Kana
news and sport
05/07/2023
ዮናስ ዝምታውን ሰበረ !
"ድምፅ ለሆናችሁኝ በሙሉ አመሰግናለሁ!" ታግቶ የነበረው አቶ ዮናስ የሺጥላ የደረሰበትን ነገር እንዲህ ሲል አብራርቷል።
በመጀመሪያ ከኔ መጥፋት ጋር ተያይዞ ድምፅ ለሆናችሁኝ እና ለተባበራችሁኝ በሙሉ በጣም አመሰግናለሁ :: ውለታችሁን እግዚአብሔር ይክፈል ::
እኔ ላይ የደረሰውን ነገር አጠር አድርጌ ለማስረዳት እሞክራለሁ
አርብ ሰኔ 16 ከጠዋቱ 4 ሰአት ላይ የስራ ቀጠሮ ስለነበረኝ የተቀጣጠርንበት ቦታ ቀደም ብዬ ነበር የደረስኩት:: የቀጠሮ ቦታው ቦሌ ፍሬንድሽፕ አካባቢ ሎፍት የተባለ ሆቴል ስለነበር መኪናዬን ፓርክ አድርጌ እየጠበኩ ነበር :: ከዚያ ቀን በፊት በተደጋጋሚ ለስራ ጉዳይ በተመሳሳይ ቦታ ያገኘሁት በዚህ ሰዓት በስም መጥቀስ የማልችለው ባለሃብት ደውሎ እሱ መኪና ውስጥ ሆነን ብናወራ የተሻለ ስለሚሆን ፓርኪንግ ቦታው ላይ እየጠበኩህ ነው ስላለኝ ወደሱ መኪና ሄድኩኝ :: መኪና ውስጥ ገብቼ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ እዛው አካባቢ ባለቤቱ እንዳለችና ከሷ ጋር በጋራ ስለ ስራው እናውራ ብሎኝ ወደሷ መሄድ ጀመርን:: ትንሽ እንደተንቀሳቀስን ሌሎች ማንነታቸውን የማላውቃቸው የታጠቁ ሰዎች መኪናውን በማስቆምና ውስጥ ገብተው ምንም አይነት ድምፅ እንዳላሰማና እና ከነበርኩበት ጋቢና ወደ ሗላ ወንበር እንድገባ በማስገደድ የሚሉኝን ካላደረኩ እርምጃ እንደሚወስዱብኝ አስፈራርተው ፊቴን ሸፍነው ወደማላውቀው ቦታ በመውሰድ ለተከታታይ 10 ቀናት አግተውኛል::
ከዚህ በላይ ዝርዝር መረጃ መስጠት የማልችለው በአ/አ ፖሊስ ልዩ ልዩ ወንጀል ምርመራ ክፍል ጉዳዩ የተያዘና ምርመራ እየተካሄደበት በመሆኑ እንዲሁም በእኔና በቤተሰቦቼ ላይ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ነው::
ስለዚህ ማንኛውም በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የሚፈልግ አካል ካለ በአ/አ ፖሊስ ልዩ ልዩ የወንጀል ምርመራ ክፍል ሄዶ ማጣራት ይችላል::
እኔ በጠፋሁ በ 24 ሰአታት ውስጥ ቤተሰቦቼ ከነመኪናዬ መጥፋቴን ለፖሊስ አሳውቀው ስለነበር የፖሊስ ፍለጋም የሶሻል ሚዲያ ድምፅም በጣም ከፍተኛ እንደነበር ከወጣሁ በኃላ ለመረዳት ችያለሁ ::
አፍነው የወሰዱኝ ግለሰቦች ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት አላደረሱብኝም:: ነገር ግን የስነ ልቦናው ጉዳት እንዳለ ሆኖ በቂ ምግብና እንቅልፍ ባለማግኘቴ እንቅስቃሴ ለማድረግ አቅም አጥቼ ነበር::
በ 10 ኛው ቀን በግምት ወደ 8 ሰአት አካባቢ አይኔን ሸፍነው መኪና ውስጥ ካስገቡኝና ረዘም ካለ ጉዞ በኃላ በአገቱኝ ሰዓት የወሰዱብኝን የግል ንብረቶች የመኪና ቁልፍን ጨምሮ መልሰውልኝ ብስራተ ገብርኤል አካባቢ ከመኪናው አስወርደው ጥለውኝ ሄደዋል ::
ወደቤት እንደተመለስኩም ቤተሰቦቼ ህክምና እንዳገኝ አድርገዋል :: በእለቱም ጉዳዩ ተይዞ ወደነበረበት ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ የደረሰብኝን ጉዳይ አስረድቼ ቃሌን ሰጥቻለሁ ::
