Yabets

Yabets

Share

social service

24/05/2022

🚺 በ4 ቀን ውስጥ ጥርስን ለማንጣት የሚጠቅም 🚺

በተፈጥሮአዊ መንገድ ህክምና ድረስ መሄድ ሳያስፈልገን ቤታችን ውስጥ ጥርሳችን እንዴት ማንጣት እንችላለን? በተፈጥሮአዊ መንገድ ዘውትር በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ትመለከታለህ...!!
እንዴት ማዘጋጀት እንችላለን?

🌀መጠን...!!

1. ለብ ያለ ውሃ ሁለት ብርጭቆ!!

2. የተፈጨ ቀረፋ አንድ ማንኪያ!!

3. የንብ ማር አንድ ማንኪያ!!

4. የሎሚ ጠብታዎች!!

🌀አዘገጃጀት...!!

ትንሽ ተለቅ ባለ ብርጭቆ ውሃውን እንጨምራለን...!!ከዚያም ቀረፋውን እና ማሩን እናስከትላለን!! በመጨረሻም ከአምስት የማይበልጡ የሎሚ ጠብታዎችን እንጨምርበትና በደንብ አዋህደን ስናበቃ ዘውትር ጠዋት አፋችንን እንጉመጠመጥበታለን...!! ለውጡን በ4 ቀናት ውስጥ ቁልጭ አድርጎ ያሳይወታል...!!

25/04/2022

75 days Asere or natanan yabets Thanks to God

24/04/2022

ዘጸአት 12
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
⁶ በዚህም ወር እስከ አሥራ አራተኛው ቀን ድረስ ጠብቁት፤ የእስራኤልም ማኅበር ጉባኤ ሁሉ ሲመሽ ይረዱት።
⁷ ከደሙም ወስደው በሚበሉበት ቤት ሁለቱን መቃንና ጉበኑን ይቅቡት።
⁸ በእሳት የተጠበሰውን ሥጋውንና ቂጣውን እንጀራ በዚያች ሌሊት ይብሉ፤ ከመራራ ቅጠል ጋር ይበሉታል።
⁹ ጥሬውን በውኃም የበሰለውን አትብሉ፥ ነገር ግን ከራሱ ከጭኑ ከሆድ ዕቃው ጋር በእሳት የተጠበሰውን ብሉት።
¹⁰ ከእርሱም እስከ ጥዋት አንዳች አታስቀሩ፤ እስከ ጥዋትም የቀረውን በእሳት አቃጥሉት።
¹¹ ወገቦቻችሁን ታጥቃችሁ፥ ጫማችሁን በእግራችሁ፥ በትራችሁንም በእጃችሁ አድርጋችሁ እንዲህ ብሉት፥ ፈጥናችሁም ትበሉታላችሁ፤ እርሱ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው።

22/04/2022

ጌታችን ኢየሱስ በመስቀል ላይ ለ6 ሰዓታት ቆይቷል።ሚስማር አይደለም ድንኳን የምንወጥረበት አይነት ትልቅ ችንካር በእጆቹ ላይ እግሮቹ ላይ የተመታው፣ በመስቀል ላይ ሆኖ ክብደቱን ሲለቀው እጆቹ ላይ የሚፈጠረው ህመም ከባድ ነበር።ቀና ለማለት ክብደቱን እግሩ ላይ ማድረግ አለበት ያን ጊዜ የሚፈጠረውን ህመም አስቡት ስቃዩ በጣም በጣም ዘግናኝ ነው።ይሄ ብቻ አይደለም መስቀል ላይ ያለ ሰው መናገር ከባድ ነው ነገር ግን ጌታችን ኢየሱስ 7 ነገሮችን ተናግሯል።ከእነዚህ ውስጥ አንዱ እና የመጨረሻው ተፈፀመ የሚል ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ከስድስት የተለያዩ ቁስለቶች ደም ይፈሰው ነበር።ጌታ ኢየሱስ የሞተው ሞት የድል ሞት ነው ምክንያቱም በሞቱ ነው ድል የነሳው።
በታላቅ ድምጽ ጮኾ ነፍሱን ሰጠ፣ ሰው ሲሞት ጮኾ መሞት አይችልም፣ በታላቅ ድምጽ ለመሞት ኃይል ፣አቅም ይጠይቃል።ምክንያቱም ነፍሱን ተወስዶበት ሳይሆን በፍቃዱ ነው።ተፈፀመ አለ ምንድን ነው የተፈፀመው?
1)የኃጢያትን ችግር፣ውስብስብነት ካልተረዳን በቀር ኢየሱስ የከፈለልን ዋጋ አናውቀውም።የኃጢያትን ችግር ከሰው ይልቅ ፣ ከሰይጣን ይልቅ እግዚአብሔር ጋር ነው።እንዴት? እግዚአብሔር አጥብቆ የሚወደውን ሰው እና እግዚአብሔር አምርሮ የሚጠላው ኃጢያት ተገጣጠሙበት፣ መለየት እስከማይቻል ድረስ...ሰረፀ...ገባ ...መለየት በማይቻል መጠን ስለዚህ እግዚአብሔር በፅድቅ ፣በእውነት ፈርዶ የሰው ልጅ የሚገባውን ቅጣት በገሃነም መስጠት ይችላል ምንም ችግር የለበትም ግን ምህረቱ አይፈቅድለትም አምረሮ የሚጠላው ኃጢያት እንዲቀጣለት ቢፈልግም አጥብቆ የሚወደው ሰው ልጅ እንዲጠፋ አይፈልግም። እውነቱ ደግሞ የሰው ልጅ ምህረት ይደረግለት ፣ ዝም ብሎ ይዳን ፣ የዘላለም ህይወት ያገኝ ቢል ደግሞ ኃጢያት የሚገባውን ቅጣት ሳገኝ ፅድቁ እሺ አይለውም።መስቀል የእግዚአብሔእር ጥበብ እውነት እና ምህረትን ያስታረቀ ያስማማ ነው።ለመለኮታዊ ተግዳሮት መለኮታዊ መፍትሔ ያገኘበት ቦታ ነው መስቀል።
አጥብቆ የሚጠላውን ኃጢያት ልጁ ላይ አደረገ። ሮሜ 8፡3-4 ኃጢያትን በልጁ አደረገ እና ኃጢያትን ኮነነው።እግዚአብሔር በሰው ሁሉ ላይ ያለውን ቁጣ በልጁ ላይ አደረገ፣ ኃጢያትን ቀጣው፣ ኮነነ ያንን ጊዜ ፅድቁ ረካ እውነቱ ረካ ምክንያቱም ፍትህ ተፈፀመ።በመስቀሉ ስራ የሰው ልጅ አምኖ የሚድንበት ስራ ተሰራ።ኢየሱስ ራሱን ያቀረበው ለአብ ነው (ኤፌሶን 5:2) ለአብ ራሱን መስዋት አድርጎ አቀረበ።ኢየሱስ ክርስቶስ በፍፁም ቅዱስ ስለሆነ ያቀረበው መስዋት እንከን የሌለበት ነው እንደዚህ አይነት መስዋት ማቅረብ የሚችል የለም። አሁንም በዚህ መድኃኒት ወደ አብ የሚመጣ ሁሉ ተፈፅሞለታል፣ ተሰርቶለታል ሰተት ብሎ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት ነው ፣ አማላጅ አያስፈልገው፣ አጋፋሪ አያስፈልገው፣ ሰተት ብሎ መግባት ይችላል።
ኤፌሶን 2:16-18"ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።
“መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤
በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና"
የመስቀሉ ስራ ለሚያምን ሁሉ ፃዲቅ ያደርጋል። የኢየሱስ ደም ከኃጢያት ሁሉ ያነፃል።ተፈፀመ።
ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Adama?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Adama