Ahaw Church Of Christ Toronto Local Congregation

Ahaw Church Of Christ Toronto Local Congregation

Share

Orthodoox Reformed Church

07/24/2023

"እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም"(1ኛዮሐ1፥5)
ብርሃን ፡- ቅድስናን እና ጽድቅን
ጨለማ ፡- ኃጢአትን እና ዓመጽን ይወክላል። በክርስቶስ ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ የብርሃን ልጅ ተብሎ ይጠራል። መጽሐፍም እንዲህ ይላል፡- "ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም" (1ኛተሰ5፥5)። የእግዚኣብሔር ልጅ ወደ ዓለም የመጣው በጨለማ ላይ የሚያበራ እውነተኛ ብርሃን ሆኖ ነው ፡ "ደግሞም ኢየሱስ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው" (ዮሐ 8:12) ተብሎ እንደተጻፈ። ስለዚህ ከብርሃን የተወለድነው እኛ የብርሃን ልጆች ከሆንን እኛም ደግሞ ብርሃን ነን ፡ ብርሃናችን ግን የራሳችን ሳይሆን በህይወታችን ውስጥ የሚበራ የክርስቶስ ብርሃን ነው። መጽሐፍም "እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ"(ማቴ5፥14) ይላል። ደግሞም " መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።"(ማቴ5፥16) ፡ ሲል በብርሃን የሚወከለውን መልካሙን ሥራ በመስራት ራሳችንን ለእግዚአብሔር በቅድስና በመለየት እንደ ብርሃን ልጆች እየተመላለስን ብርሃናችንን በሰው ሁሉ እንድናበራ መጽሐፍ ያስተምረናል።
- ኢሄውላቹህ ወገኖቼ ዛሬ የጌታ መምጫ በእጅጉ የተቃረበበት ዘመን ላይ እንዳለን ከማንም የተሰወረ አይደለም፡ አሁን ራሳችንን የምንመለከትበት ህይወታችንን የምንፈትሽበት ግዜ ነው፡ በክርስቶስ ያገኘነው አርነት ከክብር ወደክብር የምንሸጋገርበት ፡ የጌታን መምጣት እየተጠባበቅን ራሳችንን ለእግዚኣብሔር የምናስገዛበት ጸጋ ነው፡- "እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም። በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና። "(ሮሜ8፥1-2) ነገር ግን ኋጢአት በባህርያችን ስፍራ አግኝቶ ከሆነ ምልልሳችን አምልኮታችን ከንቱ ይሆንብናል፡ ስለዚህ መጽሐፍ እንዳለ፡-" አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ።" (1ኛጴጥ2፥16) በጸጋው ላዳነን ጌታ ራሳችንን እንድናስገዛ፡ መንፈስ ቅዱስ ይርዳን ።

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Toronto?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Toronto, ON