WFA Hoo-lataa O2

WFA Hoo-lataa O2

Share

WFA

28/04/2026

፡-

ሃይማኖትን በአፍ አምኖ በልብ መካድ እንደ አርዮስ መሆን ነው፤ በልብ አምኖ በአፍ ቢክዱም እንደ ጴጥሮስ መሆን ነው፤ ቅዱስ ጴጥሮስ ንስሐ ባይገባ ኖሮ የልቡ እምነት ባልጠቀመውም ነበር፡፡ እንግዲህ የልብን በአፍ የአፍን በልብ አንድ አድርጎ፤ አስተባብሮ ማመን ይገባል፡፡ አመንኩ በዘነበብኩ፤ በተናገርኩት አመንኩ ብሎ ክቡር ዳዊት ተናግሯል (መዝ.115፡1)፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው አፍኒ ዘየአምን ቦቱ ይጸድቅ ወልብኒ ዘየአምን ቦቱ የሐዩ፤ አፉን ልቡን አንድ አድርጎ በእውነት ያመነ ሰው ይድናል እንዳለ (2ኛ.ቆ.4፡13)፡፡
በልብ ማመን እንደምን ነው ቢሉ በሃይማኖት ፀንተን የክርስቶስን ፍቅር የሚያስጥለን ማንም የለም ብሎ አምኖ ፀንቶ መኖር ነው፡፡ መኑ የኃድገነ ፍቅሮ ለክርስቶስ ሕማምኑ፤ ምንዳቤኑ፤ ረሀብኑ፤ ዕርቃንኑ፤ መጥባሕትኑ፤ ጻዕርኑ፤ የክርስቶስን ፍቅር ማን ያስተወናል፤ ሕማም ነውን? መከራ ነውን? እሳት ነውን? ረሀብ ነውን? መታረዝ ነውን? በሰይፍ መቆረጥ ነውን? ጭንቅ ነውን? ብሎ ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረ (ሮሜ. 8፡33-36)
የቀና ሃይማኖት ካለን ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚችል የለም፡፡ እመኒ አፍርሑኒ በስደት ውስተ መካናት ርሑቃት ወእመኒ ወደዩኒ ውስተ እሳት፡፡ ወደ ሩቅ ቦታ እናሳድድሃለን፤ ወደ እሳትም እንጥልሃለን ቢሉኝ ለአናብስት አሳልፈው ቢሰጡኝ፤ ወደ ጥልቅ ባሕርም ቢያሰጥሙኝ፤ እጄን እግሬንም በሰይፍ ቢቆርጡኝ፤ ልዩ ልዩ በሆነ ሥቃይ ቢያሰቃዩኝ፤ እኔ ሃይማኖቴን አልክድም ልቡናዬ በቃለ እግዚአብሔር፤ በኢየሱስ ክርስቶስ የጸና ነው እንዳለ ሳዊሮስ፡፡ ስለዚህ የክርስቶስን ፍቅር ሊያስተወን የሚችል የለም፡፡
ክርስቲያን የሆነ ሰው ሁሉ ሃይማኖቱን ተምሮ ካወቀ በኋላ በጎውን ሥራ ካልሠራ እንደ አጋንንት መሆኑ ነው፡፡ ወአንተሰ ተአምን ከመ አሐዱ ውእቱ እግዚአብሔር ወሠናየ ትገብር አጋንንትኒ የአምኑ፡፤ ኪያሁ ወይሰግዱ እንዳለ ያዕቆብ (ያዕ.2፡19)፡፡
ዮሐንስ አፈ ወርቅም እመቦ ብእሲ ዘቦቱ ሃይማኖት ወምግባሩሰ እኩይ ውእቱ ናሁ ክህደ ሃይማኖቶ ወአጽአለ ሕገ ተምህሮ፤ ሃይማኖት ያለው ሰው ቢኖር ምግባሩ ክፉ ከሆነ እነሆ ሃይማኖቱን ካደ የትምህርትንም ሕግ አሰደበ ብሏል፤ ምግባርም ሠርቶ ሃይማኖትን ካልተማረ ካላወቀ በምግባር ብቻ ሊጸድቅ ክርስቲያን ሊባል አይቻለውም፡፡ ሃይማኖት ርትዕት ትእኅዝ ስነ ምግባራት፤ ወዘእንበሌሃሰ ኢይትከሃሎ ለክርስቲያናዊ ይሰመይ ክርስቲያነ፤ የቀናች ሃይማኖት የምግባርን መልክ ትይዛለች፤ በምግባር መልክ ትገለጻለች፤ እንዲህ ካልሆነ ግን ክርስቲያም ተብሎ ሊጠራ አይገባውም እንዳለ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፡፡
በጎ ምግባር የሌለው ሃይማኖት፤ ነፍስ የተለየው ሥጋን ይመስላል፤ ነፍስ የተለየው ሥጋ መውረድ መውረድ መውጣት፤ መብላት መጠጣት፤ ተግባረ ሥጋ ተግባረ ነፍስን መሥራት እንደማይችል ሁሉ በጎ ሥራም የሌለው ሃይማኖት ተራራ ማፍለስ፤ ድውይ መፈወስ ተአምራትን ሁሉ ማድረግ አይቻለውም፡፡ ከመ ሥጋ ዘአልቦ መንፈስ ውእቱ ከማሁ ሃይማኖትኒ እንተ አልባቲ ምግባረ ሠናይ ምውት ይእቲ ለሊሃ፤ ነፍስ የሌለው ሥጋ የሞተ እንደሆነ ሁሉ በጎ ምግባር የሌላት ሃይማኖትም በራስዋ የሞተች ናት (ያዕ.2፡17)፡፡
በአፍ ማመን እንደምን ነው ቢሉ እነሆ ክርስቲያን የሆነ ሰው ሁሉ ስለ ሃይማኖቱ ማናቸውንም ነገር ሳይፈራና ሳያፍር ገልጦ መናገር ይገባል፡፡
ወልደ እግዚአብሔር በአባቱ ፊት ልጄ ወዳጄ ብሎ እንዲያምነው እንዲወደው፤ ክቡር ዳዊት ወእነግር ስምዓከ በቅድመ ነገሥት ወኢይትኃፈር ብሎአል (መዝ.118፡45-46)፡፡ ከአላውያን ነገሥታት ፊት ምስክርነትህን እናገራለሁ አላፍርም አልፈራም ብሎ እንደተናገረ ዮሐንስ መጥምቅ የሄሮድስን የሄሮድያዳን ፊት፤ ኤልያስ የአክአብን የኤልዛቤልን ፊት፤ ሠለስቲ ደቂቅ የናቡከደነጾርን ፊት እንዳላፈሩ፡፡ ጌታም በወንጌል ወለዘሰ አምነኒ በቅድመ ሰብእ አነኒ አአምኖ በቅድመ አቡየ ዘበሰማያት፤ በሰው ፊት ያመነኘን እኔም በአባቴ ፊት ልጄ ወዳጄ እለዋለሁ እንዳለ (ማቴ.10፡32)፡፡
ለክርስቲያን ልጅ ሁሉ ከተግባረ ሥጋ ከተግባረ ነፍስ አስቀድሞ የቀና ሃይማኖትን መማር ይገባዋል፤ ለበጎ ሥራ ሁሉ መሠረቱ የቀና ሃይማኖት ነውና።

Waldaa Fayyisaa Addunyaa Damee Hoo-lataa





Gochuu hin dagatinaa

Want your business to be the top-listed Food & Beverage Service in Holeta?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address

Lemialemayehu8@gmail. Com
Holeta