Menen Daniel

Menen Daniel

Share

Model and actors

12/04/2026

መልካም ፋሲካ ✝️💒🙏

13/03/2026

✍️✍️ ሰላም ተወዳጆች part 4 እንዳዘገየሁት አውቃለሁ ለዛም ከልብ የመነጨ ይቅርታን እጠይቃለሁ። እነሆ አሁን ተለቋል

[ ] part 4 ✍️✍️ ቀና ስል ያየሁትን ማመን አቃተኝ፤ ስለ አለቃዬ ላጫውታቹ አሁን ከፊት ለፊቴ ቆሞ ያየሁት ሰውነቴ በረዶ እስኪሆን በድንጋጤ ያቀዘቀዘኝ ሰው በአንድ ወቅት አፈቀርኩሽ በሚል ሰበብ መግቢያ መውጫ ያሳጣኝ ሰው ነበር እሱን ላለማግኘት ሰፈር ቀይሬያለሁ፣ ስልክ ቁጥር ቀይሪያለሁ፣ በቻልኩት መጠን በየትኛውም ማህበራዊ ገፆችም እንዳያገኘኝ ተከላክያለሁ። ለምን ጠላሽው ራቅሽው ልትሉ ትችላላቹ? የተዋወቅነው እኔ አንድ ድርጅት ላይ እሰራ ነበር በአጋጣሚ ይሄ ሰው ደምበኛችን ነበር ስራው ከውጭ የሚገቡ የተለያዩ መሳሪያዎችን ያከፋፍላል ጅርጅታችን እሱም የዚህ እቃዎች ተጠቃሚ ነበር። በዚህ የተጀመረ ትውውቅ ወደድኩሽ የሚል መልዕክት መጣ እኔም በጨዋ መልክ አለመፈለጌ ጥያቄውን አለመቀበሌን አስረግጬ ተናገርኩ። ለምን አለኝ መዋሸት አልፈለኩም ስለዚህ ትክክለኛውን መልስ ተናገርኩ። አልፈልግም ምክንያቴ የምፈልገው ነገር እሱ ጋር የለም ። ምንድነው የምትፈልጊው? በተግባባንባቸው ጊዜያት ትንሽም ቢሆን የታየኝ ማንነት አለ ያን ደሞ እኔ አልወደውም። እኔ የምፈልገው ስብዕና ማየት አልቻልኩም ስለዚህ አንተን መቀበል አልችልም አልኩት። እሱ ግን እልህ ያዘው ጠዋትም ማታም መሄጃዬን አጣበበብኝ። ስራውን ተውኩት ከላይ እንደተናገርኩት በየትኛውም መንገድ እሱ እኔን ማግኘት እንዳይችል መንገድ ዘጋሁ ከዛ በኋላ ነበር ስራ ፍለጋ ስወጣ እሱ ድርጅት ውስጥ የተገኘሁት። በዝምታ ተዋጥን ሁለታችንም ደንግጠናል። ወደራሴ ተመልስኩ እና ዞር ብዬ ቦርሳዬን ለማንሳትት ስዞር ምን ልታደርጊ ነው አለኝ? ልሄድ፤ ለምን? ትክክለኛ ቦታ አይደለሁም አልኩት። ቁጭ በይ እናውራ አለኝ። ስለምን? ስለ ሁሉም። እሺ ። ቁጭ አልኩ፣ እሱም ተቀመጠ። ለምን እንደዛ አደረግሽ ? ምን ማድረግ ነበረብኝ? ትክክል አልነበርሽም። እሺ። የእኔ መልስ ነበር አሁንም ከእሱ ጋር ማውራት አልፈለኩም። በረጅሙ እየተነፈሰ........ አሁን ይሄ ስራ ቦታ ነው ከእኔ እና ከአንቺ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ስራሽን መስራት ትችያለሽ። እኔ አለቃሽ ነኝ በቃ ሌላ ነገር የለም። ያ ያለፈ ታሪክ ነው። መልካም ቀን ብሎኝ ቢሮዬን ለቆልኝ ወጣ። ጭንቅላቴ ተጨነቀ ይበል እንጂ ያለፈ ታሪክ እንደማያደርገው እርግጠኛ ነበርኩ ስለዚህ የሱን ሀሳብ መስማት አልፈለኩም በድጋሚ ሌላ ስራ መፈለግ እንዳለብኝ ተሰማኝ። ስልኬን ከቦርሳ አውጥቼ ስመለከት መልዕክት አለኝ።