Stand With Raya

Stand With Raya

Share

የራያ ህዝብ ድምጽ ሊሰማ እና የማንነት ጥያቄ ሊከበር ይገባል።!!

03/05/2026
Photos from Stand With Raya's post 09/03/2026

ጉዳዩ:- የፌደሬሽን ም/ቤት በራያ ምርጫ ክልሎች ያስተላለፈው ውሳኔ እንዲጸናልንና ጥያቄው ላይ ማስተካከያ እንዲደረግልን ስለመጠየቅ ይመለከታል።!!

በኢፌዴሪ ፈዴሬሽን ም/ቤት ውሳኔ መሠረት ጥር 25/2018 ዓ.ም የተጻፈለትን ደብዳቤ መነሻ በማድረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የካቲት 16/2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በትግራይ እና አማራ ክልል መካከል አጨቃጫቂ ቦታዎች የምርጫ ክልሎች ከተባሉት መካከል የራያ ኮረም አፍላ እና ራያ አላማጣ ምርጫ ክልሎች ከትግራይ ክልል ወጥተው በየትኛውም ክልል ላይታቀፉ በሚቀጥለው ምርጫ በቀጥታ ለፌዴራል ምክር ቤት እንዲመርጡ የሚለውን ውሳኔ ተቃውሞ ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ከሳሽ) በተከሳሽ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ላይ በቀን የካቲት 19/2018 ዓ.ም በኮ/መ/ቁ 351364 ባስገባው የቃለ መሐላ አቤቱታ መሠረት የፈዴራል የከፍተኛ ፍርድ ቤትም በተመሳሳይ ቀንና መዝገብ ቁጥር ጊዜያዊ እግድ መስጠቱ ይታወቃል።!!

ነግር ግን የራያን ሕዝብ የማንነትና የራስን በራስ አስተዳደር ኮሚቴ የፌዴሬሽን ም/ቤት ውሳኔ እና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እየተከተለው ያለው የአተገባበር ሂደት ተገቢና የራያ ሕዝብ ሕገመንግሥታዊና ዴሞክራሲያዊ መብትን የሚያስከብር ውሳኔ ነው ብሎ ያምናል፡፡!!

ኮሚቴው የራያ የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ሕገመንግስታዊ ጥያቄው እንዲመለስለት ሲል የወከለውን ሕዝብ 5% የሚሆን 27 ሺሕ የድጋፍ ድምጽ (ፊርማ አሰባስቦ በቀን ጥቅምት 29/2011ዓ.ም በቁጥር ራማ/001/2011 በወቅቱ ለነበረው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ቤት በቀጥታ ለኢፈዴሪ ፌዴረሽን ምክር ቤትና ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ደግሞ በግልባጥ ማስገባቱ ይታወቃል፡፡ ይህንንም መነሻ በማድረግ የራያን ሕዝብ የማንነትና ራስን በራስ አስተዳደር ፍትሐዊ ጥያቄ በገባ በሁለት ዓመቱ በታኅሳስ ወር 2013 ዓ.ም በጊዜው የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈጉባኤ የነበሩት ክቡር አቶ አደም ፋራሕ የመሩት የልኡካን ቡድን ወደ አከባቢው በአካል በመሔድ በተለያዩ ወረዳዎችና አከባቢዎች የሚገኘውን ነዋሪ ሕዝብ በቀጥታ በማወያየት የራያ ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄ ማንነትና ይዘት ምን እንደሆነ አጥንቶ ለውሳኔ መነሻ ሊሆን የሚያስችለውን መረጃ ይዞ ተመልሷል፡፡!!

የጥናቱና የጕብኝቱ ሪፖርትም በወቅቱ ኮሚቴውን በሰብሳቢነት ይመሩት በነበሩት አባላችን እና ልኡካኑን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት መደረጉ ይታወሳል፡፡!!

