Mella

Mella

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mella, Eastern Orthodox church, Reston, VA.

03/19/2023

I have reached 100 followers! Thank you for your continued support. I could not have done it without each of you. 🙏🤗🎉

Photos 06/10/2021

በዓታ ለማርያም
ባዕታ ለማርያም በእለተ ቀኗ ከክፉ ነገር ሁሉ ትሰውራችሁ።
እናታችን ቅድት ድንግል ማርያም ከአባቷ ከእያቀብና ከእናቷ ከሐና ሐምሌ 30 ራእይ አይተው ነሐሴ 7 በብስራተ መልአክ በፈቃደ እግዚአብሔር እሑድ ተፀነሰች።
በእናቷ ማህፀን ሳለች ብዙ ታምራትን አድርጋለች የሞተውን ሳሚናስ ከሙት አስነስታዋለች።ይህም ሳሚናስ የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካአጎቱ ቤት ሄዶ የሞተው ለቀብር ስወስዱት ከመንገድ ባሳረፉት ጊዜ ሐናም የአጎትዋ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቿ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ እርሷም እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነሳቶ ስብሐት ለኪ እሙ ለፀሐይ ጽድቅ ማርያም ሆይ ለአብ ሙሽራው ለወልድ ወላድቱ ለመንፈስ ቅዱስ ጽርሐ ቤቱ ተፈስሒ ደስ ይበልሽ ብሎ ሰገደላት።
መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በእናቱ በኤልሳበጥ ማህፀን ሳለ ለእናታችን ማርያም እንደ ሰገደላት ሰላም ለኪ እንዳላት
{ ሉቃ.1፥41 } ይህም የሞተው ሳምናስ ከሞተበት ተነስቶ ሰገደላት።
☞ ይህንን ታምራት ስትሰራ በሐና ማህፀን 9 ወር ተቀመጠች። ግንቦት መባቻ ዕለት{ ግንቦት 1} ልባኖስ በምትባል አከባብ ተወለደች። በስምንተኛውም ቀን ስሟን "ማርያም" ብለው አወጡላት።
☞ እናታችን ማርያም በእናት አባቷ ቤት 3 ዓመት ተቀመጠች። መዝሙረኛው ዳዊት አባቷ በ{ መዝ 44፥10-11 }ላይ ልጄ ሆይ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ ንጉስ ውበትሽን ወድዶአልና እርሱ ጌታሽ ነውና እንዳለ እናታችን ቅድት ድንግል ማርያም በ3 ዓመቷ የስለት ልጅ ናትና በተመቅደስ ወስደው ለካህኑ ለዘካርያስ ሰጧት።
☞ ቀኑም የታህሳስ ባታ ነበር።መልአኩ ፋኑኤል ከሰማይበመሰቦ ወርቅ ህብስተ ሰማያዊ በብርሃን ጽዋ ስቴ ሕይወት ይዞ ረቦ ታያቸው።እመቤታችንንም በአንዱ ክንፍ ጋርዶ በአንዱ ክንፉም አጎናፅፎ ህብስቱን አብልቷት ወይኑን አጠጥቷት እመቤቴ ሆይ! መንገድ ባስመታሁሽ ማርኝ ብሎ የብርሃን መሶብ የብርሃን ጽዋ ይዞ ወደ ሰማይ አረገ።
☞እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ሕብስተ ሰማያዊ እየተመገ በች ስቴ ሕይወት እየጠጣች ከንጹሓን ይልቅ ንጽሕት የሆንሽ አንቺ ነሽ ከማይነቅዝ ዕንጨት እንደ ተሰራ በወርቅ እንደ ተጌጠና ዋጋው ብዙ በሆነ በሚያበራ ዕንቁ እንደተለበጠ ታቦት በቤተ መቅደስ ውስጥ የኖርሽ የተመረጥሽ ድንግል ነሽ እንዳለ እትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን ቁጥር 6እንዲህ ሆና መላእክት ምግቧን እያመጡላት እየጎበኟት ከመላእክት ጋራ እየተጫወተች እየዘማረች 12 ዓመት በቤተ መቅደስ ተቀመጠች።
☞ የእናታችን የድንግል ማርያም ምልጃ ጸሎት በረከት እረድኤት ከእኛ ከቃልኪዳን ልጆቿ እንዲሁ የአስራት ሃገሯ ከሆነች ከእትዮጵያ ዘወትር አይለያት አይለየን አሜን።

Mella 05/24/2021

Mella Eastern Orthodox Church

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Reston?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

Reston, VA
20190