Yeka press first

Yeka press first

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Yeka press first, Grocers, Dm, Addis Ababa.

Photos from Debre Markos City prosperity party /ብልፅግና's post 11/11/2025
Photos from ንጉስ ተክለኃይማኖት ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ  ፔጅ's post 09/11/2025
Photos from Amhara Prosperity Party /APP/'s post 05/11/2025
Photos from Yeka press first's post 23/10/2025

በ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ10 ነጥብ 2 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል

በ2018 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ10 ነጥብ 2 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ100 ቀን እቅድ ግምገማ የዓለምን የኢኮኖሚ አዝማሚያ እንዲሁም የኢትዮጵያን ማክሮ ኢኮኖሚ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ተመልክቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም የእድገት አዝማሚያን እና አጠቃላይ ምልከታን ያካተተ እንደነበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዓለም የኢኮኖሚ ልማት አውድ አንጻር ኢትዮጵያ ልዩ ጥንካሬ እና የእድገት ፍጥነት ማሳየቷ ነው የተገለጸው፡፡

በ2017 የበጀት ዓመት የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢኮኖሚ አፈፃፀም በጥንካሬው በመቀጠል 9 ነጥብ 2 በመቶ ዓመታዊ የጂዲፒ እድገት አሳይቷል።

ይህም 7 ነጥብ 3 በመቶ በሆነ ጠንካራ የግብርና ውጤት መስፋፋት፣ በ13 በመቶ የኢንዱስትሪ እድገት ብሎም በ7 ነጥብ 5 በመቶ የአገልግሎት ዘርፍ እድገት የተገለጸ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡
የኢትዮጵያ የጂዲፒ ተዋፅኦም በብዝኃ መሠረት እየያዘ መሄዱን የሚያሳይ ሲሆን÷ ይህም በግብርና 31 ነጥብ 3 በመቶ፣ በኢንደስትሪ 30 ነጥብ 2 በመቶ እና በአገልግሎት 39 ነጥብ 6 በመቶ አስተዋፅኦ የታየ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

እየተካሄዱ በሚገኙ የለውጥ ሥራዎች፣ በመንግሥት እየተከወኑ ባሉ የተለያዩ የልማት ሥራዎች እና አዲስ ኢንቨስትመንቶች በመደገፍ በ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ10 ነጥብ 2 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል።

እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ፕሮጀክቶች መጠናቀቅ ብሎም የማዳበሪያ ማምረቻ እና የተፈጥሮ ጋዝ ልማት ሥራ ጅማሮዎች የኢኮኖሚ እድገቱን የበለጠ እንደሚያነቃቁ ተገልጿል፡፡

የየዘርፉ የእድገት ትንበያም ጠንካራ ውጤት እንደሚገኝ ያመለከተ ሲሆን÷ግብርና በ7 ነጥብ 8 በመቶ፣ በአዳዲስ የማኑፋክቸሪንግ ፕሮጀክቶች እና የተሻሻሉ ግብዓቶች የተጠናከረው ኢንዱስትሪ 13 ነጥብ 2 በመቶ እንደሚያድጉ መተንበዩ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም የአገልግሎት ዘርፉ እድገት በሚያሳዩት የንግድ እንቅስቃሴ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የቱሪዝም ፍሰት እና የዲጂታል ኢኮኖሚ መስፋፋት በመጠቀም 9 ነጥብ 3 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል።

የውጭ ንግድ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን÷ ይሄም እቅዱን እና የባለፈውን ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ አፈፃፀም የበለጠ ሆኖ መታየቱ ተጠቅሷል፡፡

የፋይናንስ ዘርፉ የልማት ሥራዎችን እና ኢንቨስትመንትን በመደገፍ እና ቁልፍ ሚናውን እየተወጣ ሲሆን ÷ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 113 በመቶ የሆነ ከቀደመው ተመሳሳይ ጊዜ ብልጫ ያለው የብድር አቅርቦት አቅርቧል።

የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትም እየተጠናከረ መሄዱን መቀጠሉና በሶስት ወራት ብቻ 6 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር የተንቀሳቀሰበት ደረጃ መደረሱ ተገልጿል፡፡

አጠቃላይ አፈፃፀሙ በሁሉም መስኮች የተሻለ ውጤትን የሚያሳይ ሲሆን÷ ይህም ኢትዮጵያ ወደ ኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ብሎም ዘላቂ እና አካታች የኢኮኖሚ እድገት የምታደርገውን ፈጣን ሒደት የሚያረጋግጥ ነው።

Want your business to be the top-listed Grocery Store in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Dm
Addis Ababa