MELA AI
በቅርብ አመታት ውስጥ AI አለምን ይቆጣጠራል።ለዚህ አብዮት ዝግጁ ናችሁ?በዚህ ቻናል ነፃ ስልጠናዎችን አዳዲስ መረጃዎችን ባጠቃላይ ስለ AI ፈልገው የሚያጡት ነገር እይኖርም።
29/07/2025
📖ዕለታዊ ትምህርት📖
ከሰው-ሰራሽ አስተውሎት አሪፍ ውጤት ለማግኘት የሚጠቅሙን 10 ብልህቶች
.....የቀጠለ
👇👇👇👇👇👇
5. የምንፈልገውን ለAI ማሳየት(SHOW THE AI WHAT YOU WANT)
አንዳንድ ምስል የሚያመነጩ ሰው-ሰራሽ አስተውሎቶች የምንፈልገውን ምስል በማጣቀሻነት እንድንጠቀም ምስል የማስገቢያ አማራጭ ይሰጡናል ለምሳሌ ChatGPT ላይ የራሳችሁን ምስል በማስገባትና የሚከተለውን prompt በመስጠት የምታገኙትን አሪፍ ውጤት ተመልከቱ።
Create a high-end black and white portrait using the uploaded photo. The face must remain exactly as in on my original photo — no editing, no retouching, no smoothing. I’m wearing the business suits. Preserve every facial detail and texture for a raw, authentic look. The lighting should be dramatic and studio-quality, using strong contrast and shadows to sculpt the features.
6. AIን እንደምናወጋው ሰው መቁጠር (TREAT IT AS A CONVERSATION)
ልክ እንደ ሰው ረዳት ወይም የስራ ባልደረባ ከAI ጋር መነጋገር መልካም ውጤት ያስገኛል። በምንሰራቸው የዕለት ተለት እንቅስቃሴዎቻችን ከሰው-ሰራሽ አስተውሎት ግብረ መልስ ወይም እርማቶችን ብንወስድ በጣም ጥሩ ነው። ለምሳሌ የስልክ መተግበሪያን እያበለጸግን ነው እንበል፣ ነገር ግን AIዩ የመረጠውን የመተግበሪያ ምስል(icon) አልወደድነውም። እንዲህ ማለት እንችላለን፡
App looks great, but can we change the app icon? Make the owl more cartoony, more friendly, and less lifelike.
ሀሳባችንን ለማጣራት እርዳታ የሚፈልግ ከሆነ Al ጥያቄዎችን እንዲጠይቀን መጠየቅ እንችላለን፣
Feel free to ask me further questions if you're not sure how it should look.
7. ሙሉ እምነት አለማሳደር (DON'T TRUST IT COMPLETELY)
የሰው-ሰራሽ አስተውሎት ትክክለኛነት እየተሻሻለ የመጣ ነው። ግን ከፍፁምነት የራቀ ነው። ወሳኝ ለሆኑ ነገሮች ውጤቱን ማረጋገጣችንን እንዳንረሳ። AI በኦንላይን ላይ መልስ ካገኘ ብዙ ጊዜ በሊንክ የሚቀመጡ ምንጮችን ያቀርባል። ስለዚህ መረጃው ከየት እንደተገኘ ማረጋገጥ እንችላለን (በእርግጥ ዋናው መረጃ ትክክለኛ ለመሆኑን ምንም ዋስትና የለም ፣ ነገር ግን በምንጩ ባለቤት ላይ ፍርድ መስጠት እንችል ይሆናል)። ሒሳባዊ ስሌቶችን በሚያቀርብበት ጊዜ ደግሞ በውጤቱ ላይ እምነት እንዲኖርዎት ትንሽ የውጤት ናሙና ወስደው እራስዎ ለማረጋገጥ ይሞክሩ።
8.ለተሻለ አማራጭ ዞር ዞር ማለት (SHOP AROUND)
በጣም ብዙ የAI አገልግሎቶች አሉ ፣ ብዙዎቹ ለመጠቀም ነፃ ናቸው ፣ እንቁላልዎን በአንድ ቅርጫት ውስጥ ማስገባት አያስፈልግም። ከChatGPT የምትጠብቁትን ውጤት ካላገኙ ፣ ለምሳሌ ፣ ተመሳሳይ ጥያቄን ወደ Google Gemini አስገብተን ውጤቶቹ መሻሻላቸውን መመልከት እንችላለን። በተመሳሳይም የምስል ማመንጫዎች የተለያዩ ጥንካሬዎች እና ድክመቶች አሏቸው. Midjourney በፎቶ-እውነታዊነት (Photo-realism) በጣም ጥሩ ነው ፣ ነገር ግን እንደ ChatGPT በጽሁፍ የተካነ አይደለም። የተወሰነ ዘይቤ (Style) እንዲያመነጭልን ከፈለግን የማጣቀሻ ምስል መስጠት እንችላለን።
9. ለለውጥ መዘጋጀት (BE PREPARED FOR CHANGE)
የሰው-ሰራሽ አስተውሎት መሳሪያዎች በየጊዜው እየዘመኑ ይገኛሉ ፣ እና ያ ደግሞ ውጤታቸውን ይለውጣል። ዛሬ ጥሩ ውጤት ያስገኘ ጥያቄ (prompt) ነገ ተመሳሳይ ጥራት ላያቀርብ ይችላል። በተለይ አንድ AI መሳሪያን ከተጠቀሙ የአቅራቢውን ድረ-ገጽ ይከታተሉ ፣ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ስለተለወጠው ነገር ዝርዝር ዝመናዎችን (Updates) ስለሚያቀርብ ፣ ብዙ ጊዜ በተሳካ ሁኔታ እንዴት እንደሚጠይቁ ጠቃሚ ምክሮችን ይሰጣል።
10. ከሌሎች ልምድ መውሰድ (SEEK INSPIRATION FROM OTHERS)
ብዙ የሰው-ሰራሽ አስተውሎት አገልግሎቶች ፣ በተለይም የምስል እና የቪዲዮ ማመንጨት አገልግሎቶች ፣ በሌሎች ተጠቃሚዎች የተገኙ ውጤቶችን ያሳያሉ። ብዙ ጊዜ ጥያቄዎቻቸውን መቅዳት እና ከዚያ እንደየፍላጎታችን ማስተካከል እንችላለን። በጥያቄዎች(prompts) ላይ ምንም የቅጂ መብት ስለሌለ የሰውን አእምሯዊ ንብረት እየሰረቅኩ ነው ብሎ መጨነቅ አያስፈልግም።
ይቀጥላል....
ፔጃችንን መቀላቀል እንዳይረሱ!
Facebook
Telegram
YouTube
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Address
1000