BMB TUBE
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from BMB TUBE, Information Technology Company, Addis Ababa.
23/02/2025
" በኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር ቱርካናና ዳሰነች አከባቢ በተከሰተዉ ግጭት እስካሁን 5 ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል " - የዳሰነች ወረዳ አስተዳደር
⚫️ " በአከባቢዉ ዛሬ ከማለዳዉ 2 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ከፍተኛ ተኩስ ነበር ! "
በጎረቤት ሀገር ኬንያ ቱርካና እና ኢትዮጵያ ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች አከባቢ በአሳ ማጥመጃ ጀልባና መረብ ስርቆቶች እንደተነሳ በተገለጸ የአርብቶ አደሮች ግጭት ባለፉት ሶስት ቀናት 5 ኢትዮጵያዊያን መገደላቸውን የዳሰነች ወረዳ አስተዳደር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።
የደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ 28 ቀበሌዎች ከጎረቤት ሀገር ኬንያ ጋር ድንበር የሚጋሩ ሲሆን በአከባቢዉ በሁለቱ ሀገራት አዋሳኝ ላይ ከሚገኘው የቱርካና ሀይቅ አሳ በማስገር ስራ የአከባቢው አርብቶ አደሮች በጋራ ሲጠቀሙ የቆዩ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኦሞ ወንዝ መሙላቱን ተከትሎ በኢትዮጵያ በኩል የአሳ ምርት መበራከቱንና የኬንያ አርብቶ አደሮች ወደ ኢትዮጵያ ዘልቀዉ የመግባትና የአሳ ማስገሪያ መረብና ጀልባዎች (ዛተራ) የመስረቅ አዝማሚያዎች እየተበራከቱ መምጣታቸውን የዳሰነች ወረዳ አስተዳዳር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል።
ይህን ተከትሎም ባሳለፍነዉ ሳምንት በኬንያ ቱርካና ግዛት የአከባቢው አስተዳዳሪዎች ጋር በመነጋገር መግባባት ላይ በመድረስና ከሁለቱም አከባቢ አርብቶ አደሮች ጋር ለመወያየት ቀጠሮ ተይዞ በነበረበት የኬንያ አርብቶ አደሮች ከትላንት በስቲያ ሁለት ኢትዮጵያዊያንን በትላንትናው ዕለት ደግሞ ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላትን መግደላቸዉን ተከትሎ የዳሰነች አርብቶ አደሮች አስከሬን ለመዉሰድና ለአፀፋ ተኩስ ከፍተዉ እንደነበር የወረዳዉ መንግስት አስታውቋል።
👉
19/02/2025
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በግፍ የተጨፈጨፉበት ቀን !
የካቲት 12 የጣልያኑ ማርሻል ሩዶልፍ ግራዚያኒ ላይ ለተደረገው የግድያ ሙከራ ጣልያን በአፀፋው የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን የጨፈጨፈችበት ቀን ነው፡፡
በወቅቱ እስከ 30,000 ሰዎች እንደሞቱ የተገመተ ሲሆን በጊዜው የከተማዋን ነዋሪዎች 20 ከመቶ ያህል ነው ተብሏል፡፡
የጣልያኑ የጦር መሪ ግራዚያኒ በቀድሞው ቤተመንግሥት በአሁኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ " ለኢትዮጵያ ህዝብ ስጦታ እሰጣለሁ " በሚል ዜጎቻችን ይሰበስባል።
በዝግጅቱ ላይ ኣብርሃም ደቦጭ ፣ ሞገስ ኣስግዶም ፣ ስምኦን ኣደፍርስ ፣ ስብሃት ጥሩነህ እና ሌሎች ወጣቶች ቦንብ ይዘው ወደ ስብሰባው ገቡ፡፡
በተለይ ኣብርሃም ደቦጭ እና ሞገስ ኣስግዶም በኤርትራ በነበሩበት ወቅት የጣሊያን መንግሥት በኤርትራ ሕዝብ ላይ ይፈጽም የነበረውን ግፍ ያውቁ ሥለነበር ከፍተኛ ቁጭት ነበረባቸው፡፡
ወጣቶቹ ወደ አዳራሹ እንደገቡ ግራዚያኒ ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ ፣ ስለ አርበኞች እና ስለ ንጉሡ በንቀት ይናገር ነበር፡፡
ወጣቶቹ በግራዚያኒ የንቀት ንግግር እና በስብሰባው ውስጥ በታደመው ተሰብሳቢ ተናደዱ፤ ወደ ግራዚያኒ ቀስ ብለው በመጠጋት ሰባት ቦንቦችን በተከታታይ ወረወሩ፡፡
ተሰብሳቢው የመጀመሪያው የቦንብ ፍንዳታ የደስታ ርችት መስሎት ስለነበር አልተደናገጠም፡፡
በ2ተኛው የቦንብ ፍንዳታ ግራዚያኒ ተመትቶ ብዙ ቦታ ላይ ቆሰለ፣ የጦር ኃይል አዛዥ የነበረውን አውራሊያ ሊአታ አይኑ ጠፋ፤ እግሩ ተቆረጠ፡፡ ሌሎች ሹማምንትም ሕይወታቸው አለፈ።
ይህን ተከትሎ ነው ግራዚያኒ አ/አ ነዋሪዎችን በግፍ የጨፈጨፈው።
እለቱ ለ88 ጊዜ በአ/አ 6 ኪሎ በሚገኘው መታሰቢያ ሀውልት ተከብሯል።
ማጣቀሻ ፦ ኢትዮጵያና የጣልያን ጦርነት (ጳውሎስ ኞኞ)
👉
19/02/2025
ልዩ ዜና ትግራይ
“ በሃይማኖት አባቶች የተጀመረው የሽምግል እና የእርቅ እንዲሁም የካቲት 11 በጋራ የማክበር እንቅስቃሴ አልተሳካም አሉ “ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ።
ፕሬዜዳንቱ ለእርቅ እና ሽምግልና አለመሳካት “ ቡድን “ ሲሉ የጠሩትን አካል ተጠያቂ አድርገዋል።
ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባወጡት መግለጫ “ መንግስት የማያውቀው ርችት በመተኮስ የሚያጋጥም ችግር ካለ ተጠያቂው ቡድኑ ነው “ ብለዋል።
አላስፈላጊ የአመፅ እንቅስቃሴዎች እየታዩ መሆናቸው የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ፤ ህዝቡ አከባቢውን በልዩ ሁኔታ በመጠበቅ በዓሉ እንዲያከብር አሳስበዋል።
ከቀናት በፊት ለእርቅና ሽምግልና ፍቃደኛ መሆናቸው በትግራይ የሃይማኖት አባቶች መግለጫ የተሰጠባቸው ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳና የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በትናንቱ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እጅ ለእጅ ሲጨባበጡ የሚያሳይ ፎቶ መለቀቁ ብዙዎች አስደስቶ ነበር።
👉
16/02/2025
* የፕሪቶሪያውን ስምምነት
የፕሪቶሪያውን ስምምነት በሚመለከት በአፍሪካ ሕብረት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሄደ
በትግራይ ክልል የነበረውን ግጭት ያስቆመው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሂደትን በተመለከተና ከስምምነቱ "ሌሎች ምን እንማር?" በሚል ርዕስ ዛሬ የካቲት 9ቀን 2017ዓ.ም
በአፍሪካ ህብረት ሪፓርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
በዚህ ውይይት ላይም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና የህወሓት ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል(ዶ/ር) የተገኙ ሲሆን ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌድዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ፣ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ መሐመድ እድሪስ እና ሌሎች ተገኝተዋል።
የፕሪቶሪያውን ስምምነትና አፈፃፀም የተመለከተውን ሪፓርት ደግሞ ተሰናባቹ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፉኪ ማህማት፣ የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪ ቡድን ሰብሳቢ ኡሊሲንጎን ኦባሳንጆ እና ከፍተኛ ኮሚሽነሮች አቅርበዋል።
ከአንድ ሰአት በላይ የዘለቀ ውይይት ከተካሄደ በኋላ አቶ ጌታቸው ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa