Kufa Multimedia
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kufa Multimedia, News & Media Website, Addis Ababa.
23/05/2023
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!!💔
አሏህ ያሻውን ሰሪ…የወደደውን ፈረደ!
ለዓመታት የቀጥባሬን ሐድራ ያጋፈሩት፣የመውሊዱ አበባ የነበሩት፣ የራቲባው ድምቀት፣ የነዝሙ የመደዱ ዘዋሪው… ሸይኽ ሰልማን ወደ አኼራ ሒደዋል። የቀጥባሬን መስጂድን ለዘመናት በዒማምነት አገልግለዋል። ሸይኽ ሰልማን ለነፍሳቸው ምቾት እና ዱንያዊ ተድላ ሳይጓጉ፣ ከሼኾች ሐድራ ሳይርቁ ዘውትረው ኺድማቸውን ፈፅመዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ደረሶችን አቅርተዋል። ብዙዎችንም ለትልቅ ዓሊምነት አብቅተዋል። የቃጥባሮች ኮኮከብ ዛሬ ሌሊት ወደ አኼራ ቤታቸው ተሻግረዋል።
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
የሸይኻችን ስርዓተ ቀብር ነገ ማክሰኞ ከዙሁር ሶላት ስግደት በኋለ በቃጥባሬ ሐሪማ ቅጥር ግቢ ይፈፀማል።
መድረስ የቻልን ለቀብር ኹላችንም እንድረስ። ያልቻልነው ደግሞ በያለንበት ዒማማችንን በፋቲሃ እናውሳቸው!!💔
ተተኪያቸውን አላህ አያሳጣን
06/05/2023
የህገወጡ የአዲስ አበባ መጅሊስ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አማን የአዲስ አበባን ሙስሊም ሰላም እየነሳ ሽብር እየፈጠረ ነው።
ሱልጣን አማን የሚያሰማራቸው ጎረምሶች በታላቁ አንዋር መስጊድ ከ2 አስርት አመታት በላይ ከአሱር ሰላት በኋላ በመስጊዱ ማይክ የሚደረገው ዳእዋ ካልቆመ እርምጃ እንወስዳለን ብለው ሰሞኑን አንዋር መስጊድን የሁከት ማእድ ለማድረግ ከርቀት ቦታ እየተጠራሩ በመምጣት ችግር እየፈጠሩ ሁከት ቀስቃሽ ድርጊቶችን እየፈፀሙ ይገኛል።
በነገው እለት ሚያዝያ 28/2015 በጉለሌ ሙስሊም መቃብር መስራች ሸህ ሀሰን በቱል ስም የሚዘጋጀው ዓመታዊ መውሊድ አይከናወንም በማለት በሱልጣን አማን የሚመራው ህገወጡ መጅሊስ በማዘዙ የሸህ ሀሰን በቱል የልጅ ልጆች ያዘጋጁትን ዓመታዊ መውሊድ ፖሊስ አታደርጉም ብሎ እክል እየፈጠረ ያለበት ተጨባጭ ላይ እንገኛለን።
ይህ ሁሉ እየተፈፀመ ያለው የአዲስ አበባን ሙስሊም ወደ ሁከት በማስገባት ህዝበ ሙስሊሙን ለማጋጨት ሆን ተብሎ የተጠነሰሰ ሴራ ነው። መንግስትና ህዝብ የህገወጡ መጅሊስ መሪ አቶ ሱልጣን አማን እና አጋፋሪው አቶ መሀመድ አባተ የሚፈፅሙትን የሽብር ተግባር የማስቆም ግዴታ አለባቸው። ያ ሳይሆን ቀርቶ በታላቁ አንዋር መስጊድ እና በጉለሌ ሙስሊም መቃብር ግጭት ቢነሳ ለሚፈጠረው ችግር አቀነባባሪዎቹ የህገወጡ መጅሊስ አመራሮች እንደሚሆኑ መታወቅ አለብት።
የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ማሕበር
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa