Cheta Woreda Communication

Cheta Woreda Communication

Share

Cheta woreda communication

24/05/2026

"373 መምህራን የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ወስደዋል" :- የካፋ ዞን መምህራን ማህበር

የካፋ ዞን መምህራን ማህበር የመምህራንን መብት እና ጥቅማ-ጥቅም የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡

የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ወንድሙ፣ ማህበሩ ከ13 ሺህ በላይ አባላትን ያቀፈ አንጋፋ ማህበር ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ማህበሩ ከተቋቋመለት አላማ አንፃር የመምህራንን መብት እና ጥቅማ-ጥቅም የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የትምህርት ጥራትን የማረጋገጥ ሥራዎች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም ነው የገለጹት፡፡

የመምህራን የደረጃ ዕድገት፣ የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ እንዲሁም ሌሎች የትምህርት ማሻሻያ ላይ ማህበሩ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ በዞኑ 373 መምህራን ተደራጅተው የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እየተሰጣቸው እንደሆነም ገልፀዋል።

በቀጣይ ተደራጅተው እየጠበቁ ያሉ መምህራን የመሬት ባለቤት እንዲሆኑ ማህበሩ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

ከማዘጋጃ ከተሞች ውጭ ያሉ መምህራንን በሚመለከትም የአከባቢው አስተዳደር እና ህዝብ ምቹ መኖሪያ እንዲያዘጋጁላቸው ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

ማህበሩ ከዞኑ አስተዳደር ጋር ባለው መልካም ግኑኝነት ችግሮችን በውይይት የመፍታት ልምድ እየዳበረ መጥቷል ብለዋል፡፡

የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ የበርካታ አካላትን ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው ያሉት አቶ ተመስገን "የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው መምህር ነው" ብለዋል፡፡

በዚህም መሠረት መምህራን የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ የበኩላቸውን ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙም ነው የገለጹት፡፡

በቀጣይ ቀናት ለክልላዊና ብሔራዊ ፈተናዎች ተማሪዎችን የማዘጋጀት ሥራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

.4

የጨታ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት።

ወታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡክና ቴሌግራም ገፆቻችን ይከታተላሉ ፣ይወዳጁ👇👇👇👇👇????

በፌስቡክ፦https://www.facebook.com/profile.php?id=100091368031356

በቴሌግራም፦https://t.me/C12g6/1057?single

በቲክቶክ፦https://vm.tiktok.com/ZMHtnCGMKnVKa-Th2vR/

Photos from Cheta Woreda Communication's post 23/05/2026

የጋዜጠኛ ፍቅሩ በላይ የቀብር ስነ-ስርዓት በቦንጋ ደብረ-ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተፈፀመ

በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የቦንጋ ቅርንጫፍ ጣቢያ ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኞ ፍቅሩ በላይ የቀብር ስነ-ስርዓት ቤተሰቦቹ፤ ወዳጅ ዘመዶቹ እና የስራ ባልደረቦቹ በተገኙበት በቦንጋ ደብረ-ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

ዝግጅት ክፍላችን በጋዜጠኛ ፍቅሩ በላይ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹ፤ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለስራ ባልደረቦቹ መጽናናትን ይመኛል።

Photos from Cheta Woreda Communication's post 22/05/2026

የከፋና የቦንጋ ማንነት: - የተፈጥሮ ልዕልና እና የሰብዓዊነት ውብ ቅኔ

ወደ ጥንታዊው የከፋ ምድርና ወደ ውቢቷ ቦንጋ ከተማ የሚደረግ ጉዞ ለነፍስ ልዩ የሆነ የዕርጋታና የጥበብ ስሜት ይሰጣል። ይህ ታሪካዊ ቀጠና በካርታ ላይ የሰፈረ መልክዓ-ምድር ብቻ አይደለም። ጥቅጥቅ ያሉ የዝናብ ጫካዎች (Rainforest)፣ የሉዓላዊነት ኩራትና የሰው ልጅ ረቂቅ ባህል በአንድነት የከረሙበት የኢትዮጵያዊነት ሕያው ምስክር እንጂ። የከፋና የቦንጋ እውነተኛ ማንነት ከተፈጥሮ ልግስና ጋር ተስማምቶ ከመኖር የሚቀዳ የጽናት፣ የትሕትና እና የሰላም ድንቅ ውህደት ነው። ይህቺ ምድር የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር በሰላም ሲኖር ምን ያህል ሥልጣኔና ክብረ-ነገር መገንባት እንደሚቻል ለዓለም የሚያስተምር ሕያው መድረክ ናት።

