Likesh Enter
Premium Ethiopian Specialty Coffee Exporter & Sourcing Agent. Led by certified Q-Grader/Cupper CEO. Connecting global buyers with the finest coffee origins.
10/03/2021
👏👏👏👏👏👏👏👏
ሰምተዋል?
በአፍሪካ ረጅሙ ህንፃ በአዲስአበባ ሊገነባ ነው!
ዝርዝሩን ያድምጡት ይወዱታል 👌
Like and subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ 🙏
በአፍሪካ ረጅሙ ህንፃ በአዲስ አበባ |mesob tower in addis ababa|the tallest building in africa|mereja eth Join this channel to get access to perks:https://www.youtube.com/channel/UCg3fGtcwrFC3xJ6ssClN5QQWelcome to my channelIf you subscribe my channel you get mor...
የእቴጌ ጣይቱ የአድዋ ገድል የሚጀምረው ለአድዋ ጦርነት መነሻ ከሆነው ከውጫሌ ስምምነት ነው፡፡
ኮንት አንቶኔሊ የውጫሌ ውል እርሱ እንደፈለገው እንደማይሆን እና 17ኛዋ አንቀፅ እንደተሰረዘ በሰማ ጊዜ እቴጌ ጣይቱ እና አጤ ምኒልክ በተቀመጡበት እልፍኝ ገብቶ "የ 17ተኛዉ ክፍል ተሰርዞአል ተብሎ ተፃፈ" በማለት አጤ ሚኒልክን ይጠይቃል።አጤ ሚኒልክም "ሁለታችን አንተና እኔ ተነጋግረን አንተ ወደህና ፈቅደህ የተፃፈ ቃል ነዉ ሌላ አልታከለበትም ባስተርጐሚህ የተናገርከዉ ነው" አሉት።
ከዛ ኮንት አንቶኔሊ እንዳልተሳካለት አውቆ የውሉን ወረቀት በጫጨቀውና ጦርነቱ እንደማይቀር ተናግሮ ከእልፍኝ እየወጣ እያለ እቴጌ ጣይቱ ከት ብለዉ በመሳቅ
" የዛሬ ሳምንት አድርገው በዚህ የሚደነግጥ የለም። ሂድ የፎከርክበትን አድርግ እኛም የመጣውን እናነሳዋለን። እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር ሰጥቶ አገሩን የማያድን ሰው ከዚህ የሌለ አይምሰልህ የገዛ ደሙን ገብሮ ለገዛ አገሩ መሞት ጌጥ ነው እንጅ ሞት አይደለም አሁንም ሂድ አይምሽብህ የፎከርክበትን በፈቀደህ ጊዜ አድርገው እኛም ከዚሁ እንቆይሀለን፤
“ያንተ ፍላጐት ኢትዮጵያ በሌላ መንግስት ፊት የኢጣሊያ ጥገኛ መሆኗን ለማሳወቅ ነው። ነገር ግን ይህን የመሰለው የምኞት ሃሳብ አይሞከርም!! እኔ ራሴ ሴት ነኝ። ጦርነት አልፈልግም። ነገር ግን ይህን ውል ብሎ ከመቀበል ጦርነትን እመርጣለሁ!” በማለት ፈፅሞ በኢትዮጵያ ሉአላዊነት እንደማይደራደሩ መናገራቸውን ጳውሎስ ኞኞ አጤ ምኒልክ በሚለው መፅሃፍ አስፍረዋል፡፡
እቴጌ ጣይቱ ሴቶችን በማስተባበር ትልቅ ስራም ሰርተዋል፡፡ እቴጌ ጣይቱ በአድዋ ዘመቻ ወቅትም የራሳቸውን ጦር እየመሩ ዘምተዋል፡፡
ጣሊያኖች ወደ መቀሌው ምሽግ በተሸሸጉ ጊዜም ይህን ሁኔታ የተገነዘቡት እቴጌይቱ የጣሊያኖችን የውኃ ምንጭ በራሳቸዉ ጦር በማስከበብ እና ምንጩን በማሳገድ ውሃ ሲጠማቸው ሽንፈታቸውን እንዲቀበሉ አድርገዋል፡፡ ይህ በመቀሌ የሚገኘው ምንጭም እስከዛሬ ድረስ ውሃ የሚያፈልቅ ሲሆን ለንግስቲቱ መታሰቢያነት ይሆን ዘንድ ‹‹ማይ እንስቲ›› ተብሎ ተሰይሟል፡፡ትርጓሜውም የሴት ውሃ ማለት ነው፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Jemo