Hanan Taha
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hanan Taha, Women's clothes shop, Addis Ababa.
ቁርአን ላይ ከተቀመጡ ታሪኮች ውስጥ ከሚገርሙኝ....የነብዩላህ ሙሳ love life!❤
ነብዩላህ ሙሳ, The big guy, the strong fit man፣ አንበሳው ከሀገራቸው አምባገነኑ የፊርአውንን መንግስት ሸሽተው ተሰደው ሲጓዙ መድየን ወደምትባል ቀበሌ ደረሱ። የቀበሌው ሰው ታዲያ መድየን ውስጥ ባለችዋ ብቸኛ የዉሀ ምንጭ እየተጋፋ ግመሉንና ፍየሉን ያጠጣል። ጉልበተኛ እዛ ነው የሚታየው በቃ። ያለችው ምንጭ አንድ ነች እዛ ተጋፍቶ የሚያጠጣውና ለራሱም የሚቀዳው አለ የተባለ ጠንካራ ወንድ ነው። የከተማው ወንድ ታዲያ ትግል የሚገጥመው እዛ ነው። ሁሉም ታግሎ ያጠጣል ይጠጣል። ከዛ ደካሞቹ ደግሞ ጉልበተኞቹ ታግለው አጠጥተው እስኪጨርሱ ዳር ላይ ተኮራምተው ይጠብቁና መጨረሻላይ በትግሉና በፍትጊያው የደፈረሰውን ውሀ እንስሳቶቻቸውንም ያጠጣሉ እነሱም ይጠጣሉ። ለቤታቸውም የደፈረሰውን ውሀ ይቀዳሉ። ታዲያ ምን ያርጉ💁
ነብዩላህ ሙሳ በስደት በረሀውን ተጉዘው መድየን ምንጭ ውሀ ሲደርሱ ሰዉ ይራኮታል። የጦፈ ትግል ነው ያለው። በዚ መሀል አሻግረው ሲያዩ ሁለት ሚስኪን ልጃገረዶች ጥግ ላይ ቆመው እንስሳቶቻቸውን ሰብሰብ አርገው ይጠብቃሉ። ሙሳ(አሰ) ሁኔታቸው ግራ ገባቸውና ተጠግተው ምነው እንስሳቶቻችሁን አታጠጡምን? ሲሉ ጠየቋቸው። እነሱም ምን እናርግ ብለህ ነው አቅም የለንም እዚ ተጋፍቶ ማጠጣት። አባታችንም ሽማግሌ ነው አቅም የለውም። ስለዚህ ጠብቀን ጉልቤዎቹ ሲጨርሱ እንጂ ማጠጣት አንችልም ሲሉ መለሱ። ሙሳም ነው እንዴ አሉና የልጆቹን ፍየሎች ይዘው ወደምንጩ በመሄድ ምንጩ ላይ ያለን ጉልቤ ሁሉ አተራመሱት። ለጉልቤም ጉልቤ አለው አሉ እትዬ ዙልፋ። ማን ይግፋቸው ሙሳን። እያንዳንዱን አሽቀንጥረው ጥለው የሴቶቹን ፍየሎች አጠጥተው ለራሳቸውም ጠጥተው ጉልቤውን ሁሉ ልክ አስገብተው ተመለሱና ፍየሎቹን ለሴቶቹ ሰተው ሂዱ በሉ ብለው እሳቸው ያው ስደተኛና ሙሳፊር ናቸውና መንገዳቸውን እስኪቀጥሉ ትንሽ ልረፍ ብለው ዛፍ ስር ቁጭ አሉ። ያላገቡ ላጤ የነበሩትና ስራም ቤትም መሄጂያም ማረፊያም ያልነበራቸው ስደተኛውና ሙሳፊሩ ነብዩላህ ሙሳ ዛፏ ስር ቁጭ ብለው َربِّ إِنِّي لِمَا أَنزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ" " ጌታዬ ሆይ እኔ አንተ ወደኔ ላወረድከው በጎ ነገር ከጃይ ነኝ" ሲሉ ዱአእ አደረጉ። እቺ ዱአእ ስንት ነገር መለሰች?እናየዋለን.... ግን እዚጋ ጀለሴ ለካ ከሴቶቹ አንደኛዋ እዛው wow ብላለች..ሁብ ጠብ አርጓታል። ሙሳ (አሰ) መች አወቁና
ሴቶቹ ቤታቸው እንደደረሱ በጊዜ መመለሳቸው ግራ የገባቸው አባታቸው ምነው ዛሬ ሲሉ ጠየቁ። ሴቶቹም ያጋጠማቸውን ይነግሯቸዋል። አባታቸውም ስማቸው ነብዩላህ ሹአይብ(አሰ) ይባላሉ። ደስ አላቸው ከዛም ጠርተው ሊያመሰግኑት እሺ ካለ ደግሞ ለሰራው ስራ ሊከፍሉት እንድትጠራው ከሁለቱ ልጆች መሀል ልቧ ጠብ ያለውን ልጅ ላኳት። እሳቸውም መች አወቁና። እየሮጠች ሄደች። ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ አገኘችው። አይኗን ሰበር አርጋ አባቷ እንደሚፈልጉት ነገረቻቸው። ሙሳም (አሰ) ጥሪ ማክበር ዋጂብ ነውና እሺ አሉ። እሳቸው ከፊት እሷ ከሗላ ሆነው መንገዱን እሳቸው አያውቁትምና መታጠፍ ሲኖርባቸው በድምፅ ሳይሆን መታጠፍ ወዳለባቸው አቅጣጫ ጠጠር እየወረወረች እየመራቻቸው ከፊትና ተጠባብቀው አባቷ ቤት ገቡ። ልጅቷ በሰውዬው አላህን መፍራት፣ ታማኝነት አይናፋርነትና ጀንትልነት ይባስ ማረካት። አባትየውም ተቀበሉት። አመሰገኑት። ከየት ነህ አሉት። ታሪኩን ሙሉ ነገራቸው። አላህ አትርፎሀል አይዞህ ሲሉ አፅናኑት። ሙሳም መቼስ መንገደኛ ነውና ዛሬን አድሮ ነገ ወደማያውቀው መንገድ መጓዙ አይ
23/04/2026
#ሰበር መረጃ፦ጉደኛዋ ኢራን ጉድ አፈላች!
#ኢራን የተናገረችውን አደረገችው!
#ኢራን ለክፉ ቀን ብላ ካስቀመጠቻቸውና አለም ካላያቸው መሳሪያዎቿ መካከል አንዱን ብቻ ወደ ሆርሙዝ አቅጣጫ ተኩሳ አለምን ጉድ አሰኝታለች፣አሜሪካን እና እስራኤልን ደግሞ በድንጋጤ አመዳቸው ቡን አንዲል አድርጋለች።
ይቺ ለጉድ የፈጠራት የአሜሪካና የእስራኤል የጎን ውጋትና የሆድ ቁርጠት የሆነች ሀገር ለካ የምትፎክረውና የአለም አለቃ ለሆነችው አሜሪካ ጭምር አልታዘዝም ያለችው በፈጣሪዋና በመሳሪያዎቿ ተማምና ነው።
ኢራን አዲስ ይፋ ያደረገችውና ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ ያስወነጨፈችው አዲሱ የጦር መሳሪያ "የመሳሪዎች ንጉስ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ሲተኮስ ከአፈሙዙ ሲወጣ አኖድ ሆኖ ይወጣና ዐየር ላይ ተጉዞ ኢላማው ጋር ሲደርስ እዛው ዐየር ላይ በመፈንዳት በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ፈንጂዎችን ወደ ሰማይ በመልቀቅና በመንጋ ወደሚፈለገው ኢላማ ሄደው እንዲፈነዱ የሚያደርግ ነው።
በእርግጥም ኢራን የሰላም ድርድሩ ካልተሳካና አሜሪካ ዳግም ኢራን ላይ ወረራ ከፈፀመች ምላሹ የከፋ ይሆናል።አለም አይቷቸው የማያውቃቸውን መሳሪያዎች ይፋ አደሮጋለሁ ስትል የነበረው ዛቻ እውነት መሆኑን የዚህ አዲስና አደገኛ መሳሪያ ይፋ መሆን ጥሩ ማስረጃ ነው።
ኢራን አሁንም ገና ያልተነኩና ያልታዩ አዳዲስ መሳሪያዎች አሉኝ።ኢራን በምንም አይነት መመዘኛ በአሜሪካና በእስራኤል አትሸነፍም።ነፃነቷንና ሉኣላዊነቷን አስከብራ ትኖራለች ሲሉም የሀገሪቱ ባለ ስልጣናት ጠንከር ያለ አቋማቸውን ገልጸዋል።
የተኩስ አቁሙ ስምምነት ሊጠናቀቅ ጥቂት ሰዓታት በቀሩት በዚህ ወቅት ኢራን ይህንን አዲስና አውዳሚ መሳሪያ ይፋ ማድረጓ የቀጠናውን ውጥረት ወደ አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሮታል።
ምርጫውን ከሚያሸንፈው ፓርቲ ይልቅ ፕሪሚየም ሊጉን የሚያሸንፈው ቡድን የሚያሳስበው ትውልድ😑
23/04/2026
🇧🇳 🕌 ብሩናይ ዳሩሰላም ደሃ የማይኖርባት የሀብታሞች መዲና ያሙስሊሙ አለም ኩራት ማወቅ ያለባችሁ ድንቅ እውነታዎች!
