SOFI MEDIA

SOFI MEDIA

Share

እንኳን ወደ ሶፊ ሚዲያ በሰላም መጣችሁ
ሰድክራይብ ሼር ላይክ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኒ
እውቀት ሙሉ ሰው ይደርጋል

13/05/2022

የጉግል ኩባንያ የ ኦሮምኛንና የትግርኛ ቋንቋን ጨምሮ 24 ቋንቋዎችን በመተርጓሚያ ዝርዝር ውስጥ አካተተ
ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉግል እና #ትግርኛ ጨምሮ ከ300 ሚሊዮን በላይ የሚናገራቸውን 24 አዳዲስ ቋንቋዎች በጉግል መተርጎሚያ ዝርዝሩ ውስጥ አካቷቸዋል።
ከእነዚህ ውስጥ አስሩ ቋንቋዎች በአፍሪካ የሚነገሩ ሲሆን ከነዚህም መካከል አፋን ኦሮሞ ፣ ትግርኛ፣ ትዊ፣ ባምባራ፣ ክሪዎ፣ ሉጋንዳ ይገኙበታል።
በኢትዮጵያ እና በኬንያ ወደ 37 ሚሊዮን የሚጠጉ ነዋሪዎች አፋን ኦሮሞ የሚናገሩ ሲሆን ከ8 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የኤርትራና የትግራይ ተወላጆች ትግርኛን ይናገራሉ።
" ለዓመታት ጉግል መተርጎሚያ የቋንቋ ልዩነቶችን በማጥበብ በመላው ዓለም የሚገኙ ማህበረሰቦችን ለማገናኘት ረድቷል " ሲል የአሜሪካው ኩባንያ ገልጿል።
አክሎም አሁን ቋንቋቸው በአብዛኛው ቴክኖሎጂ ውክልና ያልተሰጣቸው ሰዎችን መርዳት ይፈልጋል ብሏል።
አሁን የተካተቱትን ቋንቋዎች ጨምሮ በጉግል ተርጓሚ የተካተቱ አጠቃላይ ቋንቋዎች ብዛት ወደ 133 ደርሷል።
አዲሶቹ የተካተቱት ቋንቋዎች የቴክኖሎጂ ምዕራፍን እንደሚወክሉ ገልጾም ምሳሌ ሳይኖር የሚተረጉም የማሽን መማሪያ ሞዴል እንደሚጠቀሙ አስፍሯል።
ይህ ኮምፒውተርን ለማሰልጠንና ትርጉሞቹን በማሰባሰብ የመረጃ ቋቱን ለማካበት የሚያገለግሉ በርካታ ሰዎች ለሌሏቸው ቋንቋዎች ጠቃሚ ሊሆን ይችላል ብሏል።
ነገር ግን ኩባንያው ቴክኖሎጂው ፍጹም እንዳልሆነ አምኗል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
የዩትዩብ ቻናላቻችንን በመቀላቀል ወዳጅነታችንን ያጠናክሩ
https://youtu.be/7gkABYu4xAY

05/05/2022

ሶፊ ሚዲያ ሰድክራይብ ሼር ላይክ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኒ
https://www.youtube.com/channel/UCTQig593Mf_oZR6aAqnzRuQ

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa