PR Department Getachew

PR Department Getachew

Share

Ethiopian communications authority is a legal entity that registers and regulates all types of commu

01/11/2021

ሁለተኛው የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ የጨረታ አሸናፊ በቅርቡ እንደሚገለጽ ታወቀ፡፡
መንግስት የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፉን ለውድድር ክፍት ለማድረግ በወሰነው መሠረት ዘርፉን የሚቀላቀሉ ሁለት ኩባንያዎች ለ15 ዓመታት አገልግሎቱን ማቅረብ የሚችሉበት ፈቃድ ለመስጠት በ2013 ዓ/ም በወጣው ጨረታ ግሎባል ፓርትነርሺፕ እና ኤም ቲ ኤን የተባሉት ኩባንያዎች ተወዳድረው ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ የተባለው የኩባንያዎች ጥምረት አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ባልቻ ሬባ እንደገለጹት ሁለተኛውን የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ ለመስጠት መስከረም 18 ቀን 2014 ዓ/ም የወጣው ጨረታ አሸናፊ የሚሆነው ኩባንያ በመጪው ጥር ወር ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ ለመስጠት በወጣው ጨረታ ለ126 ዓመታት ተይዞ የነበረውን የኢትዮጵያ የቴሌኮም ኢንዱስትሪ የተቀላቀለው ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ ‘ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ‘ በሚል ስያሜ አራት ታዋቂ የግል የቴሌኮም ኩባንያዎችን ይዞ ያሸነፈበትን 850 ሚሊዮን ዶላር ለመንግስት በማስገባት ወደ ስራ እንደገባ አብራርተዋል፡፡
ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ በመጪዎቹ 3 እና አራት ወራት ውስጥ ወደ ስራ እንደሚገባ የገለጹት ኢንጂነር ባልቻ ሬባ ኩባንያው ዓለም የደረሰበትንና ዘመናዊ የተባለውን የኢንተርኔት አገልግሎት በማቅረብ ተወዳዳሪ ለመሆን መዘጋጀቱን እንደገለጸ ተናግረዋል፡፡

Want your business to be the top-listed Advertising & Marketing Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30