩትን አሜሪካ ፣ዩኬ፣ የኢዩ ሀገራትን ወታደራዊ ጣቢያዎችንና መርከቦቻቸውን በቀጥታ ማጥቃት እጀምራለሁ" ስትል ይፋዊ መግለጫ የሰጠች ሲሆን ፤እንደሚታወቀው ሁሉም የተጠቀሱት ሀገራት የወታደራዊ ጣቢያና ባህር ሃይላቸው በአንድ ላይ ተከማችተው የሚገኙት እና የሚተላለፉባት የበሬ ግንባር የምታክለውና የ120 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን ህልውና የኪራይ ወደባችን በሆነችው ጂቡቲ ነው።

ኢራን እንዳለችውም በጅቡቲ የሚገኘውን የአሜሪካ የጦር ቤዝ ለማጥቃት በቀጥታ የጦር ቀጠና ምታደርጋት ከሆነ ያለ አንዳች ጥርጥር ለኢትዮጵያ ከባድ አደጋ ይዞ ይመጣል። ለኢትዮጵያ import እና export ይቆማል ማለት ነው።
አሁን ላይ ኢራን በጅቡቲ በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ቤዝ ላይ ጥቃት የመፈፀም እቅድ ስለመያዟ የታወቀ ነገር የለም።


=====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
ገጻችንን Share & Like በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣

Photos from Ethio Info's post 14/06/2025

#ሞሳድ‼️
"በአለም ላይ የተሳካ ወታደራዊ ኦፕሬሽን በመስራት ማንም አይስተካከለንም" የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር‼️
"መፍትሄ ማምጣት ካልቻልክ የችግሩ አካል ነህ" ይላሉ የሞሳዱ ዳይሬክተር ኤሚት....
- ሞሳድ መንፈስ ነው። የማይገኝበት የምድራችን ቦታ የለም።
- በዘመቻ አልማዝ፦ አዲሱን የራሽያ ሚግ- 21 ከራዳር ቁጥጥር ውጭ በመብረር ከኢራቅ መንግስት ሰርቀውታል።
- ከፈረንሳይ ሸርቡር ወደብ ዘመናዊ ሚሳየል የተገጠመላቸውን የጦር መርከቦች ያለምንም ኮሽታ ሰርቀውታል
- በዘመቻ ፕላምበት፦ 200 ቶን የሚመዝን ውድ ዩራኒየም ማንም ሳይነቃ ከአውሮፓ ሰርቀዋል። ይሞታል እንዴ?
ሞሳዶች እንዲህ ይላሉ " አንድ የመሥክ ሰላይ ከሙሉ ባላቲዎን ሠራዊት ይበልጣል " በትክክልም በተግባር አሳይተውታል።

- የኤሊ ኮኸን ገድል በሶሪያ ምድር ድንቅ ነበር። እስራኤል የጎላን ተራራዎች ከሶሪያ ላይ በቁጥጥር ስር ታውል ዘንድ ኤሊ ኮኸን በደማስቆ ሰይጣን መሆን ነበረበት።

ኤሊ ኮኸን በጠላት ቀጠና (በሶሪያ) ምክትል የመከላከያ ሚኒስቴር ለመሆን ተቃርቦ ነበር። እስራኤላውያን ኤሊ ኮኸንን "የኛ ሰው በደማስቆ " እያሉ ዝንት ዓለሞ ሲያደንቁት ይኖራሉ።
- ወልፍጋንግ ደግሞ ወደ ግብጽ የተላከ የእስራኤል ሰይጣን ነበር። የቤተ-መንግስት ባለሟል ለመሆን ጊዜ አልወሰደበትም ነበር። ለማንም የማይፈቀደውን የግብጽን ወታደራዊ ምስጢር እንዲጎበኝ ተፈቅዶለታል። እስራኤላውያን "በካይሮ የቴላቪቭ አይን" ይሉታል።

- በ6ቱ ቀን የእስራኤልና የአረቦች ጦርነት የግብጽን የጦር ጀቶች (ሚጎች) በራሳቸው አዘዋቸዋል። የግብጽም የጦር መኮንኖች በመምሰል የግብጽን የምድር ጦር በመምራት ትእዛዝ ሰጥተዋል።

