Kolfe Media Network

Kolfe Media Network

Share

Committed to deliver reliable information to our Facebook community.
ትክክለኛ እና ወቅ?

29/07/2023
Photos from Kolfe Media Network's post 09/07/2023

የአዲስ አበባ ምክር ቤቱ የከተማ አስተዳደሩን ለ2016 ዓ.ም በጀት አመት የ140.29 ቢለየን ብር በጀት አፀደቀ፤
---------
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደሩን የ2016 ዓ/ም በጀት እቅድ መርምሮ ያፀደቀ ሲሆን
በበጀት አመቱ:-
=> ለመደበኛ በጀት ወጪዎች ብር 23,498,446,197.00
=> ለካፒታል ወጪዎች 69,336,835,072.00
=> ለመጠባበቂያ በጀት 5,300,000,000.00
---
ለክፍለ ከተሞች:-
=> መደበኛ በጀት ወጪዎች ብር 33,498,495,001.00
=> ለፒታል ወጪዎች 8,657,773,794.00 የመደበ ሲሆን፣
በጥቅሉ ለከተማ አስተዳደሩ የ140,291,550,064.00 ብር በጀት ለመደበኛ፣ ካፒታልና መጠባበቂያ በጀት አፅድቋል፡፡

የበጀት እቅዱን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብድር ቃድር ሬድዋን እንደገለፁት አጠቃላይ አሁናዊ በጀቱ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር የ40% እድገት እንዳለው ገልፀው የተያዘውን በጀት ለማሳካት ከታክስ ነክና ታክስ ነክ ካልሆኑ ገቢዎች፣ ማዘጋጃቤታዊ፣ መንገድ ፈንድ፣ የውጭ እርዳታ የውጭ ብድር ገቢን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ኃላፊው አክለው እንደገለፁት የገቢና ወጭ አፈፃፀምን ለማሳካት የኢኮኖሚውን እድገት ማስቀጠል፣ ምርታማነትንና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ ከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ በትኩረት የሚሰራበት ይሆናል ብለዋል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Bethel
Addis Ababa