Aptitude Quiz
Facebook 4 education(ፌስቡክን ለትምህርት)
ገፁን ለሌሎች በማጋራት ግዙፉን የፌስቡክ ት/ቤት ለመመስረት አሻራችን እናሳርፍ !!
12/10/2022
For those taking Ethiopian grade 12 exam, here is one of the link to prepare for aptitude subject. Search by yours for further information.
Good luck.
መልካም ፈተና
Click the link below
Quantitative Aptitude MCQ Questions and Answers - Arithmetic Ability Arithmetic Ability provides you all type of quantitative and competitive aptitude Mcq questions on arithmetic aptitude with easy and logical explanations.
25/04/2022
Science Quiz
መርዛማ ብረትን የሚያስወግዱ ዕፅዋት
ሚያዝያ 17 ቀን 2014 ዓ.ም
በአፈር ውስጥ ያለን መርዛማ ብረት ከአካባቢ ጋር ተስማሚ በሆነ መንገድ የሚያስወገዱ ዕፅዋት መኖራቸው መረጋገጡን ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ ለንባብ አብቅቶታል::
በሲንጋፖር የናንያንግ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ባደረጉት ምርምር በአገሪቱ የሚገኝን በመርዛማ ብረት የተበከለ ለአዝርዕት ልማት የማይውል መሬት ለልማት ማዋል የሚችሉ አገር በቀል ዕፅዋት መኖራቸውን አረጋግጠዋል:: የምርምር ቡድኑ “Phytoremediation” ከአፈር ውስጥ መርዛማነትን የማስወገድ ስልትን ተግባራዊ ማድረጉን አስታውቋል:: በዚህም በአፈር ውስጥ መርዛማነቱ ጐልቶ በሚስተዋልበት ከባቢ አገር በቀል ዕፅዋትን በመትከል ባደረጉት ሙከራ መርዛማ ብረቱን በሥራቸው ሰብስበዉ የመያዝ አቅም ያላቸውን ለይተዋል:: ይህም ብክለቱ በስፋት እንዳይዛመት ማድረግ እንደሚችል ነው ያረጋገጡት።
ሲንጋፖር አነስተኛ የመሬት ስፋት ያላት አገር በመሆኗ የተበከለ መሬትን አፅድቶ እንደገና ለልማት ማዋልን ግድ እንዳላቸው ነው ተመራማሪዎቹ ያስታወቁት:: ለዚህም ተክሎቹን በምርምር አረጋግጠዉ ማግኘታቸዉን ይፋ አድርገዋል::
በናንያንግ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ቡድኑን የመሩት ፕሮፌሰር ላምያንግ በቆዳ ስፋቷ አነስተኛ ለሆነችዉ ሲንጋፖር መሬትን ከእርሻ ወደ ኢንዱስትሪ ወይም ማዕድን ማውጣት ዘርፍ አቀያይሮ መገልገል እንደሚገባ አስምረውበታል:: በመሆኑም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ከፍተኛ ምሁራን ባደረጉት ያላሰለሰ ጥረት ያለሙትን ግብ ማሳካት የሚያስችል ግኝት ላይ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል::
ከአፈር ውስጥ መርዛማነትን ከከባቢ ጋር ተስማሚ በሆነ መልኩ በዕፅዋት ማስወገድ በአነስተኛ ወጪ፣ ዘላቂነት ባለዉ ቀላል መንገድ ተግባራዊ ማድረግ የሚቻል መሆኑንም አስገንዝበዋል።
አዲሱ መርዛማ ብረትን ከአፈር ውስጥ ማስወገጃው ስልት አፈርን ከመሸርሸር የሚታደግ ከባድ መርዛማ ብረትን ከመከማቸት እና መሰራጨት የሚከላከል ነው ተብሎለታል:: በሲንጋፖር በምርምሩ ከተተኮረባቸዉ 46 የዕፅዋት ዝርያ 12ቱ መርዛማ ብረትን ለማስወገድ የሚያስችሉ መሆናቸውም ተገልጿል።
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር ሚያዝያ 17 ቀን 2014 ዓ.ም ዕትም
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ
በhttp://www.amharaweb.com/Bekur ላይ ማግኘት ይችላሉ።
24/03/2022
✳️ ዶክተር ኢንጂነር ቅጣው እጅጉ ማን ናቸው?
