Maba Tech info
heaven citizens deu 6:4
25/05/2026
17/03/2025
በኢትዮጽያ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ታላቅ ዓመታዊ የአለምአቀፉ ኮንፈረንስ ( ዋራ ቤቴል ) በሰላም ተጠናቀቀ።
የሰላምና መቻቻል ተምሳሌት በሆነችው ሲዳማ ክልል ላለፉት አራት ቀናት ሲካሄድ የነበረው 34ኛው የአለምአቀፉ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ታላቅ አመታዊ ኮንፈረንስ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ምዕመናንና ታላላቅ የሀይማኖት መሪዎችና አባቶች፣ ከተለያዩ ሀገራት፣ ከአጎራባች ዞኖችና ክልሎች አንዲሁም አከባቢዎች የተሳተፉበት በትላንትናው ዕለት በሰላም መጠናቀቁ ተገልጿል።
ቤተክርስቲያኗ የሰው ልጅ በሰብአዊነት በፈሪሃ እግዚአብሔር እንዲያድጉ ኮትኩተው ከማሳደግ ጀምሮ ወደ ዘላለማዊ መንገድ እንዲጓዙ ከማደረጉ ባሻገር በሰብአዊ ድጋፍ አቅም ሌላቸው ወገኖች የምትደግፍ ሲሆን በዚሁ በዘንድሮ ኮንፈረንስም በሲዳማ ክልል ዳሌ ወረዳ ዋራ ሜዳ አከባቢው ማህበረሰብ የጤና አገልግሎት የሚውል ጤና ጣቢያ በቤተክርስቲያኗ ተሰርቶ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱም ታዉቋል።
በኢትዮጵያ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ያካሄደው 34ኛው ዋራ ቤቴል ጉባኤ ከመጋቢት 4 እስከ 7/2017 ዓ.ም በነበረው ኮንፈረንስ ምዕመናኑ ለሀገራችን ሰላምና መረጋጋት ለፈጣሪያቸው ፀሎትና ምልጃ ያደረሱ ስሆን በፕሮግራሙ የኢትዮጵያ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ ቢሾፕ ደጉ ከበደ፣ ቢሾፖች፣ ቄሶች፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቄስ ኃይሌማርያም ጨምረው ከአንድ ሚሊዮን በላይ ምዕመናን ተካፍለዋል።
በተካሄደው በዚሁ አመታዊ ኮንፈረንስ ከዓለም ዙሪያ ሁሉ ለእርሱ የተመረጡት መጥተው በዋራ ሜዳ ላይ የሰማዩን ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስን በሃሌሉያና በእልልታ ደምፅ ከፍ ያደረጉ ሲሆን 👉5306👈አዲስ ነፍሳት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለኃጥአታቸው ስርየት ተጠምቀው ወደ ቤተክርስቲያኗ መቀላቀላቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ዋራ ቤቴል ከሰሜን፣ ከደቡብ፣ ከምስራቅና ከምዕራብ ከተለያዩ አለም ሀገራት ያለዘር፣ ቋንቋና ነገድ ልዩነት በአንድ ልብና ፍቅር የተሰበሰቡ በደሙ የተዋጁ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ልጆች በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራበት ስም ሁሉ በላይ የሆነውን የታላቁን አምላክ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም እየጠሩ በፊቱ ሲሰግዱና ሲዘምሩ፣ በደዌና በአጋንንት የታሰሩ ሲፈቱ፣ ያየንበት፣ ከዚህ ጨለማ ዓለም አንዱን አምላክ ከምያስክድ ክፉ ትምህርት ሰዎች በንስሐ ሲመለሱ የታየበት ሚሊዮኖች በጉጉት የሚጠብቁት ጉባኤ" እንደሆነ ይነገራል።
በኢትዮጽያ #ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን🙏
በቤተክርስቲያናችን ለወንጌልና ለዶክትሪን የምንተጋውን ያህል ለመንፈስ አንድነት እንተጋለን። ቢሾፕ ደጉ ከበደ (በ55ኛ ዓ.ም በአገልጋዮች ሴሚናር ላይ የተናገሩት)