በአለም ላይ ብዙ ባለፀጋ ሀገራት ቢኖሩም፣ እንደ
ብሩናይ (Brunei)ያለ ሀብትን ከሰላም፣ ስልጣኔን ከስነ-ምግባር ጋር አዋህዶ የያዘ ሀገር ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው። ስለዚች ድንቅ ሀገር ማወቅ ያለባችሁ አስገራሚ እውነታዎች እነሆ፦
👑 1. በወርቅ የተለበጠው የንጉሱ ህይወት
የብሩናይ ሱልጣን ሀሰናል ቦልኪያ ከአለማችን ባለጸጋ መሪዎች አንዱ ናቸው። ህይወታቸው ልክ እንደ ተረት ነው፦
7,000 ውድ መኪኖች፦ንጉሱ 500 ሮልስ ሮይስን ጨምሮ በአጠቃላይ ሰባት ሺህ የሚጠጉ ዘመናዊ መኪኖች አሏቸው።
በወርቅ የተለበጠ አውሮፕላን፦የግል ቦይንግ አውሮፕላናቸው ውስጥ ያሉት የቧንቧ እቃዎችና መገልገያዎች በሙሉ ከንፁህ ወርቅ የተሰሩ ናቸው።
ትልቁ ቤተመንግስት፦መኖሪያቸው ከ1,700 በላይ ክፍሎች ያሉት ሲሆን፣ በአለም ላይ ትልቁ የግል መኖሪያ ተብሎ ይመዘገባል።
💰 2. የዜጎች "ነፃ" ህይወት
በብሩናይ ውስጥ መንግስት ለዜጎቹ የሚያደርገው እንክብካቤ ከመቃብር በፊት ያለ ገነት ያስመስለዋል፦
ግብር የለም (Tax-Free)፦በብሩናይ የገቢ ግብር የሚባል ነገር የለም። የሰሩት ጥሬ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለቤት ነው!
ነፃ ህክምና እና ትምህርት፦** ዜጎች በነፃ ይታከማሉ፣ በነፃ ይማራሉ። በሀገር ውስጥ የማይታከም በሽታ ካጋጠመ መንግስት በራሱ ወጪ ወደ ውጭ ሀገር ልኮ ያሳክማል።
ነዳጅ ከውሃ ይረክሳል፦ሀገሪቱ ከፍተኛ የነዳጅ ሀብት ስላላት ነዳጅ እጅግ በጣም ርካሽ ነው። በዚህም ምክንያት እያንዳንዱ ዜጋ 2 እና 3 መኪና አለው።
🕊️ 3. ፍጹም ሰላም እና ወንጀል አልባነት
ዜሮ ወንጀል፦ብሩናይ በአለም ላይ ወንጀል በሌለበት ሁኔታ ቀዳሚ ናት። ሰዎች መኪናቸውን ሞተር ሳያጠፉ ወይም ቤታቸውን ሳይቆልፉ መሄድ ይችላሉ።
አልኮልና ሱሰኝነት የለም፦ሀገሪቱ በሸሪዓ ህግ የምትመራ በመሆኗ አልኮልና አደንዛዥ እፅ ክልክል ናቸው። ይህም ማህበረሰቡን እጅግ ረጋ ያለና ጨዋ አድርጎታል።
🕌 4. የወርቅ መስጊዶች መገኛ**
ብሩናይ በአለማችን በሚያማምሩና ጉልላታቸው (Domes) በንፁህ ወርቅ በተለበጡ መስጊዶቿ ትታወቃለች። እነዚህ መስጊዶች የእስልምና ጥበብ እና የሀገሪቱ የብልጽግና መገለጫዎች ናቸው።
🌳 5. ተፈጥሮና ቴክኖሎጂ
ብሩናይ በቴክኖሎጂ የረቀቀች ብትሆንም፣ 70% የሚሆነው መሬቷ አሁንም በድንግል ደን የተሸፈነ ነው። አየሯ ንጹህ፣ ከተማዋ ውብና ጸጥታ የሰፈነባት ናት።
💡 ጥያቄ ለእናንተ (ተሳተፉበት):
ከላይ ከተጠቀሱት የብሩናይ ድንቅ ነገሮች ውስጥ ለእኛ ሀገር ቢለመድ"ብላችሁ ይበልጥ የምትመኙት የትኛውን ነው?
