Ethio Fact Info
ቅንልብ ያላቸው ሁሌም ደስተኞች ናቸው
18/09/2025
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኤርትራ ምላሽ ሰጠ
ኢትዮጵያ አሁን ላይ የባህር በር ያስፈልጋታል ወይስ አያስፈልጋትም የሚለውን መመለስ የምንችለው እኛና እኛ ኢትዮጵያዊያን ብቻ ነን ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ይህንን የገለጸው በባህር ጥያቄ ላይ በኤርትራ በኩል የሚሰነዘሩ ሀሳቦችን በተመለከተ ማብራሪያ በሰጠበት ወቅት ነው።
የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት በሰጠው ሳምንታዊ መግለጫ፤ 4 ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጓል። እነርሱም የሕዳሴ ግድብ መመረቅ እና ዲፕሎማሲያዊ አድምታዎቹን፣ ባሳለፍነው ሳምንት የተከናወኑ የአፍሪካ ካሬቢያን ሀገራት እና የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን በተለመለከተ እንዲሁም፤ በቀጣይ ሳምንት በሚከናወነው 80ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጉባኤን የተመለከቱ ናቸው።
ቀጣይ ሳምንት በሚካሄደው 80ኛው የተባበሩትን መንግሥታት ድርጅት ጉባኤ መስራች የሆነችው ኢትዮጵያ በዚህ ጉባኤ ተሳታፊ ከሆኑ ሀገራት መካከል ስትሆን፤ ብሔራዊ ጥቅሟቿን ለማስጠበቅ ትሳተፋለች ሲሉም የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ተናግረዋል።
አምባሳደሩ "ከሰሞኑ በተለያዩ መድረኮች የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የባህር በርን በተመለከተ እየሰጡት ያለውን አስተያየት አስመልክቶ የኤርትራ መንግሥትን ምላሽ እንዴት ይመለከቱታል?" ተብለው ተጠይቀዋል።
ይህንን ሲመልሱም፤ የባህር በር አስፈላጊነትን በሚመለከት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እንዲሁም ከፍተኛ አመራሮች በተደጋጋሚ የተገለጸ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም "የባህር በር ለምን እንደሚያስፈልግ የምናውቀው እኛ ኢትዮጵያዊን ብቻ ነን!" ያሉ ሲሆን ለምን እንደሚያስፈልገን በግልፅ አስቀምጠናል" ሲሉም ገልጸዋል። ይህንን ማግኘት የምንችልበት ሰላማዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ፣ ፍትሀዊ እና ሕጋዊ መንገድ በተመለከተ ይሆናል ሲሉም አስረድተዋል።
ይህ የባህር በር አስፈላጊነት በተመለከተ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ሀገራት መሪዎች ጭምር መገለጹን አስረደተዋል። ከሰሞኑ የሶማሊያው ፕሬዝዳት ሀሰን ሼክ መሐመድ በሰጡት ቃል መልልስ ላይ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ያለው ነው ማለታቸው መዘገቡ ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ "ዛሬ የኛ የሆነውን ቀይ ባሕርን መልሶ ለመጠየቅ የሚሰጋ፣ የሚጠራጠር ትውልድ መፈጠሩ የሥነ-ልቦና ስብራት አካል ነው" ማለታቸው ይታወሳል፡፡
25/06/2025
ፕሬዚዳንት ረጀብ ጣይብ ኤርዶኻን እና ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሔግ ተወያዩ .....................
የቱርኪዬው ፕሬዚዳንት ረጀብ ጣይብ ኤርዶኻን እና ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዘ ሔግ እየተካሄደ ካለው የኔቶ ጉባኤ ጎን ለጎን ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
ሁለቱ መሪዎች በትናንትናው ዕለት ባደረጉት ውይይት በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ እንዲሁም የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። ፕሬዚዳንት ኦርዶኻን በዚሁ ወቅት በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጥረት የተደረሰውን የእስራኤል እና የኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት በበጎ እንደተቀበሉት ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ፣ በጋዛ ያለው ቀውስ እንዲያከትም እና በዩክሬን ጉዳይ ላይ ንግግር እንዲቀጥል መጠየቃቸውን የቱርኪዬ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል። ሀገራቸው በኢነርጂ፣ በኢንቨስትመንት እና በመከላከያ ዘርፍ ከአሜሪካ ጋር በትብብር መሥራት የምትችልባቸው አማራጮች መኖራቸውን ገልጸዋል።
በተለይም በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚደረገውን የንግድ ልውውጥ ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር ከፍ የማድረግ ዓላማን ለማሳካት የሚያስችል ዕድል እንዳለም መጠቆማቸው ነው የተገለጸው። ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች በኔቶ ውስጥ ግንባር ቀደም አጋሮች በመሆን የድርጅቱን የመከላከያ አቅም ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል ሲል የዘገበው አናዶሉ ነው።
12/05/2025
"ከምስጉን ታዎቂ የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት የተላከ መልዕክት
"ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ: ስራ የምናቆመው:-
1. የተሻለ ህክምና እንደሚገባህ ስለምናምን የጤና ስርዓቱ ይሻሻል ብንል ሰሚ ስለአጣን ነው።
2. ታመህ ወደ ጤና ተቋም ስትሄድ ፊቱ ደስተኛ የሆነና ለማገልገል ዝግጁ የሆነ ሐኪም ታገኝ ዘንድ ነው::
3. መታከም በፈለግህበት ሰዓት ሁሉ ሄደህ ሐኪሙ የለም ሳትባል የሚመለከተውና የተሻለው ባለሞያ ጊዜ ሰጥቶ ያይህ ዘንድ ነው።
4. ማማከር የምትፈልገውን በነፃነት የምታማክርበትና በነፃነት እንደቤትህ የምትቆጥረው ጤና ተቋም ይኖርህ ዘንድ ነው።
ባይሆንማ ኖሮ የጤና ባለሞያው ቢነግድ ማትረፍ ፣ ቢያርስ ማምረት ፣ ቢፈልግ ደግሞ ሀገር ጥሎ የተሻለ ቦታ መሄድ የሚችል እንደሆነ ይታወቃል::
ሀገር ስታድግ ዜጎቿ የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ እንጂ የተገላቢጦሽ የተማሩና ህዝብ የሚያገለግሉ ልጆቿ እንዲራቡ የሚሆኑት በስርዓት ችግር እንጂ በሀገር አቅም ማጣት አይደለም።
ስለዚህ ስለነገው የጤና ስርዓት ስትል አግዘን። ከጎናችንም ሁን። ስርዓቱ ሲስተካከል ደግሞ ሌት ተቀን እንደምናገለግልህ ቃላችን ነው።"
Dr. DEBOL
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Addis Ababa