በተደጋጋሚ በህወሓት TPLF ጸብ አጫሪነት ሳቢያ ከፌደራል መንግሥት ጋር ይካሄድ በነበረው ተደጋጋሚ ጦርነት እና አለመረጋጋት ምክንያት የራያ ሕዝብ የማንነትና ራስን በራስ አስተዳደር ጥያቄ ወቅታዊ ምላሽ ስላላገኘ እና በጦርነቱ ወቅትም “አጨቃጫቂ አከባቢዎች የሚል ስያሜ የተሰጣቸው የራያ አከባቢዎች ባለቤቱ የሆነውን የራያን ሕዝብ ወደ ጎን በመተው "ርስት መልሰናል" በሚሉ የአማራ እና “መሬታችን አንሰጥም በሚሉ የትግራይ ታጣቂዎች በወቅቱ የነበሩት የሁለቱም ክልሎች አመራሮችና ፖለቲከኞች ሳይቀሩ የራያን ሕዝብ ስነ ልቦናና ህልውና በሚገዳደር መልኩ ብዙ ግፍና መከራን ሲፈጽሙበት ስለነበር ኮሚቴው ይህንኑ ግፍና መከራ እንዲሁም የማንነትና የራስን በራስ አስተዳደር የክልልነት ጥያቄ የያዘ አቤቱታ በድጋሚ በሀምሌ 27/2014 ዓ.ም በቁጥር ራማ/026/2014 ለፌዴሬሽን ም/ቤት አስጉብቷል፡፡!!

ምንም እንኳ ሕዝበ ውሳኔ ተካሂዶ ጥያቄው ፈጣን ምላሽ ባይሰጠውም የፕሪቶሪያ ስምምነቱ በሚያዘው መሠረት አምስት የሚሆኑ የራያ ወረዳዎች በፌደራል መንግሥት ቁጥጥር ስር ሆነው እስከ ባለፉት ሁለት ወራት ድረስ በኮማንድ ፖስት ሲተዳደሩ ነበር፡፡ ይህ በመሆኑም በውሳኔ ያልተደሰቱ በአንዳንድ ሕገመጥ ታጣቂዎች የሽፍትነት ተግባራት ይስተዋሉ የነበሩ ቢሆንም “እኔን ካልመሰልክ ላሰቃይህና ላጥፋህ የሚለው ግልጽ የሆነ ኢ-ሰብአዊና ኢ-ዴሞክራሲያዊ ግፍ የተመላበት ተግባር በአንጻሩ የቀነሰበት ሁኔታ ነበር፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ከሁለቱም ክልሎች ተጽእኖ ተላቆ በፌደራል ስር ስለነብር ነው:: አሁንም የ7ኛው ዙር ሃገራዊ ምርጫን አስመልከቶ የራያ ኮረም/አፍላ እና ራያ አላማጣ ምርጫ ክልሎች ከትግራይ ክልል ወጥተው በየትኛውም ክልል ሳይታቀፉ በቀጥታ ለፌደራል ም/ ቤት እንዲመርጡ የሚለውን የፌዴረሽን ም/ቤት ውሳኔ እንዲጸና ኮሚቲያችን ድጋፉን ይገልጻል፡፡ ይህ ባይሆን ግን ሲያጋጥሙት የነበሩትና በከፋ ሁኔታ ተጠናክረው የሚቀጥሉት ችግሮችና የመብት ጥሰቶች በርካታ ይሆናሉ፡፡ ከዚህ ቀደም ይፈጸሙ የነበሩትና ተጠናከረው ይቀጥላሉ ብሎ ኮሚቴው የሚያነሳቸው ግፋዊና ኢ-ሰባዊ ድርጊቶች መካከል ለማሳያነት ያክል የሚከተሉትን ይጠቅሳል፦

1ኛ.ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ የሆኑት በነጻነት ሃሳብን የመግለጽ፣ የመሰብሰብ የመምረጥና የመመረጥ መብቱ በሁለቱም ክልል የፖለቲካ አመራሮችና ሊሂቃን ምክንያት ተጽእኖ ስር ይወድቃል:: በመሆኑም ነጻ፣ ግልጽና ተአማኒነት ያለው የ7ኛው ዙርምርጫ በተገቢው ላይካሄድ ይችላል ብሎ ይሰጋል፡፡!!