መኪናውንም ሰኔ 16 ፓርክ ባደረኩበት ሎፍት ሆቴል ፓርኪንግ ቦታ ለ 10 ቀናት ሳይንቀሳቀስ መቆየቱን ፖሊሶች በአሻራ ምርመራ አረጋግጠው መልሰውልኛል ::
የመጥፋቴን ዜና ከሰማችሁበት እለት ጀምሮ ድምፅ ስትሆኑኝ ለነበራችሁ በፀሎት በሃሳብ ቤተሰቦቼን በማፅናናት በተለያየ መንገድ ለረዳችሁኝ በሙሉ እንዲሁም ለአዲስ አበባ ፖሊስ እና ለየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አመራሮችና አባላት በሙሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ :: ከነበርኩበት ቦታ ለመውጣት የእናንተ ድምፅ መሆን እና የቤተሰቦቼ ጥረት ትልቁን ድርሻ ይወስዳልና ከልብ አመሰግናለሁ ::
ድንገት ለስራ እንደወጡ በዛው የቀሩ የት እንደገቡ ሳይታወቅ ብዙ ጊዜያት ያለፉ ብዙ ዜጎች ይኖራሉና ለኔ ያደረጋችሁትን ትብብር ለነሱም እንድታደርጉ አደራ እላለሁ ::
ምናልባት ዛሬ ላይ እንደቀልድ የሚታዩ ነገሮች ነገ በየቤታችን የሚመጣ ጉዳይ ሊሆን ይችላልና በየትኛውም አጋጣሚ ከቤት ስትወጡ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ አትርሱ ::
አመሰግናለሁ !!
http://addismed.com/study-in-sweden-for-students-cost-eligibility-visa/
03/07/2023
አርቲስት ኢሳም ፍርድቤት ቀረበ
Artist Esam habesha and his wife case Creation organization Sequential Pictures has reported the marking of movie producer Merawi Gerima for business, marked amusement, and music video por...
01/07/2023
ስዊድን ሀገር ለታዳጊ ሀገራት የተዘጋጀውን ስኮላርሺፕ ለማግኝት ወይም በዝቅተኛ በክፍያ ለመማር የሚያስፈልጉ ሙሉ መረጃ ቪዛን ጨምሮ ምንም አይነት ክፍያ ለደላላ ሳይከፍሉ ራስዎ ስቴፑን ተከትለው ማመልከት ይችላሉ ።
መረጃውን ለሌሎችም ሼር በማድረግ ያድርሱ
Study in Sweden for Ethiopian Students: Cost, Eligibility, Visa JobsScholarship Study in Sweden for Ethiopian Students: Cost, Eligibility, Visa By admin - July 1, 2023 Share FacebookTwitterPinterestWhatsApp With its education system ranked amongst the best in the world, Sweden has been referred to as the most sustainable nation across the globe and also the happ...
ሙሉን በዚህ ተመልከቱ👇👇👇
😘https://zena360.info/mobile/watch.php?vid=ab3dbb56f
👉የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/freeapp2023
Click here to claim your Sponsored Listing.