New Line College

New Line College

Share

Maytsebri New Line College

10/04/2026

☦️ መልካም የስቅለት በዓል! ☦️

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ በሙሉ፦

"እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!"

ይህ በዓል፦

የሰላም🕊️

የፍቅር ❤️ እና

የበረከት ✨

እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን!

09/04/2026

ቢሮው በአዲስ እሳቤዎች እና ተግባራዊ አፈፃፀማቸው ዙሪያ ለጠቅላላ ሰራተኞች ስልጠና መሰጠቱን ገለፀ።

የአብክመ ሥራ እና ክህሎት ቢሮ በዘርፍ አዲስ እሳቤዎች እና ተግባራዊ አፈፃፀማቸው ዙሪያ ለጠቅላላ ሰራተኞቹ ልዩ ስልጠና በተቋማት አቅም ግንባታ: አግባብነት እና ጥራት ማረጋገጫ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር በአቶ ሙላው ልመንህ መሰጠቱን አሳወቀ። አቶ ሙላው “ የተቋሙ አዲስ እሳቤዎችና የሪፎርም አምዶች ” በሚል ርዕስ ዙሪያ ስልጠናውን በጥልቀት ያቀረቡ ሲሆን ስልጠናው የቢሮው እሳቤዎች እና አፈፃፀማቸውን ከጠቅላላ ሰራተኞች ጋር የጋራ ተደርጓል። ከዚሁ ጋር በማያያዝ አቶ ሙላው ለዘርፍ እሳቤዎች ስኬታማነት ሠራተኛው እራሱን በፈጠራ፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እና በዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ዘዴዎች አቅማቸውን ማሳደግ ይኖርብናል ብለዋል። እንደ አቶ ሙላው ልመንህ ገለፃ ዛሬ የሥራ ቦታዎች በፈጣን ለውጥ ላይ ናቸው። በመሆኑም አሉ እሳቸው የዘርፍ አዲስ እሳቤዎችን በፍጠነት በመቀበላችን እና በመተግበራችን ዛሬ ላይ ተቋማት አጠቃላይ አቅም በማሳደግ ተመራጭ መሆን ጀምረዋል። አቶ ሙላው ለዚህ ስኬት የእያንዳንዱ ሰራተኛ ድርሻ የጎላ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። በተለይ ዲጂታል መሳሪያዎችን በመጠቀም የአገልግሎት ፍጥነትን እንዴት ማሳደግ እንደምንችል ተምረናል ብለዋል።

በመጨረሻም የቢሮው ሃላፊ ዶ/ር ስቡህ ገቢያው ይህ ዓይነቱ ስልጠና በቀጣይም በተደጋጋሚ ይካሄዳል ብለው ገልጸዋል። ይህም ከጀመርነው የሪፎርም ስራ አንፃር የቢሮው ሰራተኞችን ብቃት ለማጎልበትና የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል ያግዛል ብለዋል።

የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ክፍል

08/04/2026

Call for Papers: 2nd Annual National Research Conference 📢

Debark University invites researchers and academics to submit papers for our upcoming national conference on
May 17–18, 2026.

📍 Thematic Areas:**
*Sustainable Agriculture & Environmental Management
* Tourism Development & Heritage Management
* Indigenous Knowledge

📅 Key Dates:
Abstract Deadline:April 14
Full Paper Submission: April 24–28
Acceptance Notification: May 4

📝 Submission Highlights:
Abstracts: Max 250 words
Papers: Max 10 pages (MS Word)
Publication Opportunity: *Ras Dejen Journal of Science*

📧 Contact/Submit: [email protected]
[email protected]

02/04/2026

📝ማስታወቂያ🔔
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚዘጋጅባቸውን የትምህርት ዓይነቶችና የክፍል ደረጃዎች ይፋ አድርጓል።

በዚሁ መሠረት፡-
1) ፈተና የሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች በተፈጥሮ ሳይንስ እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪና ፊዝክስ ሲሆኑ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስ ናቸው።

2) ፈተናው በየትምህርት ዓይነቱ ከ9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን ሁሉንም ምዕራፎች የሚሸፍን ይሆናል። የዝግጅት አግባቡም 9ኛ ክፍል ላይ የቀድሞውና የአዲሱ ስርዓተ ትምህርቶች የጋራ ይዘት (Common Contents) ላይ ያተኩራል። ከ10ኛ እስከ 12ኛ ከፍል ያለው በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ላይ የተመሠረተ ይሆናል። የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ግን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት ሆኖ ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን የሚሸፍን ይሆናል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Addis Ababa