2ኛ. የህወሓት/TPLF ሕገወጥ ቡድን ከዚህ ቀደም ለ30 ዓመታት ያክል በራያ ሕዝብ ላይ ያደርሰው የነበረውን ኢዴሞክራሲያዊና ኢሰብአዊ የመብት ጥሰት ማለትም እስራት፤ ማፈናቅል እና ግድያ ለማስታውስም ይከብዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ገበሬውን ከሚያርሰው መሬት በማፈናቀል ለአካባቢው ማኅበረሰብም ይሁን ለሃገር ምንም ፋይዳ በሌለው ኢንቨስትመንት ስም መሬቱን ለህወሓት TPLF ባለስልጣኖችና የነሱ አገልጋይ ለሆኑ የትግራይ ባለሃብቶች በመስጠት ሕዝባችንን ሲያራቁት፣ ታዳጊዎችና ወጣቶች እንዲሁም ጎልማሳ ወንዶችና ሴቶችን ጨምሮ ለዓረብ ሃገር ስደት ሲዳርግ የነበረበት ሂደት ያስቀጥላል፤ አሁንም በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ባሉ የራያ ራዩማ ወረዳዎች እያከናወነውና ወገኖቻችንን እያሰቃያቸው ይገኛል፡፡!!

ስለዚህ ሕገ መንግስቱ ከመጽደቁ በፊት በ1984/5 ያካለሉትን የራያ አምስቱ ወረዳዎች ለማምታታት የሚጠቀሙበትን በ1987 ዓ/ም የጸደቀው ሕገመንግስት ማጣቀሻ ተቀባይነት የሌለውና ራሱን በራሱ ማስተዳደር ለሚፈልገው የራያ ሕዝብ መበቱ የሚጋፋ መሆኑን ያሳውቃል።!!!

3ኛ. በተመሳሳይ መልኩ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የአማራ ክልል መንግስት አመራር በነበሩ እና በወቅቱ ሃገራዊነትን ሽፋን አድርገው የግል ፍላጎታቸውን ማሳካት የፈለጉ ሕገወጥ ታጣቂዎች ማንም ባልፈቀደላቸው እና የራያ ሕዝብ ይሁንታ ሳይሰጣቸው ርስታችን አስመልሰናል በሚል ኋላ ቀር የፊውዳል አስተሳሰብ ለ8 ወራት ያክል ዘርግተውት በነበረው ሕገወጥ የአስተዳደር መዋቅር እና ጉዳይ አስፍጻሚ ታጣቂዎቻቸው አማካኝነት በርካታ የሆኑ የሰባዊ መብት ጥሰቶችን ሲፍጽሙ ቆይተዋል፡፡ የብዝሃ ቋንቋ ተናጋሪ የሆነውን የራያ ሕዝብ በፈለገው ቋንቋ እንዳይናግር ገደብ ጥለውበት ነብር፤ በሚኮራበት ማንንትና ባህል ራሱን እንዳይገልጽ ያሸማቅቁት፣ ያስሩት፤ ያፍኑትና ይገድሎት ነበር፡፡ በመሆኑም ሕዝባችን ነጻነቱን እንጂ የሃገርና ሌላ ተጨማሪ ግፍ የሚፈጽምበት አካል አይሻም፡፡ ስለሆነም ሕዝባችን መብቱን ለማስጠበቅ ከሁለቱም ክልሎች ነጻ ይሁን።