1. የግብር አለመኖሩንና የነዳጅ መርከሱን?
2. ነፃ ህክምናና ትምህርቱን?
3. ወይንስ ወንጀል የሌለበትን ፍጹም ሰላሙን?
ሃሳባችሁን በኮሜንት አጋሩኝ! 👇
✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️
Hassen Ahmed. Follow my page
23/04/2026
የኡመር ኢቢኑል ከጣብ (ረ.ዐ) የጀግንነት ታሪክ፡ የፍትህና የቁርጠኝነት ጥግየኡመር ኢቢኑል ከጣብ ታሪክ የሰው ልጅ ማንነት እንዴት በእምነትና በጽናት ሊቀየር እንደሚችል የሚያሳይ ታላቅ ማሳያ ነው።
ኡመር በታሪክ "አል-ፋሩቅ" (እውነትን ከሀሰት የሚለይ) በሚል መጠሪያቸው ይታወቃሉ። የእሳቸው የጀግንነት
ታሪክ ከመለወጣቸው በፊት ጀምሮ እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ በጀግንነትና በቁርጠኝነት የተሞላ ነው።
1. ከመለወጣቸው በፊት የነበረው ግርማ ሞገስ
ኡመር ኢቢኑል ከጣብ ገና እስልምናን ከመቀበላቸው በፊት በቁረይሾች ዘንድ እጅግ የሚፈሩና የሚከበሩ ሰው ነበሩ።ቁመታቸው ረጅም፣ ድምፃቸው ነጎድጓድ፣ እና ጥንካሬያቸው ወደር የማይገኝለት ነበር። በወቅቱ እስልምናን ለማጥፋትከነበሩት ቀዳሚ ጠላቶች አንዱ ነበሩ። ሆኖም ግን፣ ያ የነበረው የልብ ጥንካሬ ወደ እስልምና ሲዞር ለዲኑ ትልቅ ጋሻ ሆነ።
2. ታሪካዊው ለውጥ፡ ከጠላትነት ወደ ታላቅነት
የኡመር ወደ እስልምና መግባት ለሙስሊሞች ትልቅ የድል ቀን ነበር። ታሪኩ እጅግ አስገራሚ ነው፡- ኡመር ነቢዩን(ሰ.ዐ.ወ) ለመግደል ሰይፋቸውን መዝዘው ሲወጡ፣ እህታቸው ፋጢማና ባለቤቷ እስልምናን መቀበላቸውን ይሰማሉ።በቁጣ ተሞልተው ወደ እህታቸው ቤት ሲያመሩ፣ እህታቸው የቁርአን አንቀጾችን (ሱረቱ ጣሀ) ስታነብ አገኟት። ያየቁርአን ቃል የኡመርን የድንጋይ ልብ አቀለጠው። ወዲያውኑ ወደ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ በመሄድ እስልምናቸውን አወጁ።"ከዛሬ ጀምሮ አላህ በግልጽ ይመለካል!" — ኡመር ኢቢኑል ከጣብ
3. የጀግንነት ጥግ፡ ስደት (ሂጅራ) ወደ መዲና
አብዛኞቹ ሙስሊሞች ከመካ ወደ መዲና ሲሰደዱ በድብቅና በሌሊት ነበር። ኡመር ግን እንዲህ አላደረጉም። ሰይፋቸውን ታጥቀው፣ ቀስታቸውን ይዘው ወደ ካዕባ ሄዱ። በዙሪያው የነበሩትን የቁረይሽ መሪዎች እንዲህ ሲሉ ተገዳደሩ፡-"እኔ ወደ መዲና ልሰደድ ነው፤ እናቱ ልጇን እንድታጣ፣ ሚስቱ መበለት እንድትሆን፣ ልጆቹም የቲም እንዲሆኑየሚፈልግ ካለ በዚህ ተራራ ጀርባ ይገናኘኝ!"ይህንን ድፍረት የተሞላበት ንግግር ተከትሎ አንድም ሰው ሊገጥማቸው የደፈረ አልነበረም። ይህ የጀግንነት ጥግ ነበር።
