Aster G
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Aster G, Health/Beauty, Addis abeba, Addis Ababa.
10/08/2023
የምናተርፈው ከዘላቂ ሠላም እንጂ ከጥላቻና ቁርሾ አይደለም!!
ሠላም በጥላቻ፣በግጭትና በጦርነት ሲተካ ሀገራት በቀላሉ እንደሚፈርሱ ፣ ዜጎችም አገር አልባ ተሰዳጅ እንደሚሆኑ እነ ሊቢያና ሶሪያ የዛሬዎቹ አብነቶቻችን አይደሉምን?
ስለሠላም ሲባል ሁሉንም አማራጮች ማጤን ብልህነት ነዉ። ዘላቂ ሠላምን ማስፈን በራሱ የአንድ ሀገር ግንባታ ትልቁ አካል ነዉ ቢባል ትክክል ሊሆን ይችላል ።
ምክንያቱም የሠላም ግንባታዉ አስተማማኝ መሠረት ላይ ያልቆመ ሀገር አገራዊ ፍላጎቶችን ማሟላት ይቸገራልና።
ስለዘላቂ ሠላም ሲታሰብ ስለዘላቂ ሀገረ መንግስት ግንባታ፣ ልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ ማሰብ ነዉና ሠላምን ለማረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን ማበርከት ይጠበቅበታል ።
የሠላም መደፍረስ የሥነ ልቦና ቀዉስን ሲያስከትል፣ ቁሳዊ ፣ ሰብአዊና ማህበራዊ ቀዉሶችን ሲያፈራርቅ ኖሯል።
የዛሬዉም ሆነ የነገዉ ትዉልድ የሚያተርፈው ከዘላቂ ሠላም ነዉ። ቂምና ጥላቻ ግጭትን ሲወልዱና ሲያዋልዱ እንጂ ለዘላቂ ሠላም መደላድል ሲፈጥሩ አልታዩም።
ዘላቂ ሠላም ኢትዮጵያ ለጀመረችዉ የብልጽግና ጉዞ መሠረት ነዉ። በዚህም መነሻ በብልጽግና ፓርቲ የሚመራዉ መንግስት ከታጠቁ ኃይሎች ጋር ጭምር በሀሳብና በንግግር ችግሮችን በመፍታት ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን ተነሳሽነት ወስዶ እየሠራ ይገኛል።
ይህን ዘላቂ ሠላምን የማረጋገጥ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ።ልዩነቶችን በሀሳብና በንግግር በማረቅ ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን ሁሉም ኃይሎች የየበኩላቸውን ኃላፊነት መወጣት አለባቸው ።
በተዛባ ትርክት ወደ ተዛባ አቅጣጫ የሚነጉዱ ኃይሎች በዜሮ ድምር ፖለቲካ ዉስጥ ከመዳከር የተለየ ዉጤት ሊያመጡ አይችሉም።
ማናቸዉንም ጥያቄዎች ማንሳት፣ መጠየቅ የሚያስችል ግልጽ የዴሞክራሲ ስርዓት ባለበት አዉድ ኃይልና ነፍጥ መፍተሔ መሆን አይችሉም።
ወደስክነት፣ ወደ ሚዛናዊነት፣ ወደ ህገ መንግታዊነትና ወደ ህጋዊነት መርህ መመለስ ያሻል።
09/08/2023
ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ!!
--------
የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ተግባራት ገምግሟል፡፡ የዕዙ የመጀመሪያ ምዕራፍ ዕቅድ በባሕር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ በደብረ ብርሃን፣ በላሊበላ፣ በጎንደርና በሸዋ ሮቢት አካባቢ የተሰባሰበውን በዘረፋ እና በጥፋት የተሰማራ ቡድን በመምታትና ከተሞቹን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ መመለስ ነበር። እነዚህ አካባቢዎች የተመረጡት ብዙ ሕዝብ የሚኖርባቸው፣ ከፍተኛ የንግድና የቱሪስት እንቅስቃሴ ያለባቸው፣ የፖለቲካና የኢንዱስትሪ ማዕከላት በመሆናቸው ነው።
በዚህ መሠረት በስድስቱ ከተሞች ዙሪያ የመጣው የጥፋት ቡድን መሣሪያውን እንዲያስረክብና እጁን እንዲሰጥ የተሰጠውን ዕድል ባለመጠቀሙ እርምጃ ተወስዶበታል፣ የሕግ የበላይነትም እንዲከበር ተደርጓል። የክልሉ ሕዝብ በዚህ ዘራፊ ቡድኑ የተማረረ በመሆኑ፣ የህግ አስካባሪ አካላት ተልዕኮዋቸውን በስኬት እንዲወጡ ተገቢውን ድጋፍ አድርጓል። ጠቅላይ መመሪያ እዙም የክልሉ ህዝብ ላደረገለት ትብብር ምስጋናውን ያቀርባል።
በአሁኑ ሰዓት ከተሞቹ ከዘረፊዉ መንጋ ስጋት ነጻ ሆነዋል። የመከላከያ ሠራዊቱ እና የክልሉ ህግ አስከባሪ አካላት በየሥርቻው የተራረፈውን ዘራፊ በማጽዳት ላይ ናቸው። ማኅበረሰቡም መረጃ በመስጠት፣ አቅሙ በፈቀደው ሁሉ ለዚህ ስራ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ሽንፈት የተከናነበው የፅንፈኞች ቡድን በአንዳንድ አካባቢዎች ወደ ቅርስ ቦታዎችና የእምነት ተቋማት በመግባት ለመደበቅ እየሞከረ ነው።
የመከላከያ ሠራዊቱ እና የክልሉ ህግ አስከባሪ አካላት ህግ፣ ሥርዓትና ሞራልን ባከበረ መንገድ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛል። በቀጣይም የመጨረሻውን የማጽዳት እና የመልቀም ተግባር በማከናወን ከተሞቹ በአጭር ጊዜ ወደ ተሟላ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለሱ ይደረጋል።
በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የጠቅላይ መምሪያ ዕዙ እስካሁን 14 ተጠርጣሪዎችን በአዲስ አበባ ከተማ በቁጥጥር ሥር ያዋለ ሲሆን ወደፊትም እንደሁኔታው በቁጥጥር ሥር የሚያውላቸውን ግለሰቦች አስመልክቶ አስፈላጊውን መረጃ ለህዝብ ይፋ ያደርጋል።
በመጀመሪያው ምዕራፍ ዕቅድ የተያዘው ከተሞቹን ከዘራፊ የጥፋት ቡድን የማጽዳቱ ተግባር እየተጠናቀቀ በመሆኑ፣
1. ከሐሙስ ነሐሴ 4 ጀምሮ ከላይ በተጠቀሱት ከተሞች መደበኛ የአውሮፕላን በረራ ይጀመራል፤
2. ከባጃጅና ከሞተር ሳይክል በስተቀር ሁሉም ዓይነት የከተማ የትራንስፖርት አገልግሎቶች ወደ አገልግሎት ይገባሉ፤
3. የመንግሥት፣ የማኅበረሰብ አገልግሎት፣ የንግድ፣ የጤና፣ የፋይናንስ፣ ወዘተ. ተቋማት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል።
በዚሁ አጋጣሚ የክልሉ ሕዝብ ራሱን ከዘራፊውና ከጽንፈኛው መንጋ በመነጠልና በመከላከል፣ ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር በመሰለፍ ላደረገው ተጋድሎ ዕዙ በድጋሚ ምስጋናውን ያቀርባል።
ነሐሴ 3 ቀን 2015 ዓም
አዲስ አበባ
የአስቸይኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Abeba
Addis Ababa