Int. Volunteering group

Int. Volunteering group

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Int. Volunteering group, Artist, Doha.

05/04/2026

እንኳን ለመድህን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ ዝክር መድዓኒአለም በዓል አደረሰን!

11/09/2025

እንቁ ለእኛ ምናችን ትሆን?"
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

“ክረምት አልፎ በጋ መስከረም ሲጠባ፣
አሮጌ ዓመት ሄዶ አዲሱ ሲገባ፣
አደይ ተከናንባ እንቁጣጣሽ ስትደምቅ፣
ምድር በልምላሜ በፀሐይ ሳቅ ስትሞቅ፣
አዲስ ዓመት ሁሌም አዲስ ይታሰባል፣
ምኞት ይታቀዳል ተስፋ ይታለማል፣
ሁሉም በየቤቱ እንደ አዲስ ይነቃል፣
ሁሉም በየሙያው በአጭር ይታጠቃል፡፡”

#እንቁጣጣሽ( ) ?
የኢትዮጵያ የወራት ሁሉ መጀመሪያው ወር መስከረም ነው፡፡ ታዲያ እሱ አንድ ብሎ የሚጀምርበት ቀን ዘመን መለወጫ፣ እንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡

ብርሃን፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት የዓመት ኡደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ የመስከረም ወር የመጀመርያ ወይም የዘመን መለወጫ አልያም አዲስ ዓመት እንደተባለ የሀይማኖት መፅሀፍት ይገልጣሉ።

እንቁጣጣሽ እንኳን ደህና መጣሽ እንላለን።
አዲስ ዓመት ሲቃረብ እንቁጣጣሽ ግን ከየት መጣች?

የሀይማኖት መዛግብት “ዕንቁ – ዕፅ አመጣሽ” ብሎ የአበባውን መፈንዳት ያመለክታል ይሉታል አንዱን ፍች።

ሁለተኛው ደግሞ “ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ አህጉራትን በእጣ ሲያካፍላቸው አፍሪካ ለካም ደረሰችው፡፡ በአፍሪካ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፡፡ ወሩ ወርኀ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ ይህቺን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል” ይላሉ።

ሌላኛውና የመጨረሻው “ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሣባ የንጉሥ ሰሎሞንን ጥበብ ለማየት ከብዙ ሠራዊቶቿ ጋር የእጅ መንሻ በመያዝ ወደ ንጉሡ ሀገር ሄደች፡፡ ንጉሡም ኢትዮጵያዊቷን ንግስት በደስታ ተቀበላት። በመምጣቷ በመደሰቱም “እንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንሽ” በማለት አራት አይነት ቀለም የሚታይበት በቀንና በሌሊት የሚያበራ ቀለበት ሰጣት። የሰጠበት ወርም ወርኀ መስከረም ነበር፡፡”

ከዚህ በመነሣት እንቁ ለጣትሽ ተሰጠሽ በማለት ለመስከረምና ለአዲሱ ዓመት እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ ወጥቷል፡፡

?
ብዙዎቻችን ስኬታችንን፣ ድክመታችንን፣ መሻገራችንን፣ የምንለካው በአዲስ ዓመት ዑደት ነው። እንቁጣጣሽ ስትመጣ ለአዲስ ሰውነት፣ ለመልካም ሥራ፣ ለስኬት፣ ለአብሮነት እናቅዳለን።

እንደሀገር ከተቸገርንባቸው ጉዳዮች ለመሻገር መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።

እንቁ ለውበት እንደሆነ ሁሉ ዛሬ ላይ እንቁ ለእኛ ተስፋ፣ እንቁ ለእኛ አብሮነት፣ እንቁ ለእኛ አንድነትና ብልፅግና የሚያስፈልግበት ጊዜና የዘመን መሸጋገርያ ላይ ነን።

አዲስ ዕድል፣ አዲስ ተስፋ፣ አዲስ ምኞትና አዲስ ስኬት፣ በአዲሱ ዓመት ስንፈልግ እንደ እንቁጣጣሽ ውድ የሆነውን ሰላማችንን በመጠበቅ፣ እንደእንቁ የከበረ ስምና ታሪክ ያላትን ሀገራችንን በአንድነትና በፍቅር በመተጋገዝ ለእድገቷ በመትጋት፣ ካለፈ የታሪክ ቁርሾ ወጥተን በይቅርታና በምክክር ችግራችንን ፈተን በመሻገር፣ ትክክለኛውን እንቁ እንድንገልጥ ያስፈልጋል።

!
🍀🍀🍀🍀🌼🌼🌼🌼🌺🌺🌺

እንኳን ለ2018 የዘመን መለወጫ በዓል በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን!
ዘመኑ የሠላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የስኬት ይሁንልን!!

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Doha?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Doha