MINI SPORT

MINI SPORT

Share

★አመቱን ሙሉ ስለ ስፖርት ይዘገባል!

03/04/2023

" ለሊቨርፑል ፍንጭ አልሰጥም "

ዋና አሰልጣኙን ያሰናበተው የለንደኑ ክለብ ቼልሲ በነገው የሊቨርፑል ግጥሚያ ቡድኑን የሚመሩት ጊዜያዊ አሰልጣኝ ብሩኖ ሳልተር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ጊዜያዊ አሰልጣኝ ብሩኖ ሳልተር በቆይታቸውም :-

" እዚህ የመጣሁት ክለቡ ይህ ትክክለኛ እርምጃ ነው ብሎ ስለሚያስብ ነው ፣ ትልቅ ፈተና ነው ነገር ግን ብዙ ልምድ አለኝ ተጫዋቾቹን ለመርዳት እሞክራለሁ እንደምችል ይሰማኛል።

- ከክለቡ አስተዳደር ጋር አውርቼ ነበር ከጎኔ እንደሆኑ እና እንደግለሰብ እንደሚደግፉኝ ነግረውኛል።

- ከአስቶን ቪላ ጋር በነበረን ግጥሚያ ጨዋታውን ተቆጣጥረን ነበር እንቅስቃሴው ጥሩ ነበር ነገር ግን በአንዳንድ ስህተቶች ተሸንፈናል።

- ያለፉትን ሀያ አራት ሰዓታት መግለጽ አልችልም በጣም ከባድ ነበር አሁን በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መገኘት እና ከተጫዋቾች ጋር ተገናኝቶ መነጋገር ትንሽ ይከብዳል።

- በነገው ጨዋታ የምንጠቀመውን አሰላለፍ በተመለከተ ለሊቨርፑል ምንም አይነት ፍንጭ መስጠት ስለሌለብኝ አልናገርም።

- ሊቨርፑል መጥፎ የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ ናቸው ነገር ግን ምርጥ ተጫዋቾች አሏቸው ፣ ዝግጁ መሆን አለብን።" ሲሉ ተደምጠዋል።

ለፈጣን መረጃዎች እና በቀጥታ ስርጭት ጨዋታዎችን ለመከታተል በቴሌግራም ይከተሉን

👉👉👉👉👉👉👉👉👉 https://t.me/mnisport

28/03/2023

#ከምሽቱ ጨዋታ በኃላ አሰልጣኝ ውበቱ እንዲህ ብለዋል

"ከእኔ በብዙ እጥፍ አቅም ያለው ሰው በዚህ ቦታ ላይ ቢቀመጥም አቅም ያላቸው ተጫዋቾች እነዚሁ ናቸው"

👇
#አሰልጣኙ ውበቱ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል:-

➡በባለፈው ጨዋታ ከመሸነፋችን ጋር ተያይዞ ተጫዋቾቹ ላይ ትንሽ ከአህምሮ ጋር የሥነ-ልቦና ትግል ጋር ነበረን.....
➡ከዓርቡ ጨዋታ ዛሬ በኳስ ቁጥጥርም ሆነ ወደ ጎል በመድረስ የተሻለን ነበር.....
➡ለአፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ ያለን ዕድል በጣም ጠባብ ነው።እርግጥ 100% የማለፍ ዕድላችን አክትሟል ማለት አይቻልም

➡ለረጅም ጊዜ የሚጫወቱ ተጫዋቾችን ማግኘት ከባድ ነው።
➡ ከእኔ በብዙ እጥፍ አቅም ያለው ሰው በዚህ ቦታ ላይ ቢቀመጥ አቅም ያላቸው ተጫዋቾች እነዚሁ ናቸው..... ጥራት ያላቸው ተጫዋቾችን የማፍራት ስራ ላይ መሰራት አለበት። ባለው ነገር ግን የምንችለውን ነገር ለማሳየት ሞክረናል....

🔛እንደ ሀገር የ 9 ቁጥር አጥቂ ተጫዋች የለንም። 9 ቁጥር ሆኖ በዛ ቦታ ልብ የሚያስደፍር ተጫዋች የለንም ፣ አንዳንዴ ማነፃፀር ይገባናል.....

➡ ከባለፈው ጨዋታ ስናነፃፅረው የዛሬው ጨዋታ የተሻለ ነበረ... ከጎል ጋር ተያይዞ ግን በርካታ ተጫዋቾች ጎል ጋር እየደረሱ እና የግብ ዕድሎችን እየፈጠሩ ነበረ ....

# ማጣሪያውን ለማለፍ በእርግጥ 100% ዕድላችን አክትሟል ማለት አይቻልም። በሂሳባዊ ስሌት ሙሉ ለሙሉ ውጪ አይደለንም ፤ ግን ዕድሉ ጠባብ ነው....

በብሔራዊ ቡድናችን ላይ ያለዎትን ሀሳብ ያጋሩን ?

ለፈጣን ስፖርታዊ መረጃዎች በቴሌግራም ፦

https://t.me/mnisport

Photos from MINI SPORT's post 24/03/2023

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቢጫ ማልያ ፥ ቀይ ቁምጣ እና ቢጫ ካሶተኒ ለብሶ ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል። ተጋጣሚያችን ጊኒ ደግሞ ቀይ ማልያ ፣ ቢጫ ቁምጣ እና አረንጓዴ ካሶተኒ በመልበስ ወደ ሜዳ ይገባል።

ጨዋታው ከምሽቱ 5፡30 ላይ ካዛብላንካ በሚገኘው መሐመድ አምስተኛ ስታዲየም ይደረጋል።

ጨዋታውን በቀጥታ ይከታተሉ ። ለጓደኞችዎ ሼር ያድርጉ ።

ጨዋታወሰን በቀጥታ ለመከታተል በቴሌግራም

👉👉👉 https://t.me/mnisport ጆይን አድርገው መከታተል ይችላሉ

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addiss Abeba
Addis Ababa