Zin-Go
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Zin-Go, Public Figure, Mekelle.
11/09/2024
11/09/2024
ወንጀለኛ የነበሩ 178 የሠራዊት አባላት ይቅርታ ተደረገላቸው
***********
ወንጀለኛ በመሆናቸው እስከ ሞት ፍርድ ተወስኖባቸው ለነበሩ 178 የሠራዊት አባላት በአዲስ ዓመት ይቅርታ መደረጉን የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ከነበረው ግጭት ጋር በተያያዘ አንዳንድ የሠራዊት አባላት የተሰጣቸውን ሕገ-መንግሥታዊ ተልዕኮ ወደ ጎን በመተው በሠራዊቱ እና በሕዝብ ጥቅሞች ላይ ወንጀል መፈፀማቸውን የመከላከያ ሠራዊት በማኅበራዊ ትስስር ገጽ አስታውሷል፡፡
ወንጀል መፈፀማቸውን ተከትሎም ጉዳያቸው በወታደራዊ ፍትሕ ሥርዓቱ አማካኝነት ክስ ተመስርቶባቸው በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው በወታደራዊ ፍርድ ቤቶች እስከ ሞት ቅጣት ተወስኖባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙ 178 የሠራዊት አባላት በፈፀሙት ወንጀል ተፀፅተው የይቅርታ ጥያቄአቸውን ለመንግስት እና ለመከላከያ ሚኒስቴር አሥገብተዋል።
የይቅርታ ጥያቄ ማስገባታቸውን ተከትሎ በአንድ በኩል ጉዳያቸው ለይቅርታ ቦርድ ቀርቦ በአዋጅ ቁጥር 840/2006 አንቀፅ 3 ድንጋጌ መሰረት ይቅርታ ማድረግ የሚያሳካቸውን አላማዎች ግምት ውስጥ በማስገባት እና እነዚህ የሰራዊት አባላት በፈፀሙት ወንጀል መፀፀታቸውም ተመልክቷል።
የመከላከያ ሚኒስቴር የይቅርታ ቦርዱን ውሳኔ መሰረት በማድረግ በመታረም ላይ የነበሩ 178 የሠራዊት አባላት ከዛሬ ጳጉሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከእስር በይቅርታ እንዲለቀቁ መወሰኑን አስታውቋል፡፡
#ኢትዮጵያ2017
እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን !
ፈጣሪ አዲሱን ዓመት ፦
- የሰላም
- የፍቅር
- የአንድነት
- ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ የሰው ልጅ ሞት የማንሰማበት
- ደመ የማይፈስበት
- ሰው ታገተ፣ ተገደለ፣ ታፈነ የሚል ቅስምን ሰባሪ ዜና የማንሰማበት
- በመላ ሀገሪቱ ፍጹም እርጋታ ያለበት
- እናት የማታለቅስበት
- ሰው ወጥቶ ቀረ የማይባልበት
- ፍትሕ ለተነፈጉ ሁሉ ፍትህ የሚሰፍንበት
- ፍትሕ አጥተው የሚያነቡ ፍትሕ አግኝተው እንባቸው የሚታበስበት
- እየፈተነን ያለው የኑሮ ጫና መፍትሄ የሚያገኝበት
- በሰላም በነጻነት ያሻን ቦታ ወጥተን የምንገባበት
- በሁላችንም ዘንድ የማያስማሙን ጉዳዮች መፍትሄ የሚያገኙበት
- እርስ በእርስ ልክ እንደጠላት የማንተያይበት ፣ የማንሰዳደብበት
- እሮሮ፣ ስቃይ በደል የማንሰማበት
- ያዘንን ተስፋ የቆረጥን ፤ የምንጽናናበት ተስፋ የምናደርግበት
- ሰራተኞች ፣ ተማሪዎች ፍጹም የተሳካ ዓመት የሚያሳልፉበት
- ከምንም በላይ በሀገራችን የትኛውም ቦታ ሰላም ተረጋግጦ ፣ ስምምነት መጥቶ በሀገራችን ፍጹም ደስታ የምናገኝበት
- ሁሉም በአንድ መንፈስ ለእናት ሀገሩ " አለሁልሽ " ብሎ የሚቆምበት ያደርግልን ዘንድ ምኞታችን ነው።
ፈጣሪ ምኞታችንን ያሳካልን !
መልካም አዲስ ዓመት !
ከዓመት ዓመት ያደረሰን ፈጣሪ ቀጣዩን እንድናይ ይርዳን !
ለሁላችሁም ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኛለን።
11/09/2024
👏
በሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከ600ው በተፈጥሮ እና በማህበራዊ ሳይንስ (575 እና 538) ከፍተኛውን ውጤት አምጥተው የሰቀሉት ሴት ተማሪዎች ናቸው።
ከዚህ ባለፈ እጅግ በርካታ ሴት ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት በማምጣት የዘንድሮውን ፈተና ሰቅለዋል።
በተመሳሳይ በትግራይ ክልል በተሰጠው ከ700 ፈተናም ሴቶች ከፍተኛ አኩሪ ውጤት ነው ያስመዘገቡት።
ከላይ ለማሳያ የተወሰኑ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ፎቶ ይያዝ እንጂ ሌሎችም በርከታ ሰቃይ ሴት ተማሪዎች አሉ።
የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ወጣ።
ብሔራዊ ሎተሪ አስታዳደር የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ዕጣ ዛሬ ጳጉሜን 5 በህዝብ ፊት መውጣቱን አሳውቋል።
የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 0103072 ➡️ 20,0000,000 (ሃያ ሚሊዮን ብር)
የ2ኛ ዕጣ ቁጥር 0348478 ➡️ 10,000,000 (አስር ሚሊዮን ብር)
የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 1546933 ➡️ 5,000,000 (አምስት ሚሊዮን ብር)
የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 0604640 ➡️ 2,000,000 ብር (ሁለት ሚሊዮን ብር)
(ሁሉንም የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች ከላይ ይመልከቱ)
Click here to claim your Sponsored Listing.