Tocha Communications
This is an official page of Tocha Woreda Government Communication Affairs Office posting any social, economic, cultural and political events of this woreda.
27/05/2026
በቶጫ ወረዳ "ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ከቶጫ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን እና ከቶጫ 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ብልጽግና ፓርት አባል መምህራን ጋር ውይይት ተካሄደ።
በቶጫ ወረዳ "ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል በ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት ዙሪያ፣ ከብልጽግና ፓርቲ አባል የቶጫ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እና ከቶጫ 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን ጋር ሰፊ የማክሮ-ፖለቲካና የጋራ ግንባታ ውይይት ተካሄደ።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ብሮ ም/ኃላፊ እጩ ዶ/ር ገዛኸኝ ገበየሁ እንደጠቆሙት፦መምህራን የነገዋን ተምሳሌት ሀገር የሚገነቡ ትውልዶችን በማፍራት ረገድ ግንባር ቀደም ሚና እንዳላቸው በመጠቆም "ሀገራችን የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ከግብ ለማድረስና የዴሞክራሲ ስርዓታችንን ለማጠናከር መምህራን የነቃ የፖለቲካ ተሳትፎ ሊኖራቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።
በተለይም በ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መምህራን ማህበረሰቡን በማንቃትና ምሁራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ረገድ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለባቸውም አብራርተዋል።
የቶጫ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምራት ታደሴ በበኩላቸው፣ በትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ የፓርቲው አባላት የወረዳውን ልማትና መልካም አስተዳደር ለማረጋገጥ የመሪነት ሚና መጫወት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
አክለዉ፦ ዋና አስተዳዳሪዉ በወረዳችን የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማገዝ፣ የአካባቢውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ እና መጪውን ሀገራዊ ምርጫ በስኬት ለመወጣት ከመምህራን የሚጠበቀውን የነቃ ተሳትፎ መንግስት ሙሉ በሙሉ እንደምደግፍ አሳስበዋል።
የቶጫ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አፈወርቅ ዮሐንስ ባደረጉት ንግግር፣ በትምህርት ጥራት ዙሪያና በፓርቲው አባላት መተካካት ላይ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ መምህራን በትምህርት ገበታቸው ላይ ውጤታማ ስራ ከመስራት ባለፈ ለሀገራዊና ቀጠናዊ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ረገድ ንቁ ተሳታፊ መሆን እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።
በመጨረሻም በውይይቱ የተሳተፉት የቶጫ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እና የቶጫ 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን በሰጡት አስተያየት፣ የቀረቡትን ሰነዶችና የወቅቱን ሀገራዊ ሁኔታ በሚገባ መገንዘባቸውን ገልጸው፣ ለ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ መሳካትና "ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር የማድረግ" ራዕይ እንዲሰምር በትምህርት ክፍላቸውም ሆነ በማህበረሰቡ ውስጥ የበኩላቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ዘገባዉ፦የቶጫ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ነዉ።
26/05/2026
"የአካባቢው ፀጥታ አስተማማኝ የሚሆነው በታማኝና በተደራጀ የሰው ኃይል ነው" አቶ ታምራት ታደሰ የቶጫ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ።
በቶጫ ወረዳ በሕዝብ ተሳትፎ ተመልምለው አገልግሎት በመስጠት ላይ ለሚገኙ 104 የሚሊሻ አባላት ሲሰጥ የቆየው የማጥራት፣ መልሶ ማደራጀትና የደንብ ልብስ ማልበስ ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት በስኬት መጠናቀቁ ተገለጠ።
የቶጫ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምራት ታደሰ እንደጠቆሙት የአካባቢው ፀጥታ አስተማማኝ የሚሆነው በታማኝና በተደራጀ የሰው ኃይል መሆኑን በማንሳት፣ የአካባቢን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሕዝብ ተሳትፎና የታማኝ ሚሊሻ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ዋና አስተዳዳሪው አክለውም፦"ይህ የማጥራትና መልሶ የማደራጀት ሥራ የተከናወነው ሕዝባዊ አመኔታን ይበልጥ ለማጠናከርና የአካባቢያችንን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።
አዲስ የደንብ ልብስ የለበሳችሁ የሚሊሻ አባላት፣ የተሰጣችሁን የመንግሥትና የሕዝብ አደራ በታማኝነትና በቁርጠኝነት ልትወጡ ይገባል" ሲሉ አሳስበዋል።