የእውነተኛዋ ቤተክርስቲያን የጅማረዋ እሳት የተለኮሰው ከኢየሩሳሌም ነው የፍጻሜዋ ለንጥቀት የሚያዘጋጅ እሳት የሚወጣው ግን ከኢትዮጵያ ነው ይህም ዓለምን ያጥለቀልቃል። (ቢሾፕ አማዶር)
“ወደዚያም ኮረብታ በደረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ የነቢያት ጉባኤ አገኙት፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል ወረደበት፥ በመካከላቸውም ትንቢት ተናገረ።” (1ኛ ሳሙ 10፥10)
ዓመታዊ የአገልጋዮች ሴሚናር በዋራ ሜዳ ሳስብ ከግብፅ የወጣውን የእስራኤልን ልጆች ከነዓንን አንግበው እየተጓዙ ሳሉ ድፍን አንድ ዓመት በሲና ተራራ እግዚአብሔር አስተምሯቸዋል፤ ለቀጣዩ የአሕዛብን አገራት የሚወርሱበትን መንፈሳዊ ትጥቅና አደራረግ መክሯቸዋል ሕግና ስርዓት ጽፎ ሰጥቷቸዋል፤ ደግሞ ደጋግሞ አሳስቧቸዋል፤ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለእግዚአብሔር ሥራ ብቻ የሚለዩ አገልጋይ ካህናት እንዲሆን አንድን ነገድ ለራሱ ሥራ ብቻ ለይቷል ይህም የሌዊ ልጆች ሆኗል።
እግዚአብሔር እስራኤልን ሲያስተምርም በየምድባቸው አድርጓል ይህንንም ያደረገው በሦስት ተራ ነበር።
1ኛ. ሙሴን ለብቻው (ዘጸ 19፥3 )
2ኛ. ሰባ ሽማግሌዎችን (አገልጋዮችን) (ዘኅ 11፥16) ሌዋውያኑም እንዲሁ
3ኛ. ጠቅላላውን የእስራኤል ሕዝብን (ዘኅ 8፥9)
የእስራኤል ልጆች በእነዚያ በአንድ ዓመት የሲና ተራራ ዙሪያ በቆየባቸው ጊዜአት ከአሥር ጊዜ ያላነሰ ሙሴ ወደሲና ተራራ እንደወጣና ከእግዚአብሔር ጋር ምክክር እንዳደረገ መጽሐፍ ቅዱሳችን ይናገራል። ውጤቱም “በእስራኤል ውስጥ መሪዎች ስለ መሩ፥ ሕዝቡም ነፍሳቸውን በፈቃዳቸው ስለ ሰጡ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ።” መሳ 5፥2 ይላልና።
ኢየሱስም በሥጋ በምድር በተመላለሰበት ዘመን ወደተራራ ይዟቸው እየወጣ ወደእርሱ አቅርቦ በጠንካራ ቃል የመከራቸው እና ዋኖች (ማቴ 17፥1) የተባሉ እንዳሉ እናነባለን። ይህ አድሎ አይባልም ይህ ጌታ ሰውን ከሰው ለይቶ ይመለከታል የሚያስብል የእግዚአብሔር ፍሕታዊነትን የሚጋፋ አይደለም ለአካሉና ለጋራ ዓላማ ጥቅቶችን አስታጥቆ መንፈሱን አፍስሶ ኃይሉን ሞልቶ ከድካሙ አበርትቶ ለብዙኃኑ እንዲተርፉ ያደርጋል።
“.....ሌዋውያኑም ደግሞ በፊታችሁ አለቆች ይሆናሉ፤ በርትታችሁም አድርጉ፥ እግዚአብሔርም መልካም ከሚያደርግ ጋር ይሁን።” 2 ዜና 19፥11 ተብሎ እንደተጻፈው ሌዋውያን በፊታቸው አለቆች እንዲሆኑ ይመርጣል።
የዓለም ኃይማኖት ጓዳው በሙሉ ግራ በተጋባበት በዚህ ዘመን አንድ ንግግር መናገር ቀርቶ አንድ የጋራ ስም ይዞ መቀጠል ባልቻሉበት የባቢሎንን የግንብ ሠራተኞችን ቋንቋቸው ያደባለቀ አምላክ እጁ ዛሬም አለችበት እላለሁ። ሰንሰለታማ የአመራር አሠራርን ተዋረድ የማይቀበሉ ሰማይ ተኮር ሳይሆን ገንዘብ ተኮር በሆነበት ዘመን ይህችን ቤተክርስቲያን ከአሜሪካ እስከ አውስትራሊያ ከደቡብ አፍርቃ እስከኢስያ በዓለም በአራቱም ማዕዘናት ተበታትነው የሐዋርያትን እውነት በመስዋዕትነት ተሸክመው እየሮጡ ያሉ ከእሳት የተነጠቁ ትንታግ (ዘካ 3፥2) አገልጋዮች የእርስበርስ መታያ ቀኑ እነሆ ደረሰ ይሄውም በዋራ ሜዳ ላይ ቁጥራቸው አይገመትም አዲስ ለመስዋዕት የሚቀቡ ብዙ ኢያሱዎች አሉ። “የሰማይን ሠራዊት መቍጠር የባሕርንም አሸዋ መስፈር እንደማይቻል፥ እንዲሁ የባሪያዬን የዳዊትን ዘርና የሚያገለግሉኝን ሌዋውያንን አበዛለሁ።” (ኤር 33፥22) የሚል ቃል ኪዳን ስላለው ገና ብዙ ለእግዚአብሔር ሥራ ማቃቸውን ጨርቃቸውን ጥለው የሚለዩ አሉ።
ምን እንደሚል ባላውቅም እድገቷ አስፈሪ ነው፤
Click here to claim your Sponsored Listing.
Telephone
Website
Address
Awassa
TRAININGCENTER