Blue Board

Blue Board

Share

Blue Board is an Ai service platform, where every workflow is automated. We transform complex, manual processes in to streamlined, self-running systems.

12/12/2025

The Infliction Point is here.

የአማራ ባንክ በ2018 መጀመሪያ አምስት ወራት 1.15 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዘገበ።

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፣ ታህሳስ 03 ቀን 2018 ዓ.ም የአማራ ባንክ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት ብቻ (ከሐምሌ 1 እስከ ህዳር 30 ቀን 2018) በዋና ዋና የፋይናንስ አፈጻጸም ቁልፍ የሥራ መስኮች ላይ ጠንካራና ከፍተኛ ዕድገት በማስመዝገብ ከታክስ በፊት የ1.15 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዝግቧል።

ይህ የላቀ ትርፍ የተገኘው በ2017 በጀት ዓመት ከተመዘገበው የ910.2 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል። በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አምስት ወራት 3.55 ቢሊዮን ብር ገቢ ማስመዝገብ እንደተቻለ ዋና ስራ አስፈፃመሚው ጠቅሰዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው አክለውም በእነዚህ አምስት ወራት ውስጥ የተመዘገበው አፈጻጸም ስትራቴጂካዊ ትኩረት በጠንካራ የሀብት ማሰባሰብ፣ በዲጅታል ትራንስፎርሜሽንና በብድር አስተዳደር ላይ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ላይ አተኩሮ መስራት በመቻላቸው የመጣ ነው ብለዋል።

ቁልፍ የአፈጻጸም ዋና ዋና መረጃዎች፡-
የተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ፡
አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን እስከ ህዳር 2018 ዓ.ም 35.8 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ዕድገቱ 82 በመቶ ሆኗል። ይህም በአምስት ወራት ጊዜ ውስጥ የ4.29 ቢሊዮን ብር ብልጫ አሳይቷል።

የውጭ ምንዛሪ (FCY) አሰባሰብ፡-
የአማራ ባንክ የ76.58 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ በመሰብሰብ የላቀ አፈጻጸም አሳይቷል፣ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ313 በመቶ ብልጫ አለው።

የብድር አቅርቦትና የሀብት ጥራት፡-
አማራ ባንክ ከተመሰረተ ጀምሮ ያቀረበው አጠቃላይ ብድርና የቅድሚያ ክፍያ አምና በተመሳሳይ ወቅት ከነበረበት በ53.8 በመቶ በማሳደግ ወደ 31.3 ቢሊዮን ብር አበድሯል።

በብድር አሰባሰብ፡-
በህዳር 2017 ከነበረበት 12.9 በመቶ በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ያልተከፈለ/የተበላሸ/ ብድር (NPL) ጥምርታ በአስደናቂ ሁኔታ በማውረድ ወደ 4.06 በመቶ እንዲደርስ ርብርብ ተደርጓል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ኅዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም ተካሂዶ በነበረው በባንኩ 4ኛ ዓመታዊ የባለአክሲዮኖች ጉባኤ ላይ በከፍተኛ ጉጉት የተሰባሰበው ተሳታፊ ከጠዋቱ ጀምሮ ሲታይ አስደሳች ድባብ ፈጥሮ የነበረ ሲሆን በአስደናቂው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ዝቅተኛው የምልአተ ጉባኤ ገደብ መሟላት ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ ደረጃ መሻገር ችሎ ነበር። ይህም ባለአክሲዮኖች በአማራ ባንክ ራዕይ እና አመራር ላይ ያላቸውን ጥልቅ እምነትና ቁርጠኝነት ያሳያል።

ለዚህምልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር!

www.amharabank.com

04/10/2023

HAPPY EASTER

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Dallas?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Dallas, TX

Opening Hours

Monday 8am - 6pm
Tuesday 9am - 5pm
Wednesday 8am - 6pm
Thursday 8am - 6pm
Friday 8am - 6pm
Saturday 8am - 6pm
Sunday 9am - 1pm