የቶጫ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደስታ ደዋና በበኩላቸዉ፣ የደህንነት ስጋቶችን ቀድሞ ለመከላከልና ለሕዝቡ ቀልጣፋ ጥበቃ ለመስጠት የአባላቱ ዝግጁነት በከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የቶጫ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ታሪኩ ከበደ እንደጠቆሙት፦ሚሊሻው ከፖሊስ ኃይል ጋር በቅርበትና በቅንጅት በመሥራት ረገድ ያለውን ሚና አድንቀው፣ ይሄኛው መልሶ የማደራጀት ሂደት የወንጀል መከላከል ሥራውን ይበልጥ ውጤታማ እንደሚያደርገው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል ።
የቶጫ ወረዳ ሰላም ፀጥታ ሚልሻ ጽ/ቤት ምልመላና የስልጠና ስራ ሂደት አስተባባሪ መ/አለቃ ግርማ ቡንጉዶ እንደጠቆሙት፦በሰባዊ መብት አጠባበቅ፣በህግ-መንግስት ጽንስ ሀሳብና የጦር መሳሪያ አያያዝና አጠቃቀም ዙሪያ መሰጠቱን አብራርተዉ አደረጃጀቱን ይበልጥ በማጠናከር የሕግ የበላይነትን ለማስከበር በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ሥነ-ሥርዓቱ ለተተኪና ነባር አባላቱ የደንብ ልብስ በማልበስና የወደፊት የሥራ መመሪያ በመስጠት በስከት ተጠናቋል ።
ዘገባዉ የቶጫ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ነዉ።
25/05/2026
በወረዳዉ የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎች ሰላምና ደህንነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ፣ የቶጫ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ከተለያዩ 15 ቀበሌዎች ለተውጣጡ 104 የቀበሌ ሚሊሻ አባላት የአቅም መገንቢያ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።
በቶጫ ወረዳ ለ104 የቀበሌ ሚሊሻ አባላት የአቅም መገንቢያ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ስልጠና ላይ አባላቱ በማኅበራዊ፣ በፖለቲካዊ እና በወታደራዊ ዘርፎች ዙሪያ ሰፊ ግንዛቤ እንደሚያገኙ ተገልጿል
በመርሃ-ግብር ላይ ተገኝተዉ ስልጠናዉን ያስጀመሩት የቶጫ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደስታ ደዋና እንደገለጹት፤ የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ በሚሊሻ አባላቱ ዘንድ ያለውን የአገልግሎት ዝግጁነት ማሳደግና የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በበሰለ መልኩ ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።
አክለዉ ኃላፊ፦ ሚሊሻው ከሕብረተሰቡ ጋር ያለውን ማኅበራዊ ትስስር በማጠናከርና ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታዎችን በሚገባ በመረዳት ረገድ ስልጠናው ጉልህ ሚና እንደሚኖረውም ገልጸዋል።
ሰልጣኞቹም የቀሰሙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር የአካባቢያቸውን ሰላም በንቃት እንዲጠብቁ ተጠቁሟል ።
ይህ ስልጠና በሚሊሻ አባላቱ መካከል ያለውን ዝግጁነትና ቅንጅት በማሳደግ የወረዳዉን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለዉ ተጠቁሟል ።
የቶጫ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነዉ።
24/05/2026
ሻምፒዮኑ አርሰናል ክሪስታል ፓላስን 2ለ1 አሸነፈ
*****************
ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀው የመድፈኞቹ የዋንጫ ጥማት ዛሬ በደመቀ ሁኔታ ተቋጭቷል።
አርሰናል በ38ኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታው ክሪስታል ፓላስን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን የክብር አክሊል ይረከባል።
ለአርሰናል በመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ገብርኤል ጀሱስ የመጀመሪያዋን ግብ አስቆጥሯል፡፡ በሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ማዱኬ ሁለተኛዋን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል፡፡ ለክሪስታል ፓላስ ብቸኛዋን ግብ ማቴታ ማስቆጠር ችሏል፡፡
ቡድኑ እስከ ጨዋታው ፍጻሜ ድረስ ብቃቱን በማስመስከር 2ለ1 ማሸነፉን ተከትሎ የለንደን ጎዳናዎችን በደስታ እና በእልልታ እንዲሞሉ አድርጓል።
በሌሎች የዛሬው የመጨረሻ ሳምንት መርሃ ግብሮች ማንቸስተር ሲቲ በአስቶን ቪላ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ሲሸነፍ ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ ብራይተንን 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲረታ፣ ፉልሃም ኒውካስትልን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ እንዲሁም ዌስትሃም ሊድስን በ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ቢያሸንፍም ወደታችኛው ሊግ ወርዷል።
በሌላ በኩል ሊቨርፑል ከብሬንትፎርድ ጋር 1 ለ 1 ሲለያይ፣ ሰንደርላንድ ቼልሲን 2 ለ 1 በማሸነፍ ያልተጠበቀ ውጤት አስመዝግቧል።
ቶተንሃም ኤቨርተንን 1 ለ 0 አሸንፎ በሊጉ ሲቆይ ፣ በርንሌይ ከዎልቭስ እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ከቦርንማውዝ ጋር 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት የውድድር ዘመኑን አጠናቀዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Telephone
Website
Address
Toamasina