- ከሂሊኮፍተር ላይ የሚወረወሩት የእስራኤል ኮማንዶዎች የዓለምን ሕዝብ ቆሞ እንዲያጨበጭብ አስገድደውታል ... የዚህ የአርያን ሻሮን የጦር ንድፍ በአሜሪካንና በአውሮፓ በሚሊታሪ አካዳሚዎች እንደ አንድ ትምህርት ይሰጣል።


- የያሲር አረፋትን ምክትል "አቡ ጀሀድን " በቱኒዚያ ለመግደል የውጭውን በር ሰብረው፣ ሹፌሩን ገድለው ፣ ሁለቱን ጠባቂዎቹን ገድለው፣ ሳሎኑን አልፈው ማንበቢያ ክፍሉ ገብተው ለመግደል ያቀዱት 22 ሰከንድ ሲሆን እነሱ ግን በ13 ሰከንድ ኦኘሬሽኑን ጨርሰውታል። መንፈስ ነገር ናቸው።

‼️90 ደቂቃ በኢንተቤ‼️

#በመካከለኛው ሌሊት አራት የጦር ጀቶች፣ ሁለት ቦይንግ የህዝብ አውሮኘላን ፣100 ኮማንዶዎች የአረቡን የአየር ክልል እየሰነጠቁ ፤ ከራዳር ክልል ውጭ እየተወነጨፋ ዩጋንዳ ኢንቴቤ ከተማን ወረሯት... በ30 ደቂቃ አስደናቂ ጦርነት የዪጋንዳ ሚጎችን ወደ አፈርነት ቀየሩት... ሁለተኛው ግሩኘ በዮናታን ናታኒያሁ የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር የቢኒያሚን ናታኒያሁ ታላቅ ወንድም የሚመራው ቡድን የታገቱትን ይሁዲዎች ካስለቀቀ በኋላ... አጠቃላይ በ90 ደቂቃ ውስጥ የጽዮናዊቷን ሀገር ተልእኮ በድል አጠናቀው ወደ ቴላቪቭ በጀግንነት ሲመለሱ ላዬ የጽዮንን ልጆች አለማድነቅ ክፋት ይሆናል።

‼️ቴክኖሎጂ‼️
- ከ2006 እ.ኤ.አ በፊት ሞሳድ በከፍተኛ ጥበቃ የተቆለፉ ኮምፒተሮችን በመሥበር ዳታውን የሚገለብጥ "ቴምፐስት" የተባለ ረቂቅ መሣሪያ ፈጥረዋል።

- ስማርት ዳስት..የጉንዳን መጠን ያላቸው መሳሪያዎች ሲሆኑ በጠላት ቀጠና ያለውን ማንኛውንም ድምጽ ቀርጸው ለሞሳድ ቢሮ ይልካሉ። ከአንድ ወር በኋላ እራሳቸውን ያጠፋሉ።


=====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
ፔጃችንን Share & Like በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ

13/02/2025

"ኢትዮጵያን ከኛ በፊት አለም አያውቃትም ነበር፣በዚህ አለም አልነበረችም፣ሌላው ይቅር ኢትዮጵያ ጫማ መስራት አትችልም ነበር (መሽረፈት) ማራገብያ እንኳን መስራት አትችልም ነበር":-አቦይ ስብሃት‼️

አቦይ ስብሀት ነጋ ዝምታቸውን ሰበሩ፡፡ አንጋፋው የሕወሓት መስራች አቦይ ስብሀት ዘለግ ካለ ዝምታ በኋላ በአንድ የትግረኛ ሚዲያ ተከስተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአሜሪካ ድጋፍ ነው ስልጣን የያዙት በሚል ንግግራቸው የሚታወሱት አቦይ ስብሀት፤ ተክደናል፣ በደም የገነባናት ኢትዮጵያ ትመለስልን፣ መታጠቅ መደራጀት አለብን የሚሉ እና መሰል ሀሳቦችን ሲያንጸባርቁም ተደምጠዋል፡፡

