Hashim tube

Hashim tube

Share

ኑ አዉሩ

08/12/2025

ታዲያ “ሙስሊም” ማለት አንዱን አምላክ በብቸኝነት ማምለክ ከሆነ እስልምና የተጀመረው መቼ ነው? አንዳንድ ስለ እስልምና እሳቤው የሌላቸው ሰዎች በነብያችን”ﷺ” የተጀመረ ይመስላቸዋል፤ ነገር ግን እውነታው እስልምና ነብያችን”ﷺ” ከመላካቸው በፊት የነበሩት ሰዎች፣ ጂንዎች እና መላእክትም ሙስሊም ናቸው፤ እንዲህ ሲባል እንደው እውርና ድንብር የሆነ ፀለምተኛ ሙግት ሳይሆን ከቋንቋ ሙግት እና ከአምላካችን ከአላህ ንግግር ተነስቼ ነው፤ ይህንን ነጥብ በነጥብ እናያለን፦

ነጥብ አንድ
“መላእክት”
በሰማያት ያሉት መላእክት ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የታዘዙ ናቸው፦
3፥83 በሰማያትና በምድር *”ያሉት ሁሉ”* በውድም በግድም ለእርሱ *”የታዘዙ”* ወደርሱም የሚመለሱ ሲኾኑ ከሓዲዎች ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን? أَفَغَيْرَ دِينِ ٱللَّهِ يَبْغُونَ وَلَهُۥٓ أَسْلَمَ مَن فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ طَوْعًۭا وَكَرْهًۭا وَإِلَيْهِ يُرْجَعُونَ

“የታዘዙ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “አስለመ” أَسْلَمَ ሲሆን “ሙስሊም” مُسْلِم የሚለው ቃል የመጣበት ስርወ-ግንድ ነው፣ ስለዚህ በሰማያት ያሉት መላእክት ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የታዘዙ ሲሆኑ እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፤ አይሰለቹም፦
21:19 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉም የእርሱ ነው፡፡ እርሱ ዘንድ ያሉትም መላእክት *”እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፤ አይሰለቹም”*፡፡ وَلَهُۥ مَن فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۚ وَمَنْ عِندَهُۥ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِۦ وَلَا يَسْتَحْسِرُونَ

ይህ እስልምና ውስጡ ሡጁድ ያቀፈ ሲሆን ይህም ሡጁድ “ሡጁዱል ዒባዳ” سُّجُود العبادة ማለትም “የአምልኮ ስግደት” ነው፦
16:49 ለአላህም በሰማያት ያለው ከተንቀሳቃሽም በምድር ያለው ሁሉ፣ *”መላእክትም ይሰግዳሉ፤ እነርሱም አይኮሩም”*፡፡ وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ مِن دَآبَّةٍۢ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةُ وَهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ
16፥50 ጌታቸውን ከበላያቸው ሲኾን ይፈሩታል፡፡ *”የታዘዙትንም”* ሁሉ ይሠራሉ፡፡ يَخَافُونَ رَبَّهُم مِّن فَوْقِهِمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ ۩
7፥206 እነዚያ እጌታህ ዘንድ ያሉት መላእክት እርሱን *“ከማምለክ” አይኮሩም፤ ያወድሱታልም፤ “ለእርሱም ብቻ ይሰግዳሉ”* ። إِنَّ ٱلَّذِينَ عِندَ رَبِّكَ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِۦ وَيُسَبِّحُونَهُۥ وَلَهُۥ يَسْجُدُونَ ۩

01/12/2025

፨ "መኽሉቅ" مَخْلُق ማለት "ፍጥረት" ማለት ሲሆን ፍጥረት ውጤት ከሆነ ፈጣሪ መንስኤ ነው፥ አሏህ ስለመኖሩ ጉልኅ ማረጋገጫ የፍጥረት ሙግት"cosmological argument" ነው፦
56፥58 በማኅፀኖች የምታፈሱትን አያችሁን? أَفَرَأَيْتُم مَّا تُمْنُونَ
56፥59 እናንተ ትፈጥሩታላችሁን? ወይስ እኛ ፈጣሪዎቹን ነን? أَأَنتُمْ تَخْلُقُونَهُ أَمْ نَحْنُ الْخَالِقُونَ

በተራክቦ ጊዜ በሴት ብልት ውስጥ የሚፈሰውን የወንድ ሕዋስ"sperm cell" ሰው አርገን መፍጠር አለመቻላችን በራሱ የተፈረጠውን የሚፈጥር ፈጣሪ እንዳለ አመላካች ነው፥ በመንስኤ እና በውጤት ሕግ ያለ ሠሪ ተሠሪ እንደሌለ ሁሉ ያለ ፈጣሪ ተፈጣሪ የለም። የፍጥረት ሙግት በመቀጠል ሰው እራሱን እራሱ አለመፍጠሩ የፈጠረውን ፈጣሪ እንዳለ በቂ ማሳያ ነው፦
52፥35 ወይስ ያለ አንዳች "ነገር" ተፈጠሩን? ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን? أَمْ خُلِقُوا مِنْ غَيْرِ شَيْءٍ أَمْ هُمُ الْخَالِقُونَ
52፥36 ወይስ ሰማያትን እና ምድርን ፈጠሩን? አይደለም አያረጋግጡም፡፡ أَمْ خَلَقُوا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ ۚ بَل لَّا يُوقِنُونَ

ፍጥረት ያለምንም ፈጣሪ እንዳልተፈጠረ እሙን እና ቅቡል ነው፥ ፍጥረትን ፍጡር አልፈጠረም። ሰማያትን እና ምድርን ሰው አለመፍጠሩ በራሱ ፈጣሪ መኖሩን ማረጋገጫ ነው። ይህንን ሙግት በምንጨታዊ፣ በስሙር፣ በርቱዕ ሙግት ስናዋቅረው፦
1. ማንኛውም ነገር መነሾ አለው፣
2. መነሾ ያለው ነገር መንስኤ"cause" አለው፣
3. ስለዚህ ፍጥረትን ያስገኘው መንስኤ ፈጣሪ ነው፦
46፥3 በሰማያት እና በምድር ውስጥ ለምእምናን ሁሉ እርግጠኛ ምልክቶች አሉ፡፡ إِنَّ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ لَآيَاتٍ لِّلْمُؤْمِنِينَ
7፥54 ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡ إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ

Want your business to be the top-listed Food & Beverage Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Adiss Abeba
Addis Ababa