Al-Huda News
Al-Huda News
ኢስቲግፋር
ሸይኽ ያሲር ሐፊዘሁላህ
በመካነ ሰላም ግድያ ለተፈፀመባቸው ምዕመናን በአዲስ አበባ መስጅዶች ሶላተል ጋኢብ እንዲሰገድ ከፍተኛ ም/ቤቱ ጠየቀ #መካነሰላም #የመስቀልጦረኞች
#ኃይማኖታዊጦርነት
#መካነሰላም
#ሙስሊምጠልነት
#አሐዳዊነት
#ሞዓተዋህዶ
#ፋኖ
#ኢማሙንገደሉት
#መስጂዱንደፈሩት
አዳምጡት‼ ሼር ይደረግ
በዚህም ዘመን የልባቸውን ከሠሩ በኋላ ማንነታቸውን መደበቅ የሚችሉ መስሏቸው ነበር?
የፋኖ የዘመቻ ቅስቀሳ እንዲህ ነው! | ሼር አድርጉት
" እኛ የምናጠቃቸው በእምነታችን ነው ፤ እኛ የምናጠቃቸው በሀይማኖታችን ነው። እኛ የምናጠቃቸው መድሀኔያለምን ሀይል አድርገን ነው ስለዚህ መድሀኔያለምን እስከያዝን ድረስ እነርሱ አርብ እሮብን እያረዱ እየበሉ ከእኛ ጋር ሊመጣጠኑ አይችሉም"
04/10/2025
በመካነ ሰላም ግድያ ለተፈፀመባቸው ምዕመናን በአዲስ አበባ መስጅዶች ሶላተል ጋኢብ እንዲሰገድ ከፍተኛ ም/ቤቱ ጠየቀ
04/10/2025
መንግሥት በመካነ ሰላም የመስጅድ ኢማምን ጨምሮ ግድያ የፈፀሙ ላይ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወስድ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ጥሪ አቀረበ
04/10/2025
የፌዴራሉ መጅሊስ መግለጫ አውጥቷል‼
==========================
✍️ «ኢናሊላሂ ወኢና ኢለሂ ረጂኡን!
እኛ የአላህ ነን ወደ እሱም ተመላሾች!
ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ!
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ከተማ መስከረም 23፣2018 ዓ.ል በመስጂድ ኑር በኢሻ ሰላት ወቅት ወደ መስጂድ የታጠቁ ኃይሎች በመግባት ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን በመወጣት ላይ በነበሩ ፦
1 የመስጂድ ዋና ኢማምና የወረዳው መጅሊስ ም/ሰብሳቢ
2 የመስጂድ አመራሮች
3 የመስጂድ ኻዲሞችን አሰቃቂ እና አረመኔያዊ በሆነ ሁኔታ መግደላቸውን የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አረጋግጦልናል።
እነሱም ሸሂድ ሆነዋል አላህ ጀነተል ፍርዶስ ይወፍቃቸው ።
ጠቅላይ ምክርቤቱ የእምነት ተቋማት የተከበሩ ቦታዎች በመሆናቸው ሊጠበቁ እንጅ እንዲህ አይነት አፀያፊ ተግባር የሚፈፀምባቸው መሆን የለባቸውምና ድርጊቱን በፅኑ ያወግዛል።
መላው የሃይማኖት ተቋማትም በእምነት ቦታዎች የሚደረጉ ትንኮሳዎች እና በእምነት ተከታዮች ላይ የተቃጣ መሰል የጅምላ ግድያ
ሊያወግዙና ሊያስቆሙ ይገባል።
ህዝበ ሙስሊሙ ይህንን በሀይማኖት ተቋማት ላይ የተቃጣ አደጋ ለመከላከል መረጃ በመለዋወጥ የሃይማኖት ተቋማትንና አካባቢውን እንዲጠብቅ ጠቅላይ ምክርቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ብዝሃ ሀይማኖት ባለባት ሀገራችን በተለያየ እምነት ውስጥ ያሉ ህዝቦች ለዘመናት ያቆዩተን ሰላማዊ እና መልካም መስተጋብር ሆን ተብሎ ለመናድና ማባሪያ ያጣ ቀውስ ውስጥ እንድንገባ የሚፈልጉ አካላት የፈፀሙት መሆኑን ጠቅላይ ምክርቤቱ ይገነዘባል።
በመጨረሻም ሁሉም ሃይማኖት ተቋማትና መሪዎች ይህ ጉዳይ አብሮ የመኖር እሴት እንዳይሸረሽር ብሎም እንዳያጠፋ ድርጊቱን እንድታወግዙ እንዲሁም በፅኑ እንድትቃወሙ እየጠየቅን መንግስትም ይህንን ተግባር በእምነት ቦታዎችና አባቶች ላይ የፈፀሙት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን።»
©: መስከረም 24፣2018 ዓ.ል
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት
04/10/2025
የአዲስ አበባ ከተማ መጅሊስ ትናንት ምሽት በመካነሰላም ህይወታቸው ላለፈው የመስጂድ ኢማም፣ የመጅሊስ አባላትና ሙስሊሞች ግድ' ያ ጉዳይ መግለጫ አውጥቷል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
1165