Halaba City Sport Club
⚽ Halaba Kenema FC | Official Page
Welcome to the official page of Halaba Kenema Football Club.
21/10/2026
ሀላባ ከተማ / በርበሬዎቹ (2019)
20/10/2026
በተከታታይ 3 ጨዋታ ጠንካራ ክለቦችን አስተናግደን ጅማሬያችንን በሊጉ ልምድ ካላቸው ክለቦች በተሻለ አሳምረናል፡፡
ባለፉት 3 የቤታችን ጨዋታዎች በርበሬዎቹ ማራኪውን የኳስ ፍሰት ይዘው ለሊጉ ክስተት ሆነው መቅረባቸውን በተግባር ማስመስከርም ጀምረዋል፡፡
እስካሁን ባድውረግናቸው ጨዋታዎች በሊጉ ከከረሙ ክለቦች በተሻለ መልኩ ያሳየነው ድንቅ ብቃት እጅግ የሚያስደስት ጠንካራ የቡድን ቁመና እንዳለን አመላካች ነው፡፡ ሆኖም ይህ አኩርቶ የሚያስቆመን ሳይሆን የበለጠ የሚያጠናክረን ነው፡፡
በሌላ በኩል በሀገሪቱ የእግር ኳስ ውድድሮች ደረጃ የተቀዛቀዘውን የደጋፊዎች ድባብ በመመለስ ለመላው የኢትዮጵያ ስፖርት አፍቃሪያን መነቃቃትን መፍጠር መቻላችን በራሱ ተጨማሪ ድል ነውና መላው የክለባችን ደጋፊዎች በሀላባ ከነማ ስም ዛሬም ከልብ እናመሰግናለን!!❤️🙏
እንግዲህ በዚህ ሳናበቃም በቀጣይ ጨዋታዎች እንደ ክለብ የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ እንዲሁም እንደ ደጋፊ የበለጠ ድባብ በመፍጠር የፕርሚየር ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪነታችንን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል!! ደግሞ እናሳካዋለን!!
በተሻለ ድልና ድባብ ከሀላባ ከነማ ጋር ወደ ፊት ብቻ!
20/10/2026
በ3ተኛ ሳምንት ጨዋታ ክለባችን ሀላባ ከተማ ከፋሲለሰ ከነማ ጋር አቻ ተለያየ
***
*ጥቅምት 10/2019
በሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ3ኛ ሳምንት ጨዋታ ፋሲል ከነማን የገጠመው ክለባችን ሀላባ ከተማ 1 አቻ ተለያይቷል።
ጨዋታው በተጀመረ በ10ኛው ደቂቃ የክለባችን የመሀል ተከላካይ ካሌብ አማንኩዋ ክለባችንን ሀላባ ከተማን ቀዳሚ ቢያደርግም በሁለተኛው አጋማሽ 50ኛው ደቂቃ ላይ ሮማርክ ያስቆጠራት ግብ ፋሲል ከነማን አቻ አድርገ ጨዋታው 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል።
ሀላባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Website
Address
Cape Town
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when Halaba City Sport Club posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.