Walia Media

Walia Media

Share

Follow for daily Daily information

11/06/2026

አሳዛኝ መረጃ‼️

በሲዳማ ክልል ከኩታዮ ቀበሌ ፈልቆ፣ በኦሳ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብርሃኑን ማብራት የጀመረው ድንቅ ኮከብ፤ የማትሪክ ውጤቱን ሰቅሎ ለአካባቢው አይንና ኩራት የሆነው ወጣት ምሳሌ ቡዙነህ በድንገት ተለየን።

በአርሲ ዩኒቨርስቲ የሕክምና ትምህርት ክፍልን በመቀላቀል በማዕረግ (With Distinction) የተመረቀ የነገ ትልቅ ተስፋ የነበረው ባለሙያ ነበር።

ለቤተሰቦቹ ብቸኛ ወንድ ልጅ በመሆኑ ከምንም በላይ የሚሳሱለት፣ በአካባቢው ታላላቅ ልጆች ዘንድ "ተከታያችን" ተብሎ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት፣ ታናናሾቹም እንደ ስሙ 'ምሳሌ' አድርገው የሚያዩት እጅግ ትሁት እና ከተባለው በላይ Excellent ልጅ ነበረ።

በቅርቡ በሞጆ አካባቢ በሚገኝ የሕክምና ተቋም ውስጥ በሙያው ማኅበረሰቡን ማገልገል ጀምሮ እንደነበር ሰምተን ሳይጠገብ፣ ትናንትና አመሻሽ ግን ሕይወት አዳኝ በነበሩት በእነዚያ ጎበዝ እጆቹ በራሱ ላይ ጨክኖ ሕይወቱን ማጥፋቱን ስንሰማ ልባችን በሐዘን ተሰበረ። ኦሳ መብራቷን አጥታለች፤ ሎካም የነገ ተስፋዋን ተነጥቃለች።

የውድ ልጃችን ሃኪም ምሳሌ ቡዙነህ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በነገው ዕለት በተወለደበት በኩታዮ ቀበሌ ልዩ ስሙ 'ባዲቻ' በሚባለው ቦታ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ ይፈጸማል።

ለተከበሩ ቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለጠቅላላው የኦሳ፣ የኩታዮ እና የሎካ ማኅበረሰብ ጥልቅ መጽናናትን እንመኛለን።

10/06/2026

"እፈውስሃለው" በማለት የወጣቱን ህይወት ያሳጣው ፓስተር

ዋቅጅራ ገነት ይባላል፡ በምዕራብ ወለጋ የቂልሹ ካራ ተወላጅ ነው። በዩናይትድ ስቴትስ ይኖር የነበረ ለሰርግ ወደ ኢትዮጵያ በመጣበት ሰአት በህክምና የልብ ድካም እንዳለበት እና ቀዶ ጥገና ማድረግ እንዳለበት ተወሰነ።

የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የሆነችዉ ፍቅረኛው ህክምናውን ትቶ ፓስተር መሰረት ታዬ የሚባል ግለሰብ ጋር እንዲሄድ ምክር ትሰጠዋለችሽ። ግለሰቡም ወደ ፓስተሩ ሔዶ መጀመሪያ የተገጠመለትን የኦክስጅን ገመድ ፓስትሩ አስወገደለት።

"አዲስ ልብ ሰጥቼሃለሁ ተፈውሰሃል" ብሎም ላከው። ዋቅጂራ የሕክምና ባለሙያዎችን ንግግር ችላ ብሎ የነቢዩን ምክር ተቀበለ።

በሚያሳዝን ሁኔታም ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የመጣዉ ተስፈኛዉ ወጣት ወደ ቤቱ ለማረፍ እንደገባ እስከወዲያኛዉ አሸለቧል።

05/06/2026

ሀሰተኛ መረጃ በርካቶች "የአርሲ ኦርቶዶክሶች" ተብሎ እየተሰራጨ ይገኛል ነገሩ ግን አርሲ አይደለም በአማራ ክልል ማኖ ቀጨኔ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያ የአከባቢው ገበሬ አዲስ ላሰራው ቤተክርስቲያን በከተማ የተሰሩ የቤተክርስቲያን ንዋይተ ቅድሳትን ይዞ ወደ አዲሱ ቤተ ክርስቲያን ሲሄድ የሚያሳይ ምስል ነው።
በቪዲዮ ላይ የሚያውቁን የከተማ ሰዎች እየደወሉ ምን ሆናችሁ ነው? በማለት እየተጨነቁ ስለሆነ እኛ ጋር ሰላም መሆናችን የሚዘዋወረው ፎቶ እና ቪዲዮ ለአዲሱ ቤተክርስቲያን መሆኑን አሳውቁልን። በአርሲ የተፈጸመውን ተግባር ሙሉ በሙሉ እናወግዛለን።​ #አንድነት #ሰላምለሕዝባችን

04/06/2026

''የአርሲው ጥቃት በሸኔ ታጣቂዎች የተፈጸመ ነው'' የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ

የአርሲውን ጥቃት አስመልክቶ የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ መግለጫ ሰጥተዋል። አቶ ሀይሉ የአርሲው ጥቃት ምርጫውን ለማደናቀፍ በሸኔ ታጣቂዎች የተፈጸመ ነው።

በጥቃቱ ከዚህም በላይ ጉዳት እንዳይደርስ ህዝቡና የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ሀይል መስዋዕትነት ከፍሏል ብለዋል።

አሸባሪው ሸኔ ይህንን ጥቃት ያደረሰው ከታሪካዊ ጠላቶች ተልዕኮ ተቀብሎ የሀይማኖት ግጭት ለማስነሳት የነበረ ቢሆንም በህዝቡ አስተዋይነት ከሽፏል ሲሉ ተናግረዋል።

መከላከያ ሰራዊትየፌዴራል ፖሊስ የኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ሀይል የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እና አካባቢውን ለማረጋጋት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
#አርሲ #ኦርቶዶክስ

01/06/2026

በሰርጋቸው እለት ድምጽ የሰጡ ሙሽሮች

ሙሽሮቹ በሆሳዕና ከተማ በሌሞ 01 የምርጫ ክልል በሄጦ ቀበሌ መስኪድ ሰፈር ምርጫ ጣቢያ 07 በመገኘት ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

01/06/2026

‹‹የሚመጣውን ውጤት በጸጋ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ›› ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ

Photos from Walia Media's post 01/06/2026

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል። ዜጎች በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምፃቸውን እየሰጡ ናቸው።
#ውሳኔ

31/05/2026

ነገ ኢትዮጵያ ትመርጣለች
ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጭ የሚሳተፍበት ምርጫ ሊካሄድ አንድ ቀን ብቻ ቀረው!
#በምርጫብቻ #ምርጫ #ኢትዮጵያ

31/05/2026

ነገ ኢትዮጵያ ትመርጣለች

ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጭ የሚሳተፍበት ምርጫ ሊካሄድ አንድ ቀን ብቻ ቀረው!

#በምርጫብቻ #ምርጫ #ኢትዮጵያ

31/05/2026

ነገ ኢትዮጵያ ትመርጣለች
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት በቁጥር

ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጭ የሚሳተፍበት ምርጫ ሊካሄድ አንድ ቀን ብቻ ቀረው!

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa