Addis Condo Winners

Addis Condo Winners

Share

List of Addis Ababa City Condominium Winners of the year 2015 who were registered in 2005. Use Id and Name for Searching the winners.

03/04/2024

የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ጨረታ የአሸናፊዎች ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እና የአዲስ አበባ ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ቢሮ አስገንብተው ለጨረታ ያቀረቧቸው የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ጨረታ አሸናፊዎች ዝርዝር ከዚህ በታች መመልከት ይቻላል።

ከዚህ በተጨማሪ በአዲስ ልሳን ጋዜጣ የመጋቢት 25/2016 እትም ማየት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን

ሙሉ ዝርዝሩን
https://t.me/c/1175658184/295

21/06/2023

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ1ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል

ቢሮው በከተማዋ ላለፉት አምስት ዓመታት ቆሞ የነበረውን መሬትን በሊዝ ጨረታ የማስተላለፍ ተግባር ዳግም መጀመሩ አስታውሷል።

ከግንቦት 24/2015 ዓ/ም ጀምሮ ለስድስት ተከታታይ ቀናት በይፋ ተከፍቶ አሸናፊዎቹ የተለየውን የ1ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎችን ስም ዝርዝር ይፋ መደረጉን አሳውቋል።

በዚህ ጨረታ ዝቅተኛ ዋጋ የተመዘገበው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሲሆን፣ ይህም በካሬ ሜትር 20 ሺህ ብር ነው፡፡

ከፍተኛው በአራዳ ክፍለ ከተማ ሲሆን በካሬ ሜትር 414 ሺህ ብር እነደሆነ ተገልጿል።

ለ21 ሺህ 636 ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የተሸጠ ሲሆን ከእነዚህ ወስጥ 11 ሺህ 437 ሰነዶች ተሞልተው ሳጥን ውስጥ ገብተዋል።

ሙሉ የጨረታውን አሸናፊዎች ስም ዝርዝር ከላይ በተያያዘው PDF ፋይል ቴሌግራም ላይ ይመልከቱ https://t.me/housinginaddisababa/10070

19/05/2023

የቤት እድለኞችን ውል የማዋዋል ጊዜ እስከ ግንቦት 30/2015 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ

የ14ኛው ዙር የ20/80 እና የ3ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት እድለኞች ውል የማዋዋል ሂደት እሰከ ግንቦት 30/2015 ባሉ የስራ ቀናት /ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ/ መራዘሙን በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቤሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አሳወቀ።

ከጥር 1 ጀምሮ እስከ ግንቦት 7 ተጠቃሚውን ሲያዋውል መቆየቱን ኮርፖሬሽኑ ባወጣው ማስታወቂያ የገለፀ ሲሆን አሁንም በተለያየ ምክንያት ያልተዋዋሉ የጋራ መኖሪያ ቤት እድለኞችን የመጨረሻ እድል ለመስጠት ሲባል እሰከ ግንቦት 30 ማራዘሙን ገልጿል።

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ያልተዋዋለ የቤት እደለኛ ቤቱን እንዳልፈለገው ተቆጥሮ ለኮርፖሬሽኑ ተመላሽ እንደሚሆንም በማስታወቂያው ተገልጿል።

_______________________
በገጻችን የምናቀርባቸውን መረጃዎች በአማራጭነት በቴሌግራም ቻናላችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
👇👇👇👇👇
t.me/housinginaddisababa
እንዲሁም፦

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Abeba?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Addis Abeba