Learning
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Learning, Digital creator, Bahir dar, Bahir Dar.
20/05/2025
ኢሳያስ አፈወርቂ ስለ አማራ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ
19/04/2025
ሊረዷችሁ የሚችሉ ያልተፃፉ 22 ማህበራዊ ህጎች፡
1. አንድን ሰው በተከታታይ ከሁለት ጊዜ በላይ አይደውሉ። ጥሪዎን ካላነሱ፣ የሚያከናውኑት አስፈላጊ ነገር እንዳለ ያስቡ፤
2. የተበደራችሁትን ገንዘብ፣ የተበደራችሁት ሰው ከማስታወሱ ወይም ከመጠየቁ በፊት መልሱ። ይህ ታማኝነትዎንና ባህሪዎን ያሳያል። ይህ በዣንጥላ፣ እስክሪብቶና የምሳ ዕቃ ላይም በተመሳሳይ መልኩ ይሠራል።
3. አንድ ሰው ምሳ/እራት ሲጋብዝዎት፣ በሜኑው ላይ ያለውን ውድ ምግብ በጭራሽ አይዘዙ።
4. ‘ኦህ፣ ገና አላገባህም/ሽም?’ ወይም ‘ልጆች የሉህም/ሽም’ ወይም ‘ለምን ቤት አልገዛህም/ሽም?’ ወይም ‘ለምን መኪና አትገዛም/ዢም?’ አይነት አግባብ ያልሆኑ ጥያቄዎችን አይጠይቁ። በፈጣሪያችሁ! ይህ የእናንተ ችግር አይደለም፤
5. ከኋላችሁ ለሚመጣው ሰው ሁል ጊዜ በሩን ክፈቱ። ወንድም ይሁን ሴት፣ ትልቅም ይሁን ትንሽ ለውጥ የለውም። በህዝብ ፊት ሰውን በአግባቡ በመያዝ ትንሽ አትሆኑም፤
6. ከጓደኛ ጋር ታክሲ ከወሰዱና እሱ/እሷ አሁን ከከፈለ/ች፣ በሚቀጥለው ጊዜ ለመክፈል ይሞክሩ፤
7. የተለያዩ አስተያየቶችን አክብሩ። ለእናንተ 6 የሆነው ነገር በተቃራኒ ላለ ሰው 9 ሆኖ እንደሚታይ አስታውሱ። በተጨማሪም፣ ሁለተኛ አስተያየት ለአማራጭ ጥሩ ነው፤
8. ሰዎች ሲያወሩ በጭራሽ አያቋርጧቸው። ሀሳባቸውን ገልጸው እንዲጨርሱ ፍቀዱላቸው። 'ሁሉን ስማ፣ ሁሉን አጣራ' እንደሚባለው፤
9 . አንድን ሰው ብትቀልዱበትና እሱ በቀልዱ እየተደሰተበት ካልሆነ ወዲያውኑ አቁሙ፤ ዳግመኛም አታድርጉት። ይህን መቀጠል ግዴለሽ መሆንዎን ያሳያል፤
10 . አንድ ሰው ሲረዳችሁ “አመሰግናለሁ” ይበሉ።
11. በአደባባይ አመስግኑ። በግል ተቹ፤
12. በአንድ ሰው የሰውነት ክብደት ላይ አስተያየት ለመስጠት የሚያበቃ ምንም ምክንያት የለም ማለት ይቻላል። ዝም ብለው፣ “በጣም ታምራለህ/ያምርብሻል” ይበሉ። ስለ ክብደት መቀነስ ማውራት ከፈለጉ፣ እነሱ ራሳቸው ያነሱታል፤
13. አንድ ሰው በስልካቸው ላይ ፎቶ ሲያሳያችሁ፣ ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ አታንሸራትቱ። ቀጥሎ ምን ሊኖር እንደሚችል አታውቁም፤
14. የስራ ባልደረባችሁ የዶክተር ቀጠሮ እንዳለው/ላት ከነገረዎት/ች፣ ለምን እንደሆነ አይጠይቁ፣ ዝም ብለው "ደህና እንደምትሆን/ኚ ተስፋ አደርጋለሁ" ይበሉ። የግል ህመማቸውን እንዲነግሯችሁ በሚያስገድድ አላስፈላጊ ሁኔታ ውስጥ አታስገቧቸው። እንዲያውቁ ከፈለጉ፣ ያለ የእርስዎ ጠያቂነት ያደርጉታል፤
15. የጽዳት ሰራተኛውን እንደ ዋና ሥራ አስፈፃሚው (CEO) በተመሳሳይ አክብሮት ይያዙ። ከእናንተ በታች ላለ ሰው ምን ያህል ባለጌ መሆን እንደምትችሉ በማሳየት ማንንም አታስደንቁም፤ ነገር ግን በአክብሮት የምትይዟቸው ከሆነ ሰዎች ያስተውላሉ፤
16. አንድ ሰው በቀጥታ እያናገረዎት ከሆነ፣ ስልክዎን ማፍጠጥ የትህትና የጎደለው ነው፤
17. እስካልተጠየቁ ድረስ በጭራሽ ምክር አይስጡ፤
18. ከረጅም ጊዜ በኋላ ከአንድ ሰው ጋር ሲገናኙ፣ እነሱ ስለእሱ ማውራት ካልፈለጉ በስተቀር፣ ስለ እድሜያቸውና ደሞዛቸው አይጠይቋቸው፤
19. ነገሩ በቀጥታ የማይመለከታችሁ ከሆነ በራሳችሁ ጉዳይ ላይ አተኩሩ - ዝም ብላችሁ ጣልቃ አትግቡ፤
20. መንገድ ላይ ከየትኛውም ሰው ጋር እያወሩ ከሆነ የፀሀይ መነፅርዎን ያውልቁ። ይህ የአክብሮት ምልክት ነው። ከዚህም በላይ፣ የአይን ለአይን ግንኙነት እንደ ንግግራችሁ ሁሉ አስፈላጊ ነው፤
21 . በድሆች መካከል ስለ ሀብታችሁ በጭራሽ አታውሩ። በተመሳሳይ፣ ልጅ በሌላቸው ሰዎች መካከል ስለ ልጆቻችሁ አታውሩ።
22 . ጥሩ መልዕክት ካነበቡ በኋላ "ስለመልዕክቱ አመሰግናለሁ" ለማለት ይሞክሩ።
ማድነቅ/ማመስገን የሌላችሁን ነገር ለማግኘት በጣም ቀላሉ መንገድ ነው።
እወዳችኋለሁ !
ተዋነይ - Tewanay
19/04/2025
“ሰውን በገንዘብ የሚሸጥ ትውልድ ይሁዳን ማማት አይችልም” ብጹዕ አቡነ አብርሃም
የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት በባሕር ዳር ከተማ ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ታስቦ ውሏል፡፡
በበዓሉ ላይ ትምህርተ ወንጌል የሰጡት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የባሕር ዳር እና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ አብርሃም በዓለ ስቅለት የማይሞተው የሞተበት፤ በሞቱ ሞትን የገደለበት፤ ለሰው ልጆች ነጻነትን ያወጀበት፤ የታሰሩት የተፈቱበት፤ የራቁ የቀረቡበት፤ የሰው ልጅ ጥንተ ጠላት ዲያቢሎስ የታሰረበት እና የወደቀበት ነው ብለዋል፡፡
ሰዎች ለገንዘብ ሲገዙ የማያደርጉት የለም ያሉት ብጹዕነታቸው ጻድቁን ያስገድላሉ፤ ንጹሕ ደምም ያፈሳሉ ነው ያሉት፡፡ ሰዎች ለእግዚአብሔር ሲገዙ ፍቅርን እና ርህራሄን ገንዘባቸው ያደረጋሉ ብለዋል፡፡
ባላቸው የተቸገረን ይረዱበታል፤ የሌላ አይመኙም፤ በተሰጣቸው እና ባላቸው ይጠቀሙበታል፤ የተራበውን ይመግቡበታል፤ የተራቆተውን ያለብሱበታል ነው ያሉት፡፡ ይሁዳ ከገንዘብ ፍቅሩ የተነሳ ጌታውን አሳልፎ መስጠቱን ገልጸዋል፡፡
ይሁዳ ጌታውን አሳልፎ ከሰጠ በኋላ ተጸጽቶ፤ ንፁሑን አሳልፌ ሰጥቻለሁ፤ በድያለሁ ብሏል ያሉት ብጹዕነታቸው ጊዜ ካለፈበት በኋላ ጸጸት መልካም አይደለም ብለዋል፡፡
ንስሐ ጊዜው ሳያልፍ ነው፤ የንስሐ ጊዜ ዛሬ ነው፤ የጸጸት ሰዓት ዛሬ ነው፤ ሁሉ ነገር ካፈ በኋላ ጸጸት ትርጉም የለሽ ነው፤ በጊዜው ካልተጸጸቱ ዋጋ የለውም ነው ያሉት፡፡
ጻድቅን አሳልፎ መሰጥተን ለምንም እንደማይጠቅም የይሁዳ ድርጊት ያስተምራል ብለዋል፡፡ በአላስፈላጊ ምኞት ሰክሮ የሚሮጥን፤ በንጹሐን ደም ተሸጋግሮ ባለሀብት ለመኾን የሚጥር ሰው ቢኖር እርባና እንደሌለው ከይሁዳ ይማር ነው ያሉት፡፡
ሁላችንም በድለናል፤ አጥፍተናል፣ በድያለሁ ብለን መጸጸት፤ ንስሐ መግባት አለብን ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡
እንደ ይሁዳ ሁሉ ዛሬም የንፁሕ ደም የሚያፈስሱ፤ ንጹሕን አሳልፈው የሚሰጡ፤ እውነተኛውን ጻድቁን የሚያስገደሉትን ኢትዮጵያ መታቀፏን ገልጸዋል፡፡
ንጹሕ ደም ማፍሰስ፤ ጻድቁን አሳልፎ መስጠት ምንም እንደማይጠቅም ከይሁዳ እንማር፤ በደላችንን አምነን አምለካችን ኾይ ማረን እንበለው ብለዋል፡፡
ይሁዳ ለራሱ ቢጎዳም ለእኛ ግን አስተምሮናል ነው ያሉት፡፡ እኛ ከይሁዳ መሻል አለብን፤ ዛሬ ላይ እንደ ይሁዳ ሰው የሚሸጥበት ዘመን ደርሰናል፤ "ሰውን በገንዘብ የሚሸጥ ትውልድ ይሁዳን ማማት አይችልም" ብለዋል። ከይሁዳ የተሻለ ትውልድ አልተገኘም፤ ከልብ ጸጸት የሌለበት፤ የከንፈር ብቻ ጽድቅ ያለበት ዘመን ነው ብለዋል፡፡
ሕሊናቸውን ለእግዚአብሔር የተሰጡ፤ ከዓለም የተገለሉ፣ ደጋግ ሰዎች ስላሉ በቸርነቱ እንኖራለን ነው ያሉት፡፡
በድያለሁ የሚለውን እንመን ያሉት ብጹዕነታቸው አምላክ በድለነው ሳለ ለእኛ መከራ ተቀብሏል፤ እኛ ግን በድለንም በድለናል አንልም ብለዋል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ግርጌ እናት ሰጥቶናል፤ ያለ እናት አልተወንም ነው ያሉት፡፡ ስለ ሰላም እንጸልይ፤ ስለ ሀገራችን እንጸልይ፤ ክርስቲያን ስለ ዓለም ሁሉ ይጸልያልና ስለ ዓለም ሁሉ እንጸልይ፤ የተፈናቀሉትን እንዲመለሱ፤ ሰላም እንዲነግስ፤ ንጹሕ ደም መፍሰስ በቃ እንዲለን ተግተን እንጸልይ ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡
Via: አሚኮ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Bahir Dar
BDU