Fact Check Ethiopia
Fact Check
04/12/2026
የታዋቂ ግለሰቦችን እና ተቋማትን ስም እና ምስል (አርማ) በመጠቀም የሚከፈቱ ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና አካዉንቶች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ተገቢዉን ጥንቃቄ እናድርግ።
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ዋና ጸሐፊ የሆኑትን ሚስጥረስላሴ ታምራትን ስም እና ምስል በመጠቀም የተከፈቱ የፌስቡክ ገጾች እና አካውንቶች የተለያዩ መረጃዎችን እያጋሩ መሆናቸዉን ተመልክተናል።
ኢትዮጵያ ቼክ በጉዳዩ ላይ ባደረገዉ ማጣራት በርከት ያሉ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገጾች እና አካውንቶች በዋና ጸሐፊዋ ስም መከፈታቸዉን አረጋግጧል።
በሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንቶቹ ከተጋሩ መረጃዎች መካከል 7ኛዉን ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተገናኘ ግለሰቦች ላይ ያነጣጠሩ የጥላቻ ንግግሮች ይገኙበታል።
ዋና ጸሐፊዋ ከቀናት በፊት በትክክለኛ የፌስቡክ አካውንታቸው ባጋሩት ጽሁፍ “በስሜ ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተከፈቱና እኔን የማይገልጹ ጽሁፎች እንዲሁም ፎቶዎች ተቀናብረው እየተለቀቁባቸው መሆኑን ተመልክቻለሁ” ብለዋል።
በተጨማሪም ትክክለኛ አካውንታቸዉ ከ55 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ይህ አካውንት እንደሆነ ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል፡፡
https://www.facebook.com/share/17f9UcAsUC/?mibextid=wwXIfr
ከታች በምስሉ የተያያዙት ሀሰተኛ ገጾች መሆናቸው ከተረጋገጡት መካከል የተወሰኑት ናቸው፡፡
04/04/2026
" የሚቆም የትራንስፖርት አገልግሎቱ የለም " - የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
Fact Check Ethiopia
መንግስት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቆም ያስተላለፈው ምንም ዓይነት ትዕዛዝ እንደሌለ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳወቀ።
በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ምክንያት በተፈጠረው የነዳጅ መስተጓጎል " የትራንስፖርት አገልግሎት ይቆማል " በሚል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትን ስምና ሎጎ በመጠቀም የሚሰራጨው መረጃ የተሳሳተ እና የውሸት መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
" መንግስት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቆም ያስተላለፈው ምንም ዓይነት ትዕዛዝ የለም። አገልግሎቱ እንደተለመደው ይቀጥላል " ብሏል።
ዜጎች ከማይታወቁ ምንጮች የሚወጡ መረጃዎችን እንዳያጋሩ እና የሀሰተኛ ወሬዎችን ስርጭት እንዲከላከሉ ጥሪ ቀርቧል።
በሌላ በኩል ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ዜጎች ከሐሰተኛ ዜናዎች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ስርጭት ራሳቸውን እንዲጠብቁ መልእክት አስተላልፏል።
" ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ተብሎ የሚደርስዎትን ማንኛውም ይፋዊ መልዕክት ከማጋራትዎ በፊት ሁልጊዜም በጽሕፈት ቤቱ ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና ድህረ-ገጽ በመግባት፣ ትክክለኛነቱን እንዲያረጋግጡ እናሳስባለን " ብሏል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Toronto, ON
V5A2Z6