Getasew Atnafu

Getasew Atnafu

Share

Collaborative effort for common results

11/04/2023

👉ስልጣናቸውን ተጠቅመው
ቤቱን እላዩላይ ሲያፈርሱበት
ፎክሮ አፀፋውን የሚመልስ እንጂ
👉መንገድ ላይ ወጥቶ የሚያለቅስ
አማራ የለም!!

11/04/2023

#በኦሮሚያ ቤተክርስቲያን አሁንም በአስገዳጅ ተፅዕኖ ውስጥ ነች።

Photos from Getasew Atnafu's post 10/04/2023

#የልዩ ሃይል ጉዳይ ለተቃውሞ መነሻ ክብሪት ሆነ እንጅ፣ እውነት ለመናገር፣ የአማራ ህዝብ ተቃውሞ መነሻ ከዚህም ከፍ ያለ ነው።

# ዜጎች በብሄራቸው ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉ፣ እላያቸው ላይ ቤታቸው ሲፈርስ፤ ብሄርተኝነት እያቆጠቆጠ: ኢትዮጵያዊ ወገናዊነት እየተዳከመ ሲመጣ እንዲሁም የኑሮ ውድነቱ፣ ስራ አጥነቱና ዝርፊያው እየተባባሰ ሲሄድ ወዘተ፣ የህዝቡ ብሶት ገንፍሎ ቢወጣ የሚጠበቅ እንጅ የሚደነቅ አይደለም:: ሁኔታዎች ሌላውንም ብሄር ወደ አደባባይ የሚያስወጡ ናቸው::

መንግሥት ከተሰቀለበት ንስራዊ የትዕቢት ማማ ወርዶ ፖለቲካዊ ርፎርም ለማድረግ ቁርጠኛ ይሁን:: ጥቂቶች የሚዘውሯት ሳትሆን አገር የህዝብ ትሁን:: መንግሥት በተደጋጋሚ ችግር ፈጥሮ እባካችሁ አረጋጉት እያለ ከመማጸን ይልቅ ለምንድነው በተደጋጋሚ ፋወል የምሰራው ብሎ እራሱን ይጠይቅ:: እንደማየው ብልጽግና ሻግቷል ወይም ህወሃትን በማሸነፉ በትዕቢት ተወጥሯል:: በዚህ ዘመን የህዝብን ልብ ማርኮ እንጅ የህዝብን እግር አንበርክኮ ለረጅም ጊዜ መግዛት አይቻልም:: አሁንም ወደ ውስጣችሁ አይታችሁ ቶሎ ካልተለወጣችሁ: የህዝብ ወጀብ ባላሰባችሁት ጊዜና ቦታ ጠራርጎ ይወስዳችሁዋል:: ይህ ምልክት ነው:: መግቢያ ነው:: ምዕራፍ አንድ: ሁለት እያለ እንዳይቀጥል ፍሩ::

Fasil yenalem

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Gondar?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address

Wogeda
Gondar
SIMADA