የቀድሞው የህወሓት ሊቀመንበር እና መስራች አቶ ስብሀት ነጋ በደም የገነባናት ፌደራላዊት ኢትዮጵያ ትመለስልን በማለት በትግረኛ በሰጡት ቃለመጠይቅ ገልጸዋል። አማራ ኦሮሞ እያሉ ህዝብን እንደጠላት ማየት የጠላትን ፍላጎት ማሳካት ነው ሲሉም ተደምጠዋል። ትግላችንም ይህ መሆን አለበት የሚሉት አዛውቱ ፖለቲከኛ፤ ከወረዳ አስመላሽ ኮሚቴነት እንውጣ ብለዋል። አቶ ስብሀት አማራ ኦሮሞ እያልን ህዝብን እንደ ጠላት ማየት ይብቃ የሚል ሀሳብ ሲያነሱ ቢደመጡም፤ እሳቸው የመሰረቱት ድርጅት ግን ለረጅም አመታት አንድን ህዝብ እንደ ጠላት ፈርጆ የሚንቀሳቀስ ነበር፡፡ አሁን ታድያ ያንን የድርጅታቸውን ሀጢያት ሳይናዘዙ ህዝብን እንደ ጠላት ማየት ይብቃ ማለታቸው ጥያቄ አስነስቶባቸዋል፡፡

የሆነው ሆኖ አዛውንቱ ፖለቲከኛ ስለ ወቅታዊው የሕወሓት ሽኩቻ ተክደናል ሲሉ ይናገራሉ፡፡ የአሁኑ እና የቀድሞው የሕወሓት ክፍፍል የተለያየ ነው የሚሉት አቶ ስብሀት፤ የበፊቱ ከክህደት ሳይሆን ከድክመት የሚመነጭ ነበር የአሁኑ ግን በክህደት የተፈፀመ ነው ሲሉ ያብራራሉ። በክህደት የወነጀሉት የትኛውን ወገን እንደሆነ በግልጽ ባያስቀምጡም ‹‹ያሁኖቹ ከጠላትም ጠላት የሆኑ ስዎች ናቸው›› በማለት በትግራይ ህዝብ ላይ ጀኖሳይድ የፈፀሙ ወታደሮችን እሰከመፍታት ደርሰዋል በማለት ወንጅለዋል።

ሕወሓትን ወደ ብልፅግና ለመቀየር የሚጥሩና የትግራይ ብሔር እንዳይኖር ደምሳሽ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሀይለች የፈጠሩት ነው ሲሉም ወቅታዊውን የህወሓት ቀውስ ገልፀውታል ። ፖለቲካችን በርዕዮተ አለም መመራት አለበት ያሉት አቶ ስብሃት ለዚህም ከ46አመታት በፊት በመጀመሪያው የህወሓት ድርጅት መስራች ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችን አሁንም መልሶ ማየትና መተግበር ይጠቅማል በማለት ተናግረዋል፡፡ እነዚያ ዉሳኔዎችም ማንቃት ፣ ማደራጀት ፣ማስታጠቅ ፣ማሰማራት እና መገምገም ናቸዉ በማለት ዘርዝረዋቸዋል። አክለውም ከህዝብ መራቅ የለብንም መመካከር አለብን በማለት በትግረኛ በሰጡት ቃለመጠይቅ ገልጸዋል፡፡

ስብሐት ነጋ ከወይን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ከተናገሩት የተወሰደ
Ethio Info
=====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
ቻናላችንን Like, Share & follow በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣

13/02/2025

.........................
የፑቲን አስደናቂ ንግግር ስለ አፍሪካውያን!
አፍሪካ ለአፍሪካውያን የቀብር ቦታ ብቻ ናት
የራሺያ ፕሬዘዳንት ቪላድሚር ፑቲን ከተናገሩት:-
አንድ አፍሪካዊ ሃብታም ሲሆን....

❖ገንዘቡን የሚያስቀምጠው በስዊዝ ባንክ ነው፣
❖ለህክምና የሚሄደው ፈረንሳይ ነው፣
❖ኢንቨስት የሚያደርገው ጀርመን ውስጥ ነው፣
❖ዕቃ የሚገዛው ዱባይ ነው፣
❖የሚጠቀመው ቻይና ነው፣
❖ለፀሎት የሚሄደው ሮም እና መካ ነው፣
❖ልጆቹ የሚማሩት አውሮፓ ነው፣
❖ለቱሪዝም ጉብኝት የሚሄደው አሜሪካ እና ካናዳ ነው።

️ሲሞት ግን የሚቀበረው በእናት ሃገሩ አፍሪካ ውስጥ ነው። አፍሪካ ለአፍሪካውያን የቀብር ስፍራ ብቻ እንጂ ሌላ አይደለችም። የመቃብር ቦታ ደግሞ እንዴት ያድጋል? "ሲል ይጠይቃል?