4ኛ, እላይ ከጠቀስናቸው የሁለቱም ክልሎች ርስትና መሬቱን ፈልገው የተከበረውን የራያ ሕዝብ ግፍ እና በደል የሚፈጽሙ ቡድኖችም ሆኑ የፖለቲካ ሊሂቃን ተላቆ ማንነትቱ በሕገመንግስቱ ተረጋግጦና ታውቆ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱ ካልተከበረለት ህልውናውን፣ ማንንቱን፣ ቱባ የሆነው እና ደማቅ ባህሉናን ታሪኩን ጠብቆ ማቆየት አይችልም፡፡ በመሆኑም ነጻና ገለልተኛ የሆነ ፍትሕም ሆነ የራሱን ማንነት መወሰን የሚችለው ቀጥታ በፌደራል ስር ሲሆን ነው።!!

5ኛ. ኮሚቴያችን በተደጋጋሚ እንደሚጠይቀው 27 ሺሕ የድጋፍ ድምጽ ፈርማ ያሰባሰብነው ራያ ራዩማ ተብሎ በሁለቱም ክልሎች ያለውን ነዋሪ ሕዝብ 5% የሚወክል ሲሆን ከራያ አላማጣ እና ኮረም ኦፍላ በተጨማሪ ከራያ ቆቦ፣ ከራያ ጨርጨር እና ከራያ ዓዘቦም ጭምር የተሰበሰበ ነው:: በማንነት ሕዝበ ውሳኔው ጊዜም ሆነ አሁን ራያን በተመለከተ በሚወሰኑት አጠቃላይ የማንነትና የአስተዳደር ውሳኔዎች "አጫቃጫቂ አካባቢዎች በሚል የሁለቱም ክልሎች የርስት ፍላጎትና የወሰን ጥያቄ ተደርጎ እየቀረበ ያለው አካሄድና ውሳኔ የራያ ሕዝብን ህልውናና ጥያቄ ወደጎን ትቶ የሁለቱም ክልሎች መሬት የመቀራመት ፍላጎትን የሚያሳካ ነው፡፡!! የራያ ሕዝብ ጥያቄ የአምስትና ስድስት ወረዳዎች ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ራያ ራዩማ ተብለው የሚታወቁት ቆላና ደጋውን ጨምሮ ከአላ አስከ ኤቦ 17 ወረዳዎችን ያካተተ (ራያ ቆቦ ፤ ቆቦ ከተማ፤ራያ አላማጣ፣ አላማጣ ከተማ፣፣ራያ ኦፍላ ፣ ኮረም ከተማ፣ራያ ዛታ ፣ራያ ዓዘቦ፣ መሆኒ ከተማ፣ራያ ጨርጨር፣ ራያ ባላ፣ ራያ ዓዲ ሞኾኒ ፣ ማይጨው ከተማ፣ ራያ ነቕሰገ ፣ ራያ ቦራ ፣ ራያ ስላዋና እና ራያ አላጀ) ጥያቄ ነው፡፡ ስለሆነም የተከበረው የፌዴሬሽን ም/ቤት የራያ ሕዝብ ጥያቄን እንዲያደርግበት ኮሚቲው አበክሮ ይጠይቃል፡፡

በውሉ ተረድቶ የወሰን ይገባኛል በሚል ሳይሆን የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር / የክልልነት ጥያቄ ብሎ ማስተካከያ እንዲያድርበት ኮሚቴው አበክሮ ይጠይቃል።!!!

ከሰላምታ ጋር🙏🙏🙏

የራያ ማንነትና ራስን በራስ አስተዳደር ኮሚቴ!!

04/03/2026

ለፈደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት

ከሳሽ፡ ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ

ጣልቃ ገብ፤ ራያ ራዩማ ዲሞክራስያዊ ፓርቲ፤ አድራሻ አዲስ አበባ

በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 41 መሰረት የቀረበ የጣልቃ ገብ አቤቱታ

ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ከሳሽ) በተከሳሽ የ ኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ላይ በቀን 19/06/2018 ዓም በሙቁ 351364 በትግራይ እና አማራ ክልል መካከል አጨቃጫቂ ቦታዎች የምርጫ ጣብያዎች በተባሉት እና በሚቀጥለው ምርጫ በየትኛውም ክልል ሳይታቀፉ በቀጥታ ለፌደራል ምክር ቤት እንዲመርጡ የፌደሬሽን ምክር ቤት በወሰነው መሰረት እና የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በሚያስፈጽመው ሂደት የተቃውሞ ከስ የጀመረ መሆኑ እና የተከበረው ፍርድ ቤትም በተመሳሳይ ቀን በተመሳሳይ መዝገብ ቁጥር እግድ መስጠቱ ይታወቃል። ስለሆነም በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተመዘገበው እና ህጋዊ ሰውነት ያለው የራያ ራዩማ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ/ራዴፓ/ ማህበራዊ መሰረቱ እና በስፋት የሚንቀሳቀስበት በራያ አከባቢ በመሆኑ አጨቃጫቂ ከተባሉት ቦታዎች መካከል ኮረም አፍላ እና ራያ አላማጣ የምርጫ ክልሎች ፓርቲው እጩ ተወዳዳሪዎች ያቀረበባቸወና የራያ ማነንትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጠያቄ እንዲመለስ የሚታገልላቸው አከባቢዎች ከፊሎቹ ናቸው::

ስለሆነም የተከበረው ፍርድ ቤት የሚሰጠው ማንኛውም ውሳኔ፤ ትእዛዝ እና ብይን ጥቅሙን በቀጥታ የሚነካ በመሆኑ ፓርቲያችን ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር እንዲፈቀድለት ታስቦ የቀረበ ጥያቄ ነው። ምክንያቱም ከቡር ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ማንኛውም ትእዛዝ የአከባቢው ህዝብ በአግባቡ ምርጫ ላይ እንዳይሳተፍ አሉታዊ ተጽእኖ ሊያሳድር ከመቻሉ በላይ አመልካች ፓርቲም የራያ ራዩማ ሕዝብ የራሱን የማንነት ጥያቄ ያለው ነው ብሎ የሚያምን እና ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድርሕገመንግስታዊ መብቱ እንዲጠቀም ዓላማውን ከግብ እንዲያደርስ የሚያግዙት ፓርቲዎች በአከባቢው እንዲሳተፍ ይፈልጋል የሚል ጽኑ እምነት ያለው በመሆኑ ይህ ሳይሆን ቢቀር ፓርቲው በአከባቢው እንዳይሳተፍ የሚያደርጉ ሁኔታዎች በመፍጠርተጨባጭ ጕዳት/practical disadvantage እና የሕግ እና ውጤት ኢተገማችነት(legal uncertainty) የሚፈጥር ይሆናል። በተጨማሪም ውሳኔው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን የቁጥጥር ስርዓት ላይ ገዥ ውሳኔ በማስተላለፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመወዳደር ሁኔታ ሊቀይር የሚችል በመሆኑ ምክንያት እና ጣልቃ ገብ ላይ የማይካስ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል በመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 41 እና በህገ መንግስቱ አንቀጽ 37 መሰረት ጣልቃ ገብተን እንድንከራከር እንዲፈቀድልን ስንል በትህትና አናመልከታለን።

አቤቱታው የቀረበው በትከክል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 92 መስረት አረጋግጫለሁ።

ራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

ጌታቸው ከበደ መረሣ ✍️✍️✍️

አዩማ ደሞል

የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ራዴፓ) ተ/ ፕሬዚዳንት

0-251-116686067/910471538 400h - https://www.facebook.com/profile.php?id=10007880907268

28/02/2026

Agreement Rayan Culture 💚💚💛💛❤️❤️

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Raya Alamata
Addis Ababa
RAYA.COM