EthioTimes
EthioTimes is a source of credible news and entertaining TV and radio productions.
07/16/2026
በሀገራችን የኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ትልቁ ውጤት በደቡብ ኮሪያ ተመዘገበ‼️
በደቡብ ኮሪያ ጊምቺዮን ከተማ ከሐምሌ 3_6/2018 ዓ.ም.(July 10_13/2026) የዓለም ሻምፒዮና(በWorld Championship In South Korea # Gimcheon City)
ከ46 ሀገራት የተወጣጡ ከ2000 በላይ አትሌቶች የተሳተፉበት በደቡብ ኮሪያ በተዘጋጀው የአለም ሻምፒዮና ውድድር ላይ ወደ ቦታው ያቀናው የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ብሔራዊ ቡድን ዘጠኝ ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ ደምቆ አጠናቀቀ።
በኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ማስተር ኤልያስ ኩመል እየተመራ ወደ ቦታው ያቀናው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በተሳተፈባቸው ውድድሮች ሁሉ የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ በመግባት የሀገራችንን ስም በአለም አደባባይ ከፍ ብሎ እንዲጠራ ማድረግ መቻላቸው ተሰምቷል።
ከአምስት ወር በላይ ዝግጂት ሲያደርግ የቆየው እና ወደ ቦታው ያቀነው ቡድናችን በውድድሩ ላይ የጠበቅነውን ውጤት በማምጣታችን ደስ ብሎናል ያሉት የቡድኑ አሰልጣኝ እና ቡድን መሪ ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ማስተር ኤልያስ ኩመል ውድድሩ ግን አድካሚ እንደነበረም ገልፀዋል።
አክለውም ብሔራዊ ቡድናችን በአራት ተወዳዳሪዎች በኢንተርናሽናል እና በኮፖት ቴኳን-ዶ የውድድር አይነቶች የተወዳደረ ሲሆን ሁሉም በተወዳደሩበት ካታጎሪ ሜዳሊያ ውስጥ በመግባት በጥሩ ውጤት ማጠናቀቅ መቻላቸውን አብራርተዋል።
በውድድሩ ላይ ሁለት ወርቅ: ሶስት ብር እና አራት ነሀስ በአጠቃላይ ዘጠኝ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ በቀን 7/11/2018 ዓ.ም ጠዋት 2:00 ሰዓት ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ሲሆን ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱም በአርቱ ደጋፊዎች በኩል ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በደቡብ ኮሪያ በተዘጋጀው የአለም ሻምፒዮና ውድድር ላይ ወደ ቦታው ያቀናው የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ብሔራዊ ቡድን ዘጠኝ ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ ደምቆ ከማጠናቀቁ ባሻገር የሁለቱን ሀገራት የቆዬ በጎ ግንኙነት ከፍ እንዳደረገ ተነግሯል።
በጋዜጠኛ ሲሳይ መንግስቴ
07/16/2026
በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ አርጀቲና እና ስፔን ለፍጻሜ ደረሱ።
ከእንግሊዝ ጋር ለዋንጫ ለማለፍ የተጫወተችው አርጀንቲና እስከ 85ኛው ደቂቃ ድረስ 1 ለ 0 ብትመራም ድራማዊ በሆነ መንገድ 2 ጎል አግብታ 2 ለ 1 በማሸነፍ ወደ ፍጻሜው ጨዋታ አልፋለች።
ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ተጋጣሚ የሆነችው አርጀንቲና የፊታችን እሁድ ምሽት 4:00 ፈረንሳይን ጥላ ወደ ፍፃሜ ካለፈችው ስፔን ጋር ትጫወታለች።
Via- tikvahethiopia
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Opening Hours
| Monday | 9am - 5pm |
| Tuesday | 9am - 5pm |
| Wednesday | 9am - 5pm |
| Thursday | 9am - 5pm |
| Friday | 9am - 5pm |
| Saturday | 9am - 5pm |
| Sunday | 9am - 5pm |