Gech Media

Gech Media

Share

Follow for more

21/02/2026
09/02/2026

With Bonga University – I'm on a streak! I've been a top fan for 3 months in a row. 🎉

23/01/2026

🔴አሳዛኝ ዜና 👉ከወላይታ‼️
#በወላይታ ዞን ከጠበላ ከተማ አስተዳደር ወደ ሶዶ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ #ተሽከርካሪ በተቃራኒ መንገድ #በሞተር ሳይክል ይጓዙ የነበሩ ሁለት #ሰዎችን በመግጨት #የሞት አደጋ አድርሷል።

#ወላይታ ሶዶ ጥር 15/2018 ዓም
ሟቾች ባልና ሚስት መሆናቸውም ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

ፖሊስ ከስፍራው ደርሶ የአደጋው መጠንና መንሰኤ እያጣራ ሲሆን በቀጣይ ያለውን መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል።

04/01/2026

Kaffa Bonga Bonooge

Photos from Gech Media's post 31/10/2025

ግዕዝን መማር ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ማወቅ ነው።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ "የአብነት ትምህርት ለዘመናዊ የኢትዮጵያ ሥነ ትምህርት" በሚል መሪ መልዕክት ዐውደ ጥናት አካሂዷል።

በዐውደ ጥናቱ የግዕዝ ቋንቋ ጥናት ለኢትዮጵያ የዕውቀት እና የምርምር ዘርፍ ስላበረከተው አስተዋጽኦ በዘርፉ ታዋቂ ምሁራን የጥናት ሥራዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ ሙሉቀን አንዱዓለም (ዶ.ር) ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ የግዕዝ ቋንቋን በማስተማር ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡ በቅርቡ ደግሞ የሦሥተኛ ዲግሪ ለመጀመር በዝግጅት ላይ መኾኑን ጠቅሰዋል፡፡

ዓለም ላይ በርካታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግዕዝን እያስተማሩ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡ ዓለም ላይ ግዕዝን የሚያስተምሩ ቁጥራቸው 31 የሚደርሱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን መመልከታቸውንም አንስተዋል፡፡ ይህን የሚያደርጉትም በምክንያት መኾኑን ነው የተናገሩት፡፡ ግዕዝን የሚማሩ ብዙ ኢትዮጵያውያን እና የሌሎች ሀገር ዜጎች እንዳሉም ጠቅሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ ደግሞ ቁጥራቸው ጥቂት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ብቻ ግዕዝን እንደሚያስተምሩ ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ ብዙ ታሪኮች ቢኖራትም በትክክል አልተጠናችም ነው ያሉት። ስለ ኢትዮጵያ ሌሎች ሀገሮች አጥንተው ከሚናገሩ ኢትዮጵያውያን ግዕዝን በመማር ታሪክን በማንበብ እና በመመርመር ማንነቷን ሊናገሩ እንደሚገባ ጠቅሰዋል፡፡

ወጣቱ ትውልድ ግዕዝን በመማር ይህን እንዲረዳ እና እንዲነቃ ለማድረግ ዐውደ ጥናቱ መዘጋጀቱን አንስተዋል፡፡ ከታችኛው የትምህርት ደረጃ ጀምሮ የራስን ቋንቋ መማር እንደሚገባም ተናግረዋል።

የዐውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች በግዕዝ ቋንቋ ትልልቅ መጽሐፎች መጻፋቸውን ነው የተናገሩት። እነዚህን ጥንታዊ መጽሐፍትን ለመረዳት እና ለመመርመር የግዕዝ ቋንቋ መማር አስፈላጊ መኾኑንም አንስተዋል።

አሁን ላይ ያለው ትውልድ ግዕዝን በመማር የሀገር እና የአባቶችን ታሪክ በማጥናት ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባውም አንስተዋል።

ግዕዝ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ቋንቋ መኾኑንም ተናግረዋል። ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ዐውደ ጥናት ማዘጋጀቱ ሊቀጥል የሚገባ ተግባር መኾኑንም ተናግረዋል።

በዐውደ ጥናቱ የማጠቃለያ መርሐ ግብርም "አብነት ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ትምህርት" በሚል ርዕስ በተለያዩ ምሁራን የተጻፋ ጥናታዊ ጽሐፎችን በማደራጀት የተዘጋጀ እና በመርሻ አለኸኝ (ዶ.ር) አርትኦት የተሠራለት መጽሐፍ ተመርቋል።

ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ (አሚኮ)

30/10/2025

With Debre Berhan University – I just got recognized as one of their rising fans! 🎉

30/10/2025

With እፎይ ኦርቶዶክስ Effoy Orthodox – I just got recognized as one of their top fans!

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa