Michu Media
Michuu Post is an independent media in Ethiopia.
13/06/2025
...ምዃኑ ግጡም እዩ።👇
የእስራኤል የስለላ ፣ የቴክኖሎጂ ሆነ የወታደራዊ አቅም ፈርጣማነት አንዱ ማሳያ ዛሬ ለሊት ቴህራን ላይ በፈፀመችው ጥቃት ... የኢራን የጦር ሐይሎች ኤታማዦር ሹም መሃመድ ባግሪ እና የአየር ሐይል ዋና አዛዥ አማር አል ሐዛድ ገድ*ያለሁ ማለቷ ነው።
በተጨማሪም ለኢራን የኑክሌር አቅም የጀርባ አጥንት የሆኑ ሳይንቲስቶችን ፣ ተመራማሪዎችን ፣ ወታደራዊ መኮንኖችን የገ*ደለች ሲሆን የኑክሌር ጣቢያዎችንም አውድማለች። በአጭር ቃል በጥቂት ሰአታት ውስጥ ብቻ ትልቅ ወታደራዊ ስኬትን አስመዝግባለች።
አስቡት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምና የአየር ሀይል አዛዥን ጨምሮ ብዙ ወታደራዊ መኮንኖች ገና ጦርነት ሳይጀመር ተገ*ደሉ ማለት የኢራን አጠቃላይ የወታደራዊ ሆነ ማንኛውም መረጃዎች በእስራኤል እጅ ውስጥ እንደነበረ ግልፅ ነው።
ጦርነት ማለት መረጃ ነው። ስለላ ነው። የጠላትህን እቅድና ተጨባጭ ሁኔታን አብጠርጥሮ በማወቅ መዘጋጀት ማለት ነው። የጠላትን ጥሩና መጥፎ ጎኑን በዝርዝር አውቀሃል ማለት አንድ ጥይት ሳይተኮስ ማሸነፍህን ታረጋግጣለህ።
እስራኤል የኢራንን ወታደራዊ ጎዳ ጎድጓዳ ሆነ የወታደራዊ አቅሟን ከአመራሮቹ ጀምሮ እስከ መኮንኖች ድረስ ማንኛውንም እንቅስቃሴ ለአመታት እጅግ በጥንቃቄና በሚስጥር መረጃዎችን ስትሰበስብ እንደነበረ ጠቋሚ ነው።
ኢራን በአንፃሩ በጠላት ሀገራት ተከብቤያለሁ እያለች በዚህ ደረጃ የውስጥ አቅሟ ተዘርክርኮ እስከ ኤታማዦር ሹም ድረስ ማጣቷ አስገራሚ ነው።
አሁን ባለው ሁኔታ ኢራን በደመነብስ ባላስቲክ ሚሳኤሎችን ልትተኩስና እስራኤል ላይ ጥቃት ለመፈፀም ትሞክር ይሆናል። ይህ ደግሞ ለሌላ ውድመት እራሷን መጋበዝ ነው።
የኑክሌር ጣቢያዎቿም ጋይተዋል። ያልወደመ የኑክሬል አቅም ቢኖራት እንኳን ለድርድር ይጠቅማት ይሆን እንጂ የመተኮሱ ነገር ከማስፈራራት አያልፍም። የሆነው ሆኖ እስራኤል በአመዛኙ የምትፈልገውን ሁሉ በአጭር ሰአታት ውስጥ አሳክታ የኢራንን በትር ሰብራለች።
Michu Media
Adugna Tolera
Lemi Kura Communication ለሚ ኩራ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the public figure
Telephone
Website
Address
Addis Ababa