Tesfaye Destaw

Tesfaye Destaw

Share

Personal blog

18/05/2022

ምርጥ ኢትዮጵያዊ

"ዛሬ ኦሮሞም ሆነ ማንም ብሄር አማራ ክልል በሰላም መኖር ይችላል፣ እኔን ጨምሮ በአባቴ እና በእናቴ ቀዬ ሰላሌ መኖር አልችልም" - ዶ/ር አብርሃም ብሩ

በኢትዮጵያ ታሪክ እንደ አማራው ሕግዚያብሔርን የሚፈራ ፍትሃዊ እና አቃፊ ሕዝብ አለ ወይም ነበረ ብል መዋሸት ይሆንብኛል። ብሔር ከብሔር ማበላለጤ ከመሰላችሁም ግድ የለኝም። ስለዚህ ማናችንም ከየትም እንምጣ ከየት ኢትዮጵያን እወዳለሁ የምንል ሁሉ ዛሬ ከዚህ ሕዝብ ጋር መቆም ይጠበቅብናል።

ዛሬ እኔን ጨምሮ ማንም ኦሮሞ ወይም ከሌላ ብሔር የሆነ ሰዉ የትኛዉም የአማራ ክልል ላይ በሰላም ወጥቶ ይገባል። በአንፃሩ ዛሬ እኔ የአባቴና ቤተሰቦቼ ምድር ሰላሌ ላይ ድርሽ ማለት አንደማልችል አዉቃለሁ ምክንያቱም በርካታ ዛቻ በየጊዜው ይደርሰኛል።

በጥቅሉ ለአማራ የማትሆን ኢትዮጵያን የማይፈልጉት አማሮች ብቻ ሳይሆኑ እኔን መሰሎችም በርካታ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን መሆናችንን ሀገር ያዉቅ ዘንድ እፈልጋለሁ። ይህን ስል የትኛዉንም ብሔር ላሳንስ ፈልጌ አይደለም። የእኔ አላማ ስለ ኩሩዉ እና ኃይማኖተኛዉ የአማራ ሕዝብ የሚሰማኝን መግለፅ ነው።

በመጨረሻም እናንተ ከኤዶም ገነት የሚወጣዉ አባይ መፍለቂያ የሆናችሁ ወንድም እህቶቼ ሆይ ደማችሁ ደማችን ነውና በፈተናችሁ ሰዓት እኛ በርካታ ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን አብረናችሁ ነን። አይዟችሁ!!

14/05/2022

ሰባር ዜና

በነገራችን ላይ በሁለት ሺ 14 fb ስገባ ምን እንደሰለቸኝ ታውቃላችሁ??? ሰባር ዜና ነው።

Want your university to be the top-listed University in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Awassa