እንግዳዬ ነበር የሱን መልዕክት ሳነብ ጭንቀቴ ሁሉ ወዴት እንደጠፋ አላውቅም ደስ አለኝ ለሱ መልዕክት መፃፍ ጀመርኩ ፅፌ ስጨርስ ከራሴጋር ለማውራት ሞከርኩ ስራ እስካገኝ መስራት እንዳለብኝ ወስኜ ወደ ስራ ገባሁ። ስራዬን እየሰራሁ ከእንግዳዬ ጋር በየመሀል መልዕክት እንላላካለን ምሳ ስዓት ደረሰ ወጥቴ በዛው ቡና እጠጣለሁ በዛው እበላለሁ ብዬ ቦርሳዬን ይዤ ለመውጣት ስንደረደር አለቃዬ መጣ። ምሳ እየወጣሽ ነው? አዎ፣ አብረን እንውጣ? አይ እታች ሰው እየጠበቀኝ ነው። እሺ መልካም ጊዜ አለኝ እና ሄደ አሁንም ምቾቴ ተነሳ፣ ወረድኩ እና ምሳ እቃ ከፍቶ ለብቻዬ መብላት አስጠላኝ። ግራ እየተጋባሁ አስተናጋጁዋ መጥታ ምን ልታዘዝ ስትለኝ፥ ውሀ አልኳት በዚህ ቅፅበት እንግዳዬ መልዕክት ላከልኝ፥ ለምሳ ወጣሽ አለኝ፤ አዎ እሩቅ ነው ስራ ቦታህ አልኩት? አይ አይደለም። የት ነው? ቦሌ ። እንዴ እኔም እኮ እዛው ነኝ። ለምን ምሳ አብረን አንበላም ብዬው ቦታዬን ነገርኩት። በሚገርም ፍጥነት መጣ ምሳችንን አብረን በላን ስራ ቦታዬን አየው። ከዛ እሱም ወደ ስራው ተመለሰ እኔም ወደ ስራ ገባሁ። አመሻሽ ስራዬን ጨርሼ ከስራ መውጫ ስዓት ደርሶ ልወጣ ቢሮዬን እየቆለፍኩ አለቃዬ መጣ። እየወጣሽ ነው? አዎ እየወጣሁ ነው። አሪፍ ወዴት ነሽ ላድርስሽ? አመሰግናለሁ ከሰው ጋር ነኝ። እሺ መልካም ምሽት ብሎኝ በፍጥነት ወደ ፊት ተራመደ። እኔም የቢሮዬን ቁልፍ በቦርሳዬ እየከተትኩ መራመድ ጀመርኩ። በስልኬ መልዕክት ገባ እንግዳዬ ነበር። በር ላይ ነኝ አልወጣሽም? በፍጥነት እየተራመድኩ እየመጣው ነው አልኩት። በር ላይ ቆሞ እየጠበቀኝ ነበር። አሁን ጉዞ ወደ ቤት ፊቴ ላይ ግን ትንሽ ጭንቀት አለ ገብቶታል ግን መጠየቅ አልፈለገም። አንድ ቦታ እንሂድ አለኝ? የት? እንጦጦ ኪዳነምህረት ተሳልመን እንምጣ አለኝ። ልቤ እንዴት በሀሴት እንደዘለለ። እሺ በጣም ደስ ይለኛል አልኩት። ጉዞ ወደ እንጦጦ ኪዳነምህረት። ነጠላ አልያዝኩም ነበር ሽሮ ሜዳ ነጠላ ገዝቶ ሰጠኝ ነጠላዬን ለብሼ ሄድን ስንደርስ ደስ የሚል አየር ቅዝቅዝ ያለ ንፋስ ብቻ ፀሎታችን ፀልየን ተቀመጥን ለረጅም ሰዓት። እንግዳዬ እንዲህ አለኝ ሲጨንቀኝ እዚህ መጥቼ ለእናቴ እነግራታለሁ እሷም ታስተካክልልኛለች። ንገሪያት የልብሽን ሁሉ እሷ የሁሉም እንባን ታብሳለች። ለሰው ቢነግሩት ትርፉ ወሬ ብቻ ነው ለእግዚአብሔር የነገሩት ግን መፍትሔ አለው እሺ። አለኝ አዎንታዬን አንገቴን በመነቅነቅ ገለፅኩለት። ብዙ እረፍትን ተሰማኝ። አመስግኜው አሁን እንሂድ አይደል እየጨለመ ነው አልኩት። እሺ እንሂድ ብሎኝ ተሳልመን መንገዳችንን ጀመርን። ወደ ቤት አድርሶኝ ተመለሰ እኔ ወደቤት ገብቼ ልብሴን እየቀየርኩ ብዙ ሀሳብ ማሰብ ጀመርኩ። አሁን ሌላ ስራ መፈለግ አለብኝ የአለቃዬ አካሄዱን አልወደድኩትም። እንግዳዬን ወድጄዋለሁ ለአፍታም ሀሳቤ ከእሱ እንዲርቅ አልፈልግም። አይኖቹ ውስጥ ያለው ርህራሄ፣ ለቤተክርስቲያን ያለው ቅርበት፣ ቅንነቱ፣ የዋህነቱ፣ ንፁ ልብ ያለው ሰው ነው። ይሄ ለእኔ የፀሎቴ መልስ ነው። እሱ በረከቴ ነው። ልቤ ይሄንን ያምናል። አሁን ምን ላድርግ ያለውን ነገር ለእንግዳዬ ነገሬው ስራ መፈለግ ላይ ያግዘኝ ወይስ እራሴ ልወጣው? አለቃዬ እንደማይፋታኝ አውቃለሁ። ስለ እንንግዳዬ ከሰማ ደሞ ለማጣላት እና ለማለያየት ቅድሚያ ተሰላፊ ነው። ለምንድነው ግን አንድ ጥሩ ነገር ሲመጣ መከራን ችግርን አስከትሎ የሚመጣው?

✍️................................

✍️✍️✍️ መነን ዳንኤል .............

Want your business to be the top-listed Interior Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

28-78031
Addis Ababa