Tibeb Media.com
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Tibeb Media.com, Public Figure, Addis Ababa.
06/01/2026
እንኳን አደረሳችሁ ለመላዉ ኢትዮጲያዊያን በሀገር ዉስጥም በዉጭ ሀገር ለምትገኙ ኢትዮጲያዊያንእና ትውልደ አኢትዮጺያን በሙሉ በዓሉ የሠላም የጤና ይሁንላችሁ።
አብርሃም ግዛዉ ኢንተርቴመንት ከኦያያ መልቲ ሚዲያ ጋር በመተባበር "የጥበብ ብልጭታ" የመዝናኛና የመረጃ ኘሮግራም እንኳን ለገና በዓል አደረሳቹህ እያለ "ገና ከእኛ ጋር" የተሰኘ ልዮ የበዓል ኘሮግራም ይዞላች ይቀርባል። በዓሉ የሰላም የጤና እንዲሆን ይመኛል። ልዮ- ልዮ አዝናኝ የበዓል ኘሮግራሞች በተወዳጅ በብስራት ኤፍ .ኤፍ101.1 ሮብ ታህሣስ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:00-8:00 ሰዓት ላይ ይዞላችሁ ይቀርባል::
አዝናኝና አሰተማሪ ድራማ :ጭዉዉቶች ሽልማት የሚያስገኙ ጥያቄና መልስ ዉድድሮች:ከታዋቂ አርቲስቶችና ሃይማኖት አባቶች ጋር ቆይታ ገና በዓል የተመለከተ የኘሮግራሙ አካል ናቸዉ::
በእለቱ የተለያዮ ስጦታዎች በዝግጅቱ እንሰጣለን ከአድማጮች ጋር በቀጥታ ስልክ መስመር እንኳን አደረሳችሁ መልክቶችን ለወዳጅ ዘመድ ያስተላልፍ ያድምጡ ይሳተፍ 0912374014 መስመር ቆይታ እናደርጋለን ያድምጡን0930470847 ይሳተፍ በድረ http://xn--www-kbpygv3a3m.bisrattv.com/ ወይም www.bisrat fm.com ላይ በመላዉ አለም እንደመጣለን።መልካም በዓል
በበዓሉ እለት ገና ታህሳስ 29 ቀን 2018 ዓ.ም 6:00 እስከ8:00ሰዓት በተወዳጁ ጣብያ ብስራት ኤፍ ኤም101.1 ላይ።
መልካም በዓል!!!መልካም በዓል!!! ኘሮግራማችን በፕላቲንየም ደረጃ ክብር ስፖንሰር 1.ሞሃ ለሥላሳ መጠጦች ኢንድስትሪ አ.ማ
2. ፖፕላር ኤሌክትሮኒክስ
እጅግ አድርገን እናመሠግናለን በወጣ ይተካ ክብረት ይስጥልን።
02/01/2026
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዓለም ዙሪያ በክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ ያለው ጭቆናና መገለል እያየለ መምጣቱን ገለፁ
የ #ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ በዓለም ዙሪያ በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸሙ ስደት፣ ግድያ እና እገታዎችን በመጥቀስ፣ በአሁኑ ወቅት ክርስትና በከፍተኛ ሁኔታ እየተገለለ መሆኑን ገለፁ።
ፓትርያርኩ የገና በዓልን እና የፈረንጆቹን ዘመን መለወጫ አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክታቸው፤ የቴክኖሎጂ እድገትንና ቁሳዊ ምቾትን ጨምሮ ዘመናዊው ስልጣኔ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች እውቅና ተሰጥተዋል። ሆኖም ግን ይህ ስልጣኔ ለክርስትና እምነት የማይመችና ፈታኝ ሁኔታን መፍጠሩንም ጠቁመዋል።
"በዓለም ላይ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ ክርስትናን የሚከተል ቢሆንም፣ በዘመናችን ግን ክርስትና በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ጎን እየተገፋ መሆኑን እያየን ነው" ብለዋል ቅዱስነታቸው።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በክርስቲያኖች ላይ እየተፈጸመ ስላለው ስቃይ፣ እገታ እና ግድያ ያላቸውን ጥልቅ ስጋት ገልጸዋል። እነዚህ ድርጊቶች ስልጣኔ አከብራቸዋለሁ ከሚላቸው የሥነ-ምግባር እሴቶች ጋር የሚቃረኑ መሆናቸውንም አስረድተዋል። አያይዘውም፣ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ክርስትናን ለማዳከም የሚሰሩ አካላት "ከክፉ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ" አሳስበዋል።
ፓትርያርኩ በመልዕክታቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የሚመለከታቸው አካላት “የሃይማኖት ነፃነትን ለመጠበቅ” ተግባራዊ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። እምነትን የመከተል መብት ሊከበር እና ሊጠበቅ የሚገባው መሰረታዊ ሰብአዊ መብት መሆኑንም አፅንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ መልዕክታቸውን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ካለው መንፈሳዊ ትርጓሜ ጋር በማያያዝ፤ የክርስቶስ ልደት ሰማይና ምድርን አንድ ያደረገ እና የሰውን ልጅ ወደ ሰላም የጠራ መለኮታዊ መገለጥ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ አዲሱ ዓመት እንደ ቀን ለውጥ ብቻ ሳይሆን ምስጋና እንደሚገባው መለኮታዊ ስጦታ ተደርጎ ሊታይ እንደሚገባም አክለው ገልጸዋል።
ቅዱስነታቸው በተጨማሪም፤ እስራኤልና ፍልስጤምን እንዲሁም ሩሲያና ዩክሬንን ጨምሮ በግጭት በሚታወኩ ቀጠናዎች ሰላም እንዲሰፍን ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፤ በሰቪሎች ላይ የሚፈጸመውን ግድያ፣ ስቃይ እና መፈናቀል አውግዘዋል። ፓትሪያርኩ ከስደተኞች እና ከተጎዱ ማህበረሰቦች ጋር አንድነት እንዲኖርም ጥሪ አቅርበዋል።
አቡነ ማትያስ መልዕክታቸውን ሲያጠቃልሉም፤ የተራቡ የሚጠግቡበት፣ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው የሚመለሱበት፣ ልዩነቶች በዕርቅ የሚታረቁበት፣ ጦርነቶች የሚቆሙበት፣ ሰብአዊ ክብር የሚመለስበት እና ፍቅር በሁሉም የሰው ልጅ ዘንድ የሚዳረስበት ፍትሃዊ እና ርኅራኄ የሰፈነበት ዓለም እንዲሆን ተመኝተዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.