4. የፍትህና የጀግንነት መሪ (አል-ፋሩቅ) ኡመር ሁለተኛው የሙስሊሞች መሪ (ኸሊፋ) በነበሩበት ወቅት፣ ግዛታቸው ከፋርስ እስከ ሮም ተዘርግቶ ነበር። ሆኖምግን፣ እሳቸው በምድር ላይ ካሉት እጅግ ሀያል መሪዎች አንዱ ቢሆኑም፣ በፍትህና በትህትናቸው ይታወቃሉ።
የኡመር ኢቢኑል ከጣብ ቁልፍ ባህሪያት መገለጫዎች
ፍትህበድሃና በሀብታም፣ በዘመድና በባዕድ መካከል ፍጹም እኩልነትን ማስፈን።ትህትና የዓለም መሪ ሆነው ሳለ፣ ዱቄት በጀርባቸው ተሸክመው ለድሆች ያከፋፍሉ ነበር። ድፍረት በጦር ሜዳም ሆነ በፖለቲካ ውሳኔዎች ላይ ለማንም ፍጡር አለመንበርከክ።አርቆ አሳቢነት የመንግስት መዋቅሮችን፣ የፖሊስ ሰራዊትንና የግብር ስርዓትን መዘርጋት።
5. የመጨረሻው የጀግንነት መስዋዕትነት
ኡመር ኢቢኑል ከጣብ የሞቱትም በጀግንነት ተግባር ላይ እያሉ ነው። የንጋትን ሶላት እየመሩ ሳለ፣ በክህደት ተወጉ።በቆሰሉበት ወቅት እንኳን ጭንቀታቸው ስለ ራሳቸው ሳይሆን ስለ ሙስሊሞች አንድነት ነበር። እሳቸው የሞቱት ለፍትህና ለእውነት በቆሙበት መስክ ላይ ነው።
ማጠቃለያ
የኡመር ኢቢኑል ከጣብ ታሪክ የጀግንነት ጥግ ብቻ ሳይሆን፣ የፍትህ፣ የርህራሄና የጽናት ተምሳሌት ነው። እሳቸው "ፍትህ ካለ ሰላም አለ" የሚለውን መርህ በተግባር ያሳዩ ታላቅ መሪ ነበሩ። ዛሬም ድረስ ስማቸው ሲነሳ የጀግንነትና የፍትህ ተምሳሌት ሆኖ ይኖራል።
ማሜ ሚዲያ ኔትወርክ
23/04/2026
የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ፍላጎት እንደምግብ .... መሠረታዊ ጥያቄ ነው:: ይሄ አልተሟላም ማለት አንድ ሴት የእለት ተለት ተግባሯን ማከናወን አትችልም:: በስነልቦናና በጤና በማህበራዊ እንቅስቃሴ ሚያመጣውን ተፅኖ ማያውቅ ያለ አይመስለኝም :: ጥቅሙንም መዘርዘር አስፈላጊ አይደለም የታወቀ ስለሆነ::
ባይሆን የተዘነጋውን ስናነሣ የዋጋው መናር የጥራቱ መውረድ እጅግ አሣሣቢ ሆኗል:: ሁሉም ማህበረሠብ ገዝቶ ለመጠቀም ሚቻልበት ሁኔታ አይደለም::
ለዚህ ደግሞ ሚመለከተው አካል እንዲመለከተው መፍትሄ እንዲሠጠን እንጠይቃለን 🙏
23/04/2026
🚨 የአክሱም ሰማይ ስር የታነቀው ፍትህ፦ ከህገ-መንግስት በላይ የነገሰው አምባገነንነት! 🚨
⚖️ "ፍትህ ለታረዱት እውነቶች... ድምፅ ለተከለከሉት ወገኖች!"