12/02/2025

ኢትዮጵያ የከፋ ሙስና ከሚታይባቸው ሀገራት ተርታ ተሰለፈች‼️
👉ከ180 አገራት 99ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች❗

በዓለም ላይ በሕዝባዊ አገልግሎቶች ዘርፍ ያለውን የሙስና ሁኔታ እየተከታተለ ዓመታዊ ሪፖርት የሚያወጣው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በተጠናቀቀው የአውሮፓውያኑ 2024 ዓመት የአገራትን የሙስና ደረጃን ይፋ አድርጓል።

ሪፖርቱ የ180 የዓለም አገራትን የሙስና ደረጃ ያወጣ ሲሆን ከፍተኛውን ነጥብ በማግኘት ሙስና በጣም በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኝባቸው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እና ግጭት የሌለባቸው አገራት ሲሆኑ፣ ሙስና ሥር የሰደደባቸው ደግሞ ግጭት እና ቀውስ ያለባቸው አገራት መሆናቸውን አመልክቷል።

በአገራት ውስጥ ያለውን የሙስና ደረጃ ለመመዘን ከሚሰጠው ከፍተኛ የሙስና ነጥብ ከሆነው 100 ውስጥ 37 በማግኘት ኢትዮጵያ ከ180 አገራት 99ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ሪፖርቱ አስፍሯል።

ይህ የአገራት የሙስና ሁኔታን አመላካች የሆነው ዝርዝር በዓለም አቀፍ ደረጃ በስፋት የሚጠቀስ ሲሆን፣ ባለሙያዎች እና የንግድ ሰዎች በዋናነት ከሙስና አንጻር የሚገመገሙት የአገራት ሕዝባዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ናቸው።

በዓለም ዙሪያ የፀረ ሙስና እንቅስቃሴን በማራመድ በሚታወቅ በትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል አማካኝነት በየዓመቱ የሚወጣው ይህ የአገራት የሙስና ደረጃ ጠቋሚ ሪፖርት ውስጥ አብዛኞቹ የዓለም አገራት ተካተዋል።

ያለፈው ዓመትን በሸፈነው በዚህ ሪፖርት ኢትዮጵያ ከ180 አገራት በሕዝብ አገልግሎት ዘርፍ ባለ ሙስና 99ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን፣ ይህም ቀደም ባለው የአውሮፓውያን ዓመትም በተመሳሳይ ደረጃ ላይ እንደነበረች ሪፖርቱ አመለክቷል።

በሪፖርቱ መሠረት ከሙስና አንጻር ከአጎራባች አገሮች አንጻር ኢትዮጵያ በተሻለ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን፣ በዙሪያዋ ያሉ አገራት በሙሉ ከኢትዮጵያ ከፍ ባለሁኔታ ሙስና እንዳለባቸው ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት ኬንያ 32 ነጥብ በማግኘት 121ኛ፣ ጂቡቲ በ31 ነጥብ 127ኛ፣ በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው ሱዳን በ15 ነጥብ 170ኛ፣ ኤርትራ በ13 ነጥብ 173ኛ፣ ሶማሊያ በ9 ነጥብ 179ኛ እና ደቡብ ሱዳን በ8 ነጥብ 180ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

የአገራትን የሙስና ሁኔታን በሚያሳየው ደረጃ ላይ ከሚሰጠው 100 አጠቃላይ ነጥብ ከግማሽ በላይ የሚያስመዘግቡ አገራት በጥሩ ሁኔታ ላይ ያሉ የሚባሉ ናቸው።

ከዚህ አንጻር በአጠቃላይ በአፍሪካ በተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኙት አገራት ሲሸልስ (በ72 ነጥብ 18ኛ)፣ ኬፕ ቬርዲ (በ62 ነጥብ 35ኛ) ቦትስዋና (በ57 ነጥብ 43ኛ) እና ሞሪሺየስ (በ51 ነጥብ 56ኛ) ደረጃ ላይ ይገኛሉ።


=====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
ቻናላችንን Like, Share & follow በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ!

