Henok
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Henok, Education, Addis Ababa.
እራሳችንን እንመርምር አዕምችን በምን እንደተሞላ እንመልከት
የውሳጣችሁን 'ትርምስ' ወደ 'ውበት' መቀየር ትችላላችሁ !!
በህይወታችን ሰላምና ደስታ ይሰጡናል ብለን ያሳካናቸው ነገሮች ፣ የውስጥ ውድቀታችን ምንጭ ቢሆኑስ? ዞር ብለን እንመልከት!
የውጪው ዓለም የሚሰጠን ስኬት የውስጥ ሰላማችንን ሊገዛ አይችልም። እውነተኛ ሰላም እና ደስታ የራሳችንን ውስጣዊ ትርምስ በውጫዊ ነገሮች ለመሸፈን መሞከርን ስናቆም የዛኔ ይገኛል።
ዋናው ሰላም የሚገኘው በውጪ ሳይሆን ውስጡን በመንፈሳዊ ስነምግባር፣ ዓላማን በማወቅ፣ እና ከሕሊና ጋር በመታረቅ መኖር ስንችል ነው። አቋራጭ መንገድ የለም— ትዕግስት እና ጊዜ ቢፈልግም፣ ስራህ በጊዜ ሂደት ፍሬ ሲያመጣ፣ የምትፈልገውን ደስታና ሰላም ከራስህ ታገኛለህ። አንተ ራስህ የራስህ ሀብት ትሆናለህ!
ነገ የሚባል ጊዜ የለም። አሁን ነው ያለህና አሁን ተነሳ! የራስህን ድክመት ለመሸከም አትፍራ! እዛኔ ነው መጀመር የምትችለው። ይህንን ጠቃሚ መልእክት ለምትወደው ሰው አጋራ።
22/11/2025
🎯 ዓላማ ከደስታ በላይ ነው።
በመጨረሻው የተስፋ መቁረጥ ጉድጓድ ውስጥ ስትሆን፣ ያን ጊዜ ነው እውነተኛ ክብር እና የሕይወት ትርጉም የሚገኘው። ✨
ያንን የተገነዘብኩት እኔ ሙሉ በሙሉ ስደክም ነበር። እንዴት እንደሆነ አሳያችኋለሁ።
👤 ስሜ ሄኖክ ነው።
ዓለሜ ተገልብጦብኝ ወደ የማንነት ጥያቄ ውስጥ ገባሁ፤ ኮቪድ ሲመጣ ከኔ ጋር የነበረኝ ፀጥታ ነው።
የኮሌጅ ግቢ ሲዘጋ፣ ለሁሉም ነገር መልስ ነበረኝ ብዬ የማስበው ልጄ በጭንቀት ደመና ውስጥ ዋኘው።
'እኔ ማን ነኝ? ዓላማዬስ ምንድን ነው?' የሚሉት ጥያቄዎች በቀን 24 ሰዓት አእምሮዬን ይደበድቡ ጀመር።
የምተነፍሰው አየር እንኳ ከብዶኝ ነበር።
በዚያን ጊዜ ነበር ልቋቋመው የማልችለው የማንነት ፈተና ውስጥ የገባሁት።
🛠️ ራሴን ከዚህ የማንነት ጉድጓድ ለማውጣት ያልሞከርኩት ነገር አልነበረም።
የዳዊት ድሪምስ ማንያዘዋል እሸቱ እንደጉድ በደመቁበት ጊዜ ከነሱ አንድም አልቀረኝም ነበር።
የዩቲዩብ ቪዲዮዎች
አነቃቂ ቃላት
ፖድካስቶች
መጻሕፍት እነዚህን ሁሉ ሞክሬ እንኳ የበለጠ ባዶነት ተሰማኝ። የምሞክረው በጨመረ ቁጥር፣ የምወድቀውም እንዲሁ ጨመረ።
"ከድጡ ወደ ማጡ"
እፎይታ ለማግኘት የሰጠሁት ሩጫ እስር ቤት ሆነብኝ።
✨ ታዲያ እንዴት ነበር ከዚህ ሁሉ የራሴ ጥረት አዙሪት የወጣሁት?
ዋናው ስህተቴ የተረዳሁት ያኔ ነበር።
ይህን ሁሉ የማደርገው ደስታን ለመፈለግ ነበር፣ ህመምን ለመራቅ ነበር።
ደስታ ግን የእኔን ህይወት የማያድን መሆኑን አላወቅኩም።
የሚያድነው ዓላማ (Purpose) ነው።
🧭 'ለምን እኖራለሁ?' 'ለምን እለፋ?'
የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ ስጀምር፣
ችግሮች የመጨረሻ ምልክት አይደሉም፣ የሂደቱ ክፍል ናቸው።
በሂደት ተቀየርኩ፣ ፈተናዎችንም ማሸነፍ ቻልኩ።
🙏 ይህ ታሪክ እርስዎንም የሚነካ ከሆነ
ወይም 'ዓላማ ከደስታ በላይ ነው' የሚለውን ትምህርት ከተቀበሉ፣
በአስተያየት መስጫው ላይ 👉 'ዓላማ!' ይፃፉ።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the school
Website
Address
Addis Ababa