🌑 የታሪክ ጥቁር ጠባሳ፦ የአክሱም "የዝግ" ስብሰባና አፋኝ ውሳኔዎች
✅ሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ.ል በአክሱም ከተማ ታሪክ የማይረሳው የጭቆና ምዕራፍ ተጽፏል። በነቡረ-እድ ጎደፋ መርሃ የተመራውና በመንግስት የጸጥታ አካላት የታጀበው ስብሰባ፣ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከሰብአዊ ፍጡርነት ተራ አውርዶ እንደ ባዕድ የሚቆጥር ውሳኔ አሳልፏል።
📍 ከአፋኝ ውሳኔዎቹ መካከል፦
✅የእምነት ነፃነት መገፈፍ፦ በትምህርት ቤቶች ሂጃብ መልበስ በይፋ ታግዷል።
የመንፈስ ስንቅ መከልከል፦ የጁምዓ ሶላት በ"ሹቅ መስጊድ" እንዳይሰገድና በኪራይ ቤት ያሉ መስጊዶች በሙሉ እንዲዘጉ ታዟል።
✨ድምፅን ማጥፋት፦ የአዛን ጥሪ በድምጽ ማጉያ መጠቀም ፍጹም ተከልክሏል።
የሙታን ክብር መርገጥ፦ አስክሬን ይዞ በአስፋልት መንገድ መጓዝ ተከልክሎ በጫካና በአማራጭ መንገዶች እንዲዞሩ ተፈርዶባቸዋል።
💡 "ግፍ ድቅድቅ ጨለማ ነው!" — ይላሉ አባቶቻችን?
"በአለም ላይ ትልቁ አምባገነንነት እውነትን በጉልበት ለመቅበር መሞከር ነው። ነገር ግን እውነት እንደ ዘር ናት፤ በተቀበረች ቁጥር በቀለች ትወጣለች።"
✨የኡመሩል ፋሩቅ (ረ.ዐ) ቃል ዛሬም ያስተጋባል፦ "እናቶቻቸው በነፃነት የወለዷቸውን ሰዎች መቼ ነው ባሪያ ያደረጋችኋቸው?" ⚖️🛡️
❓ በእኔ እምነት እንገብጋቢ ጥያቄዎችና ትዝብቶች አሉኝ (ለአሁኑ ሙስሊም ትውልድ)
✨የአንድነት ጥያቄ፦ ወንድሞቻችን በአክሱም "አትስገዱ፣ አትለብሱ" ሲባሉ እኛ በየከተማው የምንገኝ ሙስሊሞች ህመማቸው እንደ ህመማችን እየተሰማን ነው ወይስ በቁጥር መብዛታችን ብቻ ነው የሚያስመካን?
✨የመብት ጥያቄ፦ ህገ-መንግስቱ የእምነት ነፃነትን ቢፈቅድም፣ በአክሱም ግን ህጉ "የነቡረ-እድ ትእዛዝ" ሆኗል። ለምንድነው ህግ በአንድ አካባቢ ብቻ ደንብ ሆኖ ሌላ ቦታ የሚጣሰው?
✨የትዕግስት ጥያቄ፦ ትዕግስት ማለት በደልን አሜን ብሎ መቀበል ነው ወይስ በሰላማዊ መንገድ መብትን ለማስከበር ጽናት ማሳየት?
✨የነገው እጣ ፋንታ፦ ዛሬ አክሱም ላይ ሂጃብና አዛን ከተከለከለ፣ ይህ እሳት ነገ ወደ ሌላው ከተማ እንደማይዛመት ምን ዋስትና አለን?
🛡️ እንደ እኔ እምነት፦ እስላማዊ እይታና መፍትሄወች ብየ የማምነው?
እነዚህን አራት ጥያቄዎች በኢስላማዊ መነጽር እንዲህ እመለከታቸዋለሁ፦
✨መፍትሄ 1 (አንድነት)፦ ረሱል (ﷺ) እንዳሉት ሙስሊሞች እንደ አንድ አካል ናቸው።
✅የአክሱም ህመም የሁላችንም ህመም ካልሆነ ኢማናችን ጎድሏል። መፍትሄው በዱዓ፣ በድምፅና በዲፕሎማሲያዊ ጫና አንድነታችንን በተግባር ማሳየት ነው።
✨መፍትሄ 2 (ፍትህ)፦ ኢስላም በግፍ ፊት ዝምታን አይመርጥም። "ከጀሀድ ሁሉ በላጩ በአምባገነን መሪ ፊት እውነትን መናገር ነው" እንደሚለው ሀዲስ፣ ሙስሊሙ ማህበረሰብ መብቱን በህጋዊ መንገድ የመጠየቅ ሞራል ሊኖረው ይገባል።
✨መፍትሄ 3 (ፅናት)፦ ትዕግስት (ሶብር) ማለት በሀቅ ላይ መጽናት እንጂ ለባጥል እጅ መስጠት አይደለም። የአክሱም ሙስሊሞች በሰላማዊ መንገድ "አንፈርምም" ማለታቸው ትልቅ የጀግንነት ተግባር ነው።