12/02/2025

ህወሃት ከተፈናቃዮች ገንዘብ እየሰበሰበ ነው የሚል ክስ ቀረበበት‼️

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ህወሓት በመጠለያ ከሚገኙ ተፈናቃዮች በግዳጅ መዋጮ እየሰበሰበ መኾኑን በመግለጽ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ቅሬታ አቅርቧል።

የሕወሓት ባለሥልጣናት ከተፈናቃዮች በነፍስ ወከፍ 200 ብር በግዳጅ የሚሰበስቡት፣ "ፓርቲውን ለማዳን እና ለፓርቲው 50ኛ ዓመት በዓል ማክበሪያ" በሚል ምክንያት እንደኾነ ተገልጧል::

ህውሃት በበኩሉ ገንዘብ አልሰበሰብኩም የሚል ማስተባበያ ሰጥቷል።

Ethio Info
=====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
ቻናላችንን Like, Share & follow በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ

12/02/2025

ጥቆማ‼️ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር❗
ሰላም Ethio Info ፤ ወቅታዊ እና ተደራሽ መረጃዎችን በፍጥነት ስለምታደርሰን ምስጋናችን ከልብ ነው፡፡

ያንተ ፌስቡክ ብዙ ተከታዮችን ባይኖሩትም በቅርቡ የተከሰት አዲስ ክስተት ስለሆክ እባክህ ይችን ጥቆማ አድርስልኝ፡፡

ለከንቲባ ፅህፈት ቤት እንዲሁም ሌት ከቀን በኮሊደር ስራው ለተሰማሩ አመራሮች ይጠቅማል ብየ ስላሰብኩ ነው፡፡

ከላይ በምስሉ የምትመለከቱት ቦታ በቦሌ ቡልቡላ እና በቦሌ ሚካኤል መካከል የሚገኝ የክሬቸር ሳይት ነው፡፡ ይህ ሳይት ለአየር መንገዱ በጣም ቅርብ የሆነ እና አውሮፐላን የሚወርድበት እንዲሁም የሚንደርድርበት አቅጣጫ ነው፡፡

ከዚህ ሳይት የሚወጣው አቧራና የሬንጅ ማቅለጫው ጭስ ሙሉ በሙሉ ወደ መሐል ከተማና ወደ አየር መንገዱነው የሚሰራጨው፡፡ ስለዚህ የሚመለከተው አካል ቦታው ላይ ተገኝቶ ጥናት አድርጎ ብክለቱን በሚቀንስ ሁኔታ ሥራው እንዲሠራ ምክረ ሀሳብ እንዲሰጧቸው ጥቆማ እናቀርባለን፡፡

#ከቦሌ
=====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
ቻናላችንን Like, Share & follow በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ

12/02/2025

"በአምስት ዓመት ውስጥ ብቻ ከ250 በላይ አሽከርካሪዎች በሥራ ላይ እያሉ ተገድለዋል" ጣና የአሽከርካሪዎች ማህበር‼️

በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች የሚፈፀሙ እገታዎች እና ግድያዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ባለመወሰዱ አዳዲስ መስመሮችም የእገታ ተግባራት እየተፈፀመባቸው ነው ሲል ጣና የአሽከርካሪዎች ማህበር ለአሐዱ ገልጿል፡፡

በቅርቡም በጭልጋ እንዲሁም በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች መተሃራን ጨምሮ የሞቱ አሽከርካሪዎች ቁጥር በርካታ መሆኑን የማህበሩ ዋና ፀሐፊ አቶ ሰጡ ብርሃን ተናግረዋል፡፡

ከአዋሽ መተሃራ የተሸከርካሪዎች መቃጠልና የሚፈፀሙ እገታዎች ተበራክተው መቀጠላቸውን የሚናገሩት የማህበሩ ዋና ፀሐፊ፤ "በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ከዚህ ቀደም በስፋት እገታ ያልነበረባቸው እንደ ደባርቅ እና ከጎንደር መተማ ያሉ መንገዶች ላይ ተመሳሳይ ድርጊቶች እየተፈጸሙ ነው" ብለዋል፡፡