የዚህቺ ምድር የሕይወት ትርታ የሚጀምረው ከአረንጓዴው ጫካ፣ ከለመለሙ ሸለቆዎችና ከኮረብቶቿ ዘላለማዊ ግርማ ነው። ከቦንጋ ከፍታዎች ላይ ቆመው ቁልቁል ሲመለከቱ አካባቢው በጭጋግና በልምላሜ የተሸለመ ውብ የጥበብ ሥራ ይመስላል። በጫካው ጥላ ሥር የሚፈሱት ፏፏቴዎችና የወንዞች ድምፅ ከተፈጥሮ ረጋ ያለ እስትንፋስ ጋር ተቀላቅሎ ለየት ያለ የነፍስ ዕረፍት ይሰጣል። ማለዳ በቦንጋ ምድር ሲቀሰቀስ የሚነፍሰው ንጹሕ አየርና የማኅበረሰቡ ንቁ የሥራ ስሜት ተደምሮ በእያንዳንዱ ጎዳና ላይ አዲስ ተስፋንና ሕይወትን ይረጫል። ይህ የተፈጥሮ በረከት ከሕዝቡ ጥንታዊ የሞራል ልዕልና ጋር ፍጹም የተሳሰረ በመሆኑ ምድሪቱ የሰውና የተፈጥሮ የፍቅር መኖሪያ ሆና ትታያለች።

የከፋ ሕዝብ በረጋ ማንነቱ፣ በትሕትናውና ለእንግዳ ባለው ልባዊ ፍቅር ይታወቃል። ሰውን በሰውነቱ ብቻ አክብሮ የመቀበል፣ ለእንግዳ የልብ ጓዳውን በሰፊው የመክፈትና በቅንነት የማስተናገድ ትውፊት የሕይወታቸው ትልቁ መሠረት ነው። ወደ ቦንጋ የመጣ ሰው ፈጽሞ በምድሪቱ ላይ ባዕድ አይሆንም የሕዝቡ ደግነትና የልብ ሙቀት ሁሉንም እንደ እናት እቅፍ አሙቆ ይቀበላልና። በየመንደሩ በሚታየው የጎረቤት ፍቅርና መከባበር ውስጥ የሚስተዋለው ትልቁ እውነት ያ የማይበገር የአንድነት መንፈስ ነው። ይህ ማኅበረሰባዊ ትስስር የከፋን ምድር ለማንኛውም ዘመናት ውሽንፍር የማይበገር ጽኑ ግንብ አድርጎታል።

የቦንጋን ሕይወት ይበልጥ ማራኪና በማኅደር ውስጥ የማይረሳ የሚያደርገው በማኅበረሰቡ ውስጥ ያለው ጥልቅ የሰላምና የፍትሕ እሴት ነው። ለዘመናት የጸኑት የባህላዊ ዳኝነትና የሽምግልና ሥርዓቶች የሰው ልጅ ያለ ኃይልና ያለ መሣሪያ በቃል-ኪዳንና በትልቅ የሞራል ልዕልና እንዴት ፍጹም ሰላምን ማስፈን እንደሚችል በተግባር ያሳያል። በትላልቆቹ የዛፍ ጥላዎች ሥር የሚቀመጡት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የሚሰጡት ውሳኔ ከውኃ የጠራ ከዓለት የጠነከረ ነው። እዚያ አደባባይ ላይ ክህደትና ውሸት ፈጽሞ ቦታ የላቸውም ሰው ሰውን የሚያከብረው በውስጡ ባለው ማኅበራዊ ቃል-ኪዳንና በሰውነቱ ብቻ ነው።

ሲመሽና የቦንጋ መብራቶች በአረንጓዴው ሸለቆ ውስጥ እንደ ከዋክብት ፈገግ ሲሉ ከየቤቱ የሚሰማው የሰዎች ሳቅና ጨዋታ ሌላ የውበትና የፍልስፍና ምዕራፍ በይፋ ይከፈታል። እዚያ ሞቅ ባለ ማዕድ ዙሪያ የጥንቱ የጀግንነት ታሪክ በጥልቀት ይተረካል፣ የነገው የብልጽግና ራዕይ በስልት ይወጠናል ጥንታዊው ዕውቀትና የሕይወት ፍልስፍና ደግሞ ለልጆች ይተላለፋል። የቦንጋ ወጣቶች የፈጠራ ብቃት ንቁ የሥራ ተነሳሽነትና የተፈጥሮው ልምላሜ ከተማዋን ሁልጊዜም ወጣት፣ ሕያውና ተስፋ የተሞላች ያደርጋታል።

ዛዲግ አብርሃ
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት

የጨታ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት።

ወታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡክና ቴሌግራም ገፆቻችን ይከታተላሉ ፣ይወዳጁ👇👇👇👇👇????

በፌስቡክ፦https://www.facebook.com/profile.php?id=100091368031356

በቴሌግራም፦https://t.me/C12g6/1057?single

በቲክቶክ፦https://vm.tiktok.com/ZMHtnCGMKnVKa-Th2vR/

21/05/2026

የተቋማችንን ስምና መለያ በመጠቀም ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ስለ ስራ ግብር ቅናሽ ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው፡፡

ስለተቋሙ ስራዎች ትክክለኛ መረጃዎችን የገንዘብ ሚኒስቴር የማህበራዊ ሚዲያ ገፆችን በመከተል ማግኘት ትችላለችሁ፡፡

መረጃው የገንዘብ ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ገፅ ነው።

የጨታ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት።

ወታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡክና ቴሌግራም ገፆቻችን ይከታተላሉ ፣ይወዳጁ👇👇👇👇👇????

በፌስቡክ፦https://www.facebook.com/profile.php?id=100091368031356

በቴሌግራም፦https://t.me/C12g6/1057?single

በቲክቶክ፦https://vm.tiktok.com/ZMHtnCGMKnVKa-Th2vR/

20/05/2026

በሀገር አቀፍ ደረጃ የፋይዳ መታወቂያ ተመዝጋቢዎች ቁጥር 43 ሚሊየን ደረሰ

በኢትዮጵያ የብሔራዊ መታወቂያ ፋይዳ ተመዝጋቢዎች ቁጥር 43 ሚሊየን መድረሱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ዲጂታል መታወቂያን ከ100 በላይ በሚሆኑ የመንግሥትና የግል ተቋማት አገልግሎቶች ጋር በማስተሳሰር ዜጎች መረጃን መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ አስችሏል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት እንዳመላከቱት፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 20 ሚሊየን ዜጎች ለብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝግበዋል፡፡

ይህም በመላው ሀገሪቱ የብሔራዊ መታወቂያ ፋይዳ ተመዝጋቢዎችን ቁጥር 43 ሚሊየን እንዳደረሰው ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በዲጂታል ኢኮኖሚ ወሳኝ የሆነውን የሞባይልና የኢንተርኔት ተጠቀሚዎችን ቁጥር ለማሳደግ በተሰራው ሥራ በሀገሪቱ በአጠቃላይ 97 ሚሊዮን ዜጎች የሞባይል ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

ከዚህ ውስጥ 84 ሚሊዮኑ በኢትዮ ቴሌኮም፣ 13 ሚሊዮኑ ደግሞ በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኩል የተመዘገቡ ናቸው ብለዋል፡፡

የኢንተርኔት ተደራሽነት ለማሳደግ በተሰራው ሥራ በኢትዮ ቴሌኮም 49 ነጥብ 9 ሚሊዮን፣ በሰፋሪኮም ኢትዮጵያ 11 ነጥብ 1 ሚሊየን በድምሩ 61 ነጥብ 1 ሚሊየን ዜጎች የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል።

በኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠንና ዜጎች አስተማማኝ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡

#ኢ.ፕ,ድ

Want your business to be the top-listed Media Company in Bonga?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Kafa Cheta
Bonga