✨መፍትሄ 4 (ንቃት)፦ ኡማው በንቃት መቆም አለበት። "ከአንድ ጉድጓድ ሁለት ጊዜ አይነደፉም" እንደሚባለው፣ ታሪካዊ ጠላቶች ዛሬም በሃይማኖት ካባ ተሸፍነው እምነታችንን ለማጥፋት ሲነሱ በተደራጀ መንገድና በእውቀት ልንመክታቸው ይገባል።
🤲 የኔ ዱዓና ተማፅኖ
✅ያ አላህ! የአክሱም ሙስሊሞችን ከዚህ አፈናና ማ
21/04/2026
#ይህ ልጅ ከመቀሌ አዲስ አበባ ገብቷል ስባል ሰማው የኔ ትንሽዬ ወንድም ከአዶናይ ውጪ ማንንም ሰው እንዳታገኝ ከአዶናይ ውጪ በንፁህ ልብ የሚረዳህ የለም የማንም መጠቀሚያ እንዳትሆን ፈጣሪ ይጠብቅህ ትችላለህ 💪❤
Adonay Berhane Hailemichael 👈❤😳...አዶናይ ከእራሱ በላይ ለሌላ ሰው የሚያስብ የሌላው ሰው ስኬት የሚያስደስተው ለሌላ ሰው የሚተርፍ ልቡ ቅን የሆነ ሰው ነው የደግነት ባለቤት አደራህን ከእሱ ውጪ ማንንም እንዳታገኝ ሌላው መጠቀሚያ ያደርጉአል ሊጎዱክም ይችላሉ ከእግዚአብሔር ጥበቃ ጋር መጠቀቁ አይከፋም ...!!
#በእኔ ሀሳብ አስተያየት የሚትስማሙ ላይክ ሼር እያደረጋቹ አድርሱ ሀሳባቹንም አስቀምጡ 😳❤✏....... !!
20/04/2026
መሞታቸዉ እንጂ መቀበሩ ያልተሰማዉ ጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኒ እንደተጎዱ ነገር ግን በህይወት እንዳሉ የአሜሪካ የመከላከያ ሚንስተር አስታወቀ ይህም ጉዳይ ከፍተኛ የዓለም ትኩረትን የሚስብ ነው ተብሎለታል። #እንዲህ ዓይነቱ የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ሁኔታው በከፍተኛ የስልጣን ደረጃ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ያሳያል።
#በአሊ ካሜኒ ሁኔታ ዙሪያ ያለው እርግጠኛ አለመሆን ውጥረት የነገሠበት ድባብ ይፈጥራል። በኢራን ውስጥ የአመራር መረጋጋት በክልላዊ ቁጥጥር ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል፣ እና በዚያ ደረጃ ላይ ያሉ ጥቃቅን መስተጓጎሎች እንኳን በብዙ አገሮች ውስጥ ሰፊ የጂኦፖሊቲካዊ ምላሾችን ሊያስከትሉ ይችላሉ።
20/04/2026
አንዷለም በተመልካች ቁጥር ሪከርድ ሰብሮ ሁሉንም በለጠ🔥
በኢቢኤስ የቤተሰብ ጨዋታ ኮሜዲያን ያሲኖ እና አዝመራው ሙሉሰው የየራሳቸውን ክፍል ለህዝብ አድርሰዋል። የነቀምቱ አንዷለምም ሰይፉ ፋንታሁን ባዘጋጀለት ቀንነት የተሞላበት ኢትዮጵያዊነት በጎላበት መድረክ የሙከራ ክፍል ሰርቶ አሳይቷል።
የቀደሙ ሁለቱ የሰሯቸው ሁለቱንም ክፍሎች በመጀመሪያ 13 ሰዓታት ስናነጻጽር ያሲኖ አዝመራውን በእጥፍ ያክል ቁጥር መብለጡን እናስታውሳለን።
በዚህም ያሲኖ 180ሺህ ምልከታ ሲያገኝ አዝመራው በአንጻሩ 99ሺህ አግኞቶ ነበር። አንዷለም ግን 180ሺህ ለመሻገር የፈጀበት 12 ሰዓት ብቻ ሆኗል። አንዷለም በ13 ሰዓት ጊዜ 200ሺህ የሚጠጋ ምልከታ እንዲያገኝም ይጠበቃል።
ምልከታው በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ባለበት በዚህ የሙከራ ክፍል እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተመልካች የቀድሞ ተወዳዳሪ የፕሮግራም መሪዎች እንደሚያከብር የሚገልፅና አንዷለም ዕድሉ እንዲሰጠው የሚጠይቅ ሆኗል።
ዶች ኤችዲ
20/04/2026
የ7 ቀናት ድምፅ የመሆን Challenge!
ሁላችንም ሴቶች (እና እናት/እህት ያላችሁ ወንዶች) የዚህ challenge አካል እንድንሆን ጥሪ አቀርባለሁ። ዝምታችን ይሰበር!
ሰፈር ሱቅ የአንድ packet Modes ዋጋ 120 ብር ነው…እንደየሰፈሩ ደሞ ይጨምራል
are you kidding me ?
ይህ እኮ የቅንጦት ዕቃ አይደለም ተፈጥሯዊና መሰረታዊ ፍላጎት እንጂ።
ኑሮ ተወዷል በሚል ሰበብ ሴት ልጅ ንፅህናዋን ለመጠበቅ የምትቸገርበት ደረጃ ላይ ደርሰናል ወገን 🙄።
ለምን ድምፅ መሆን አለብን ካላችሁ:
1. የወር አበባ ወደን ያመጣነው ሳይሆን ተፈጥሯዊ ግዴታ ነው።
2. አንዲት ሴት በህክምናው መሰረት በየ 3-5 ሰዓቱ ሞዴስ መቀየር አለባት። ይህ ካልሆነ ግን ለከፍተኛ infection እና ለረጅም ጊዜ የጤና ችግር (including infertility) ልትጋለጥ ትችላለች። በ አንድ ወር 2 packet modes ያስፈልጋታል ማለት ነው።
3. በየቀለሙ እና በየስሙ ሀገር ውስጥ እየተመረቱ ያሉ ሞዴሶች ዋጋቸው ለምን ናረ? ጥራታቸውስ ለምን እየቀነሰ ሄደ? በየወሩ ከሚመጣው ህመም በላይ ጥራት የሌለው ሞዴስ የሚያስከትለው ስቃይ ለምን አይቆምም?
4. እኛ ዛሬ 120 ብር ኖሮን ብንገዛ፣ እነዛ ብር የሌላቸው ትምህርት የሚያቋርጡ ተማሪዎች እና በገጠር ያሉ እህቶቻችንን ጉዳይ ማን ያንሳላቸው?
እባካችሁ ድምፅ እንሁን የሞዴስ ጉዳይ ያገባናል የምትሉ ሁላችሁም ይህን challenge በመቀላቀል ይህንን ጽሁፍ በfacebook በ Tiktok እና በ LinkedIn statusአችሁ በማጋራት ለሚመለከተው አካል ድምፃችንን በጋራ እናሰማ ።
የወር አበባ ህመምን እና ተያያዥ ጉዳዮችን በ Media ሲወራ "አታካብጂ በወር አንዴ ለሚመጣው" ከሚሉ ጎጂ ንግግሮች ተቆጠቡ።
መንግስት ሞዴስ በነፃ የሚታደልበትን ወይም በትንሽ ዋጋ ለእያንዳንዷ ሴት የሚቀርብበትን መንገድ እንዲያመቻቹ እንፈልጋለን።
ሴት ልጅ ከሌለች ህይወት አይቀጥልም፤ የሴቶች ጤና የሀገር ጤና ነው! ✊
Bruktawit Bekele Uddo
19/04/2026
የሞዲየስ ዋጋ መጨመር የሴቶችን ጤና አደጋ ላይ እየጣለ ነው!
የንፅህና መጠበቂያ (ፓድ) የቅንጦት ዕቃ ሳይሆን መሰረታዊ የጤና ፍላጎት ነው። በአሁኑ ሰዓት ያለው የፓድ ዋጋ እጅግ ከመናሩ የተነሳ ብዙ ተማሪዎችና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖቻችን መግዛት የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል።
ፓድ የሴቶች የተፈጥሮ ዑደት አካል እንጂ በፍላጎት የሚገዛ "ጌጥ" አይደለም።
ዋጋው ባለመመጣጠኑ ምክንያት ብዙዎች ለተለያዩ የጤና እክሎች እየተጋለጡ ነው።
መንግስት እና የሚመለከታቸው አካላት በግብርም ሆነ በዋጋ ቁጥጥር ላይ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ድምፃችንን እናሰማ!
#የሞዲየስዋጋይቀንስ
Click here to claim your Sponsored Listing.