በዚህም የመተማውን መንገድ በመስጋት አሽከርካሪዎች በሌላ ተለዋጭ መንገዶች እየሄዱ ለተጨማሪ ወጪ እና እንግልት እየተዳረጉ እንደሚገኙ አቶ ሰጡ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

"ከዚህ ቀደም ያልነበሩ ቦታዎች ላይ እገታ፣ ግድያና ዘረፋ መበራከቱ ከዚህ ቀደም የተወሰደ እርምጃ ባለመኖሩ ነው" ሲሉም ወቅሰዋል፡፡

አክለውም "አንድ አጋች ከአሽከርካሪ ላይ እስከ 500 ሺሕ እና 1ሚሊዮን ብር ድረስ የሚቀበል ከሆነና የሚጠይቀው ከሌለ መበራከቱ የሚቀንስበት ሁኔታ የለም" ብለዋል፡፡

ማህበሩ ባለፉት አምስት ዓመታት ከአሽከርካሪዎች መታገትና ጉዳት መድረስ በዘለለ የሞቱ አሽከርካሪዎች ከ250 በላዩ መደረሱን የማህበሩ ዋና ጸሀፊ ገልጸዋል፡፡

ይህ ሁኔታ በተለይም ከወደብ ጋር የሚገናኙ አካባቢዎች ላይ እየፈጠረ ያለው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ የሚመለከተው አካል መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል ተብሏል፡፡

Ethio Info
=====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
ቻናላችንን Like, Share & follow በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ

12/02/2025

አስገዳጅ የባንኮች ውህደት እንደሚኖር ብሄራዊ ባንክ ገለፀ‼️
አስገዳጅ የባንኮች ውህደት እንደሚኖር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ማሞ እስመለአለም ምህረቱ ገለፁ።

እንደ ገዥው ገለፃ የውህደቱ ዋነኛ አላማ ችግር ያለባቸውን ባንኮች ለማዳን ነው ብለዋል።

በቅርቡ የፀደቀው የባንክ ስራ አዋጅ የባንኮችን ውህደት በተመለከተ የገለፀ ሲሆን ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ እየተጠበቀ ነው።

ብሄርን መሰረት አድርገው ስለተመሰረቱ ባንኮች በውህደት ወቅት ስለ ሚያጋጥም ተግዳሮት የተጠየቁት አቶ ማሞ ውህደትን ጨምሮ አጠቃላይ የባንክ ስራ በህግ እንደሚመራ አስታውሰው፣ "ከዚህ አኳያ ከብሄር ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ በተለይ በአስገዳጅነት የሚፈፀም ውህደት ላይ የሚኖረው ተፅእኖ አናሳ ነው፣" ብለዋል።

Via:-
=====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
ቻናላችንን Like, Share & follow በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ

Photos from Ethio Info's post 12/02/2025

ቢሊየነሩ ኤለን መስክ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ እንዲዘጋ ሀሳብ አቀረቡ።

በአዲሱ የመንግሥት ተቋመትን አፈጻጸም የሚገመግመውና በርካታ ውሳኔዎችን እያስተላለፈ የሚገኘው Department of Government Efficiency እያሥተዳደሩ የሚገኙት ኤሎን መስክ የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ እንዲዘጋ በኤክስ ገጻቸው ሀሳብ አቅርበዋል።

"ማንም ሰው አያዳምጣቸውም ይዘጉ" ይላል ያሰፈሩት ጽሑፍ።

የአሜሪካ ድምፅ የሬዲዮና እና የቴሌቪዥን ሥርጭት መሠረቱን በአገረ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገና በ47 ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች ሥርጭቱን የሚያከናውን ተቋም ነው።

ይኸው ተቋም በአሜሪካ ፌደራል መንግሥት በጀት የሚመደብለት ተቋም ሲሆን ከ278 ሚሊዮን በላይ ሳምንታዊ ተመልካች እና አድማጮች እንዳሉት ይነገራል።

Ethio Info
=====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
ቻናላችንን Like, Share & follow በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተላሉን

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

Addis Ababa