Omo Bank S.Co Labor Union
መደራጀት ሃይል እና ጥቅም ነው!! Being organized is power and benefit!!
15/07/2025
የገቢ ግብር መነሻ ገቢ ወደ 5,000 ብር ከፍ እንዲል ጥያቄ ቀረበ
| የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ፣ የኑሮ ውድነትን ታሳቢ በማድረግ የገቢ ግብር መነሻ ገቢ ከ2,000 ብር ወደ 5,000 ብር ከፍ እንዲል ጠንካራ ጥያቄ ቀርቧል።
በአሁኑ ረቂቅ አዋጅ መሰረት፣ ከ2,000 ብር በላይ በሚገኝ ገቢ ላይ 15 በመቶ ግብር እንዲከፈል ሀሳብ ቀርቧል።
ይህ የተገለጸው በፓርላማው የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተካሄደው ውይይት ላይ ሲሆን፣ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ፣ የአዋጁ ማሻሻያ የመንግስትን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።
ከግብር ነፃ የሚሆነው ገቢ አሁን ባለው ማሻሻያ በ300% በማደግ ወደ 2,000 ብር ከፍ እንዲል የተደረገ ሲሆን፣ ከፍተኛው 35% ግብር የሚያርፍበት ገቢ ደግሞ ወደ 14,000 ብር ከፍ እንዲል ሆኗል።
በውይይቱ ወቅት፣ የገቢ ግብር መነሻው ከአምስት ሺህ ብር ጀምሮ እንዲሆን፣ ለአካል ጉዳተኞች በተለየ መልኩ ግብር እንዲቀነስ፣ እንዲሁም በተለያዩ የሙያና የንግድ ዘርፎች አንፃር በደንብ እንዲታይ የሚሉ አስተያየቶች ቀርበዋል።
#ቅዳሜገበያ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the public figure
Address
Awassa