◽️ ዶክተር ኢንጂነር ቅጣው እጅጉ የካቲት 25 ቀን 1948 (እ.ኤ.አ) ከአባታቸው ከአቶ እጅጉ ሃይሌ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አስካለ በላይነህ በከፋ ጠቅላይ ግዛት በቦንጋ ከተማ ተወለዱ።
◽️ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቦንጋ፣ በዋከና በጅማ ከተማ ካጠናቀቁ በኋላ በባህር ዳር በሚገኘው ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የከፍተኛ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል። ዶክተር ቅጣው ወደ ጃፓን አገር በመሄድ በኦሳካ ዪኒቨርስቲ በቋንቋና የጃፓን ኢኮኖሚ ፣በሄሮሺማ ዩንቨርስቲ የኢንደስትሪ እና የአውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ አጥንተው ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።
◽️ በኋላም አሜሪካን ሀገር ስኮላር ሺፕ አግኝተው በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን ማስትሬታቸውን በመጨረሻም ለትምህርት ባላቸው ከፍተኛ ፍላጎት በኤሮ-ስፔስ ምህንድስና ዶክትሬታቸውን ተቀብለዋል። በልጅነታቸውም የድቁና ትምህርትን ቀስመዋል፡፡
◽️ ዶክተር ቅጣው በናሳ (NASA) በሲስተም መሃንዲስነትና
በጠፈር ሳይንቲስትነት የሰሩ ሲሆን ከሌሎች መሃንዲሶችና ሳይንትስቶች ጋር በመተባበር ለእኛ አለም (Planet Earth) እና ለተቀሩት ፕላኔቶች የምርምር ሳይንስ (Planetary Science Research and Exploration) የሚረዱ የጠፈር መንኮራኩሮችና
ሮኬቶች ፈጥረዋል።
◽️ ዶክተር ቅጣው በዚህ ከፈጣሪ በተቸሩት ታላቅ ችሎታና እውቅት ለዚህች ለምንኖርባት ዓለምና ሕዝብ ታላቅ አስተዋፅዎ አበርክትዋል።
🔺 ከነዚህም ጥቂቱን ለመጥቀስ
◽️ ለናሳ(NASA) ሁለት የኤሮ- ስፔስ መወርወሪያ ሜካኒዝም
◽️ ለቦይንግ ኩባንያ ሲሙሌተር (Flight Dynamic Simulator) እና አድቫንስድ ወይንም ኔክስት ጀነሬሽን (Advance or Next Generation) በመባል የሚታወቁትን ግሎባል ፖዚሽን ሳተላይት ሲስተም (Global Positioning Satellite System) ከፈለሰፉት ውስጥ አንደኛው ሰው እሳቸው ነበሩ። ዶክተር ቅጣው Trans Tech International በመባል የሚታወቀውን ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ድርጅት በመመስረት የተለያዩ ሀገሮች የቴክኖሎጂ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ በአማካሪነት አገልግለዋል።
◽️ በተለየም ዴርቶጋዳ በተሰኘው መጽሐፍ ሻጊዝ የተባለውን ገጸ ባህሪ የተላበሰው ቅጣው ከመጻፉ ብኻላ ብዙም ለምሁራን ትኩረት በማይሰጠው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ የበለጠ እንዲታወቅ እና መነጋገሪያ እንዲሆን አስችሎታል። በተለይም አሟሟቱ በመጽሀፉ የተለየ መላምንት መሰጠቱ አወዛጋቢነቱን አሳድጎታል።
