Hanan Mohammed
It has always been my dream to see Ethiopia🇪🇹 flourish.
30/04/2026
#መረጃ
ዛሬ የተመረቀው አዲሱ የአራዳ ፓርክ በውስጡ ምን ይዟል?
👉 5 ኪ.ሜ. የሚረዝም የውስጥ ለውስጥ የአስፓልት መንገድ
👉 የእግረኛ መንገድ፦ 6 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ምቹ የእግር ጉዞ መስመር።
👉 የብስክሌት መስመር፦ 5 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው የሳይክል ሌን።
👉 የመሮጫ ትራክ፦ 5 ኪ.ሜ. የሚረዝም ለስፖርተኞች የተዘጋጀ መስመር።
👉 የንግድ ሱቆች፦ ከፒያሳ ለተነሱ ነጋዴዎች ቅድሚያ የተሰጠባቸው 131 ዘመናዊ ሱቆች።
👉 ምግብና መጠጥ፦ 7 ካፌዎችና ሬስቶራንቶች።
👉 ዘመናዊ የስፖርት አሬና፦ አንድ (1) ዘመናዊ የአካል ብቃት ማዕከል (Gym) እና 7 አዳራሾች።
👉 መድረኮች፦ 8 ፕላዛዎችና 3 አንፊ-ቴአትሮች (ለተለያዩ ኩነቶች ማዘጋጃ የሚውሉ)።
👉ልዩ ውበት፦ በአይነቱ ልዩ የሆነ “ዳንሲንግ ፋውንቴን” (ተንቀሳቃሽ ፏፏቴ)።
👉 ብሔራዊ ምልክት፦ በሀገራችን ረጅሙ የሆነው ባለ 100 ሜትር የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ መስቀያ።
👉የሕፃናት መጫወቻ፦ 4 በሚገባ የተሟሉ ዘመናዊ የመጫወቻ ስፍራዎች።
👉 አረንጓዴ ልማት፦ 15 ሄክታር መሬት በሳርና በተክሎች የተሸፈነ፣ በፓርኩ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ 22 የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች።
👉 ፓርኪንግ፦ በአንድ ጊዜ 280 መኪናዎችን መያዝ የሚችል ሰፊ ማቆሚያ ወዘተ አገልግሎቶችን አካትቷል።
fans
08/04/2026
የኢራናውያን (ፋርሳውያን) የዘር መነሻ
ኢትዮጵያ እንደሆነ ያውቁ ይሆን?
ብዙዎቻችን ስለ ፋርስ (Persia) ስልጣኔ ስናስብ ከአፍሪካ እጅግ የራቀና የተለየ ታሪክ ያለው ይመስለናል፡፡ ነገር ግን ነገሩ እንዲህ አይደለም!
ታዋቂው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ሮይ ካሳግራንዳ
(Roy Casagranda) ጥንታውያን የግሪክ ድርሳናትን ዋቢ
በማድረግ እጅግ አስገራሚ እውነትን ይፋ ያደርጋል፡፡
ለመሆኑ የዛሬዋ ኢራን ስሟንና የንግሥና መሠረቷን ያገኘችው ከኢትዮጵያዊቷ ልዕልት አንድሮሜዳ ማኅፀን እንደሆነ ያውቃሉ?
እስኪ ታሪኩን በጥቂቱ ላጫውታችሁ...
የፋርስ እናት ፧ ኢትዮጵያዊቷ አንድሮሜዳ
ታሪኩ የሚጀምረው እዚሁ ጥንቷ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ንጉሥ ሴፊዎስ (Cepheus) እና ንግሥት ካሲዮፒያ(Cassiopeia) አንድሮሜዳ የምትባል እጅግ ውብ ልጅ ነበሯቸው፡፡
በግሪክ አፈ-ታሪክ መሠረት፡ ጀግናው ፐርሲየስ
አንድሮሜዳን ከሞት ካዳናት በኋላ ጋብቻ መሠረቱ፡፡
እነዚህ ጥንዶች በኢትዮጵያ ምድር ሳሉ "ፐርሰስ" (Perses)
የተባለ የበኩር ልጅ ወለዱ፡፡ ፕሮፌሰር ሮይ ካሳግራንዳ
እንደሚያብራራው፣ ይህ ልጅ በአያቱ በሴፊዎስ ቤተ-መንግሥት አድጎ የኢትዮጵያን ዙፋን ወረሰ፡፡ ቆይቶ ግን ወደ ምሥራቅ በመጓዝ አሁን ፋርስ (Persia) የምንለውን ግዛት መሠረተ፡፡
"ፐርሺያ" የሚለው ስያሜ የመጣውም ከዚሁ ከኢትዮጵያዊቷ አንድሮሜዳ ልጅ ከፐርሰስ ስም እንደሆነ የታሪክ አባት የሚባለው ሄሮዶተስ በድርሳናቱ አረጋግጧል!
"ሁለቱ ኢትዮጵያዎች" ፧ የሄሮዶተስ ምስክርነት
ሮይ ካሳግራንዳ በጥንቱ የግሪክ እይታ "ኢትዮጵያ" የሚለው ስም ትርጕሙ "ፊቱ በፀሐይ የተቃጠለ ሕዝብ" ማለት እንደሆነ ይነግረናል፡፡
ሄሮዶተስም ዓለምን ለሁለት ከፍሎ "ምሥራቃዊ"
እና "ምዕራባዊ" ኢትዮጵያውያን ይላቸው ነበር፡፡
ምዕራባዊያኑ∶ እኛ አፍሪካውያኑ (የዓባይ ሸለቆ ሕዝቦች)
ስንሆን፣ ምሥራቃዊያኑ ደግሞ የዛሬዎቹ ኢራናውያን (ፋርሳውያን) ናቸው፡፡
እንደ ፕሮፌሰሩ ትንታኔ፣ እነዚህ ሁለት ሕዝቦች በታሪክም ሆነ በዘር እጅግ የተሳሰሩና በጥንቱ ዓለም በአንድ "ኢትዮጵያዊነት" ጥላ ሥር የሚታዩ ነበሩ፡፡
በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊነት ከአንድ አህጉር ያለፈ፣ የጥንቱን ዓለም ሥልጣኔ የመሪ ታላቅ የዘር ሐረግ ነው፡፡
ዛሬ በፖለቲካና በጂኦግራፊ ብንራራቅም፣ የታሪክ ድርሳናት ግን ኢራናውያን የኢትዮጵያዊቷ አንድሮሜዳ የልጅ ልጆች እንደሆኑ ይመሰክራሉ!
ምንጭ፦ የታሪክ ፕሮፌሰር ሮይ ካሳግራን (Roy Casagranda)
እንግዲህ ወደ ኋላ ሄደህ መጠየቅ ነው እንደውም ኢራን ከወሎ ነች 🤷🏽♂️