Wollo Addis
Our Website www.wolloaddis.com
17/05/2026
''ከሰው እስከ መኪና በጎጃምኛ የተጨፈረበት ሳምንት''
''የማን ነህ እያሉት ኮራ አለ ጅንኑ
ከየት ነህም ሲሉት ዝም አለ ጅንኑ
ያስታዉቅ የለም ወይ ጎጃሜ መሆኑ''
መቼም ሰሞኑን ከሰዎች ተሻግሮ መኪና እንቅጥቅጥ እስክስታ የወረደበት ሳምንት ነበር ።
እዉነት ለመናገር እንደዚህ ሳምንት የጎጃምኛ ምት ያላቸው ሙዚቃዎች በሁሉም በማህበራዊ ሚዲያው መነጋገሪያ የሆኑበት ጊዜ አላስታውስም ። እንዲያውም የጎጃም ሳምንት ቢባል ማጋነን አይሆንም ።
ለዚህም ምክንያት የሆኑት ሐስዩምቃል" ዘነጡ ጎጃሞች "እና የቢሆን ዘዉዴ " ጅንኑ "ሙዚቃዎች ሲሆኑ የሰው ልጆች ከተፈጥሮ ጋር ያላቸውን ቁርኝት፤ እንዲሁም እርስ በርስ ያላቸውን ግንኙነት በሚገልፁበት የኪነት መድረክ ላይ ጎጃም ያለዉን ሁለንተናዊ ሀብት በሚገባው እንድናይ አድርገዋል ማለት ይቻላል ።
በዚህ እንደ ማህበረሰብ ተነግሮ የማያልቅ የተፈጥሮ የመልከአምድር የአስተዳደር የአኗኗር የሰርግ የዉበት የስራ ባህል እያሉን አንዷን ጀግንነት ብቻ በማንሳት በለው በለው የሚል ጦረኝነት ብቻ መነሳቱ ለሌላው ህዝብ አንድም ታጋሹ አራሹ ቀዳሱ ፍትህ አዋቂዉ ህዝብ ጦር የሚሰብቅ መጀመሪያ በሰላም ለመፍታት ሞክሮ አማራጭ ሲያጣ ብቻ ቢሆንም ተዋጊ ጦር ሰባቂ እንዲመስል ሙዚቃዎች ያደረጉትን ተፅዕኖ በመገዳደር የጥይት ኳኳታ የሌለባቸው ቱባዉን የጎጃም የሰርግ ስርዓት የስራ ባህል አምራችነት ፍትህ አዋቂነት አስተዋይነት ኩራት ምሁርነት በግጥም በዜማና በክሊፖቹ ቪዲዮዎች አሳይተዋል ።
ከዮቶር እስከ ተዋናይ ከማኛ አምራችነት እስከ ልምላሜዉ ባህሉን እሴቱን አኗኗሩን ከ እነማይ ኤልያስ ዳሞት ደጀን ጉዛምን ማርቆስ ዘጌ እነሴ ዘልቀው በዜማ በግጥም በምስልም እንድናይ አድርገዋል ።
ኪነት ከከፍተኛ ቁጥጥር ወደ ስርአት አልባ የገበያ ውድድር ከጫፍ ወደ ጫፍ በዘለለችበት ዘመንና ብዙ የሚነገርለትን ማህበረሰብ ስሜት በመኮርኮር አንጋች በማስመሰል ለሸቀጥ በሚዉልበት መድረክ የአማራ ህዝብ ጀግንነቱ በጦረኝነት ብቻ አለመሆኑን ስላሳያችሁ እናመሰግናለን ።
በነገራችን ላይ በሀገራችን የባህል ሙዚቃዎች ታሪክ በበርካቶች እይታ በማግኘት ቀዳሚዉ የጎጃምኛ ሙዚቃ ቀጥሎ ትግርኛ ናቸዉ ። ብዙ የተዘፈነላት ደግሞ ጎንደር ።
የማን ነህ እያሉት ኮራ አለ ጅንኑ
ከየት ነህም ሲሉት ዝም አለ ጅንኑ
ያስታዉቅ የለም ወይ ጎጃሜ መሆኑ
Via:- በታዴየማመይልጅ
17/05/2026
''ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካ እየመጡ በኢትዮጵያ እድገት እና ለውጥ እየተደመሙ ነው'' አዲስ አበባ ብቻ ኢትዮጵያ ናትን?
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተለያዩ ጊዜያት በሚያደርጓቸው ንግግሮች፤ ዓለም በኢትዮጵያ እድገት እና ለውጥ ቢደመምም በርካታ ኢትዮጵያውያን ግን የተሰራውን ስራ በቅጡ ለመገንዘብ እና ለማድነቅ እንደሚያዳግታቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንት ቅዳሜ ግንቦት 8፤ 2018 በተካሄደ የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ላይ ባደረጉት ንግግርም ይህንኑ አቋማቸውን ደግመውታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ንግግሩን ያደረጉት በአዲስ አበባ ከተማ የተገነባው የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምርቃት መርሃ ግብር ላይ እንዳነሱት ከውጭ ሀገራት የሚመጡ ሰዎችን ያስደሰተ ያሉትን የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት አንስተዋል።
ኢትዮጵያ 10.2 ፐርሰንት የምታድግ ብቸኛ አገር ናት ያሉ ሲሆን በድፍን አፍሪካ 10.2 ፐርሰንት እድገት የሚያድግ አንድም ሃገር የለም ብለዋል።
አዲስ አበባ ብቻ ኢትዮጵያ ናትን?
ሀሳብዎን ያካፍሉን?
16/05/2026
''ኢትዮጵያ ውስጥ የስራ ሳይሆን የሰራተኛ ችግር ነው ያለው ስራ በየቦታው አለ። የውጭ ሀገር ዜጎችን እየተጠቀምን ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ''
በዛሬው ዕለት በገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ ውስጥ ሰራተኛ ማግኘት ከባድ ነገር ሆኗል። ወጣቱ ስራ እያለ መስራት አልቻለም ሲሉ ወቅሰዋል። በየቦታው በምንሰራው ስራ ላይ እንቅፋት እየሆነ የመጣው የጉልበት ሰራተኛ ችግር ነው በማለት አብራርተዋል።
ኢትዮጲያ ውስጥ የስራ ሳይሆን የሰራተኛ ችግር ነው ያለው፤ሌላው ቀርቶ የቤት ሰራተኛ እንኳን ማግኘት ችግር ነው ያሉ ሲሆን ይህን ችግር ለመግረፍ የውጭ ዜጎችን ለመጠቀም ተገደናል በማለት'' ለምሳሌ ያክል የቻይና፣ ፊሊፒንስ፣ ኬኒያና ናይጀሪያ ዜጎችን በስፋት እያሳተፍን ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው
በጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት እርሰዎ ምን ይላሉ ሃሳብዎን ያካፍሉን?