◽️ ለውድ ሀገሩ ፍቅር የነበረው ቅጣው በሞያው ለማገዝ ያላሰለሰ ጥረት ቢያረግም የተማረ ሰው አብሾ ባለበት የመንግስት ስርአት ውስጥ ትግሉ ሊሳካለት አልቻለም። አለም ሁሉ ቅጣውን የግሉ ለማድረግ ሲሯሯጡ የኛዎቹ ግን አይንህን ላፈር ብለውት ነበር።
◽️ በኛ ሀገር ጠቢብ መሆን የ አብሪ ትል መሆን ማለት ነው። አብሪ ትል የፈለገ ብርሃን ቢኖራት ሰዎችን በማታ መንገድ ከመጠቆም ያለፈ አይደለም። ሰዎቹም ብርሃኗን ከተጠቀሙ በኻላ ጨፍልቀው ይገሏታል። የገዛ ብርሃኗ ለሞት ይዳርጋታል።
◽️ በዚህም ተስፋ ያልቆረጠው ቅጣው የፖለቲካ ድርጅት መስርቶ ለውጥ ለማምጣት እና ሀገራችንን ከበለጸጉት ተርታ ለማሰለፍ ጥረት አድርጓል።
◽️ ዶክተር ቅጣው ከባለቤታቸው ከወ/ሮ ስቴላ እጅጉ ጋር በመልካምና በደስታ ጋብቻ ተጣምረው የኖሩ ሲሆን ቢንያም ፣ ያሬድ እና አቢጋኤል የተባሉ የሁለት ወንዶችና የአንድ ሴት አባት ነበሩ። ዶክተር ቅጣው እጅጉ ወደ ኦስትን ቴክሳስ ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ መጥተው ድንገት በደርሰባቸው ሕመም ምክንያት በጥር 13 ቀን 2006 (እ.ኤ.አ) በ58 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
◽️ ዶክተር ቅጣው እጅጉ በመልካም ባህሪያቸው የተወደዱ፣
በትህትናቸው የተመሰገኑ፣ በስራቸው የተደነቁ፣ በራዕያቸው ብዙ ተከታዮችን ያፈሩ፣ የብዙዎች ተስፋና አርዓያ እንዲሁም የሀገር ኩራት የሆኑ ታላቅ ሰው ነበሩ።
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅ #ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology
23/01/2022
የሚያስመሰግን ተግባር ነዉና በፊልሙ ምርቃት በመገኘት የትምህርቱን ኢንዱስትሪ እናበረታታ።
የ "አጨብጭቡለት" ፊልም የምርቃት ገቢ ሙሉ ለሙሉ በጦርነቱ ለወደሙ ትምህርት ቤቶች መልሶ ማቋቋሚያ እንደሚውል አዘጋጆቹ ይፋ አደረጉ።
===================
ፊልሙ ጥር 16 ከቀቱ 11:00 ሰዓት በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል ይመረቃል ተብሏል።
የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር አቶ ወንዶሰን ሞላ መቼቱን ደሴ ከተማ ያደረገው ፊልሙ በምረቃው እለት የሚገኘው ገቢ ሙሉ ለሙሉ በደሴ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰበትን ትምህርት ቤት መልሶ ለማቋቋም ይውላል ብለዋል።
ከጦርነቱ በፊት ለፊልሙ ስኬት የደሴ ህዝብ ቤቱን፣ ሆቴሉንና ትምህርት ቤቶችን በመስጠት ተባብሮናል ያሉት አቶ ወንዶሶን፣ ይህንን ውለታውን በትንሹ ለመመለስ የምርቃቱን ገቢ ሙሉ ለሙሉ ለመለሶ ግንባታ ለማዋል ወስነናል ብለዋል።
የመግቢያ ዋጋ 3ሺ ብር ሲሆን ህዝቡ እየተዝናና ለትምህርት ቤት ግንባታ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
የትምህርት ሚኒስቴርም አዘጋጆቹን እያመሰገነ ሌሎችም ይህንን አርዕያ በመከተል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ ይጠይቃል።
Click here to claim your Sponsored Listing.