Visions
This page Committed to realize Ethiopia's Prosperity.
08/04/2026
አዎ! ይገባናል ። ወንጀለኞች አይደለንም ! ይበቃል ! የባህረ በር 140 ሚሊየን ህዝብ ያለ እስትንፋስ ዘግይቶ መቆየት የለም 🙅♀️🙅♀️🙅♀️🙅♀️🙅♀️🙅♀️🙅♀️
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ህጋዊና ተገቢ ነው ሲሉ የአውሮፓ የፓርላማ አባል ገለጹ
++++++++++++++++++++
| ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት እያደረገች ያለው ጥረት ሕጋዊ፣ ተገቢና በዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች የተደገፈ መሆኑን የአውሮፓ ፓርላማ አባል እና የቀድሞ የፈረንሳይ ትራንስፖርት ሚኒስትር ቲየሪ ማሪያኒ አስታወቁ።
ፈረንሳዊው የአውሮፓ ፓርላማ አባል ቲየሪ ማሪያኒ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፤ ለአንድ ሀገር የባሕር በር መዳረሻ አለመኖር ትልቅ ተግዳሮት ነው።
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት እና በፍጥነት እያደገ ያለ ኢኮኖሚ ያላት ሀገር መሆኗን ጠቅሰው፤ ይህን ተግዳሮት ለመፍታትና የባሕር በር ለማግኘት እያደረገችው ያለው ጥረት ሕጋዊ እና ተገቢ መሆኑን አንስተዋል።
እንደ ፓርላማ አባሉ ገለጻ፤ እንደ ኢትዮጵያ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት የባሕር በር የማግኘት መብት አላቸው።
ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ እና እንግዳ በሆነ መልኩ ወደብ አልባ ሀገር መሆኗን ያነሱት ቲየሪ ማሪያኒ፤ ይሁን እንጂ የባሕር በሩን ለማግኘት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ሊደረግ እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል።
በፀጋዬ ጥላሁን
++++++++++++++++++++
#ኢትዮጵያ